እግዚአብሔር
25 ቁጥሮች25አማርኛሶፎ 3:17
17አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፤ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል፡” ይባላል።
ኢያ 1:9
9በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?
ዘዳ 4:29
29ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ፤ በልብህም ሁሉ በነፍስህም ሁሉ የፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።
ዳዊ 73:25
25በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ?
ዳዊ 56:3
3እኔ ግን ፈራሁ በአንተም ታመንሁ።
ኢሳ 41:13
13እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፦ አትፍራ፥ እረዳሃለሁ፡ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።
ኢሳ 25:1
1አቤቱ፥ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን ነገር የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም አመሰግናለሁ።
ዳዊ 31:3
3አምባዬና መጠጊያዬ አንተ ነህና፡ ስለ ስምህ መንገዴን አቅና ምራኝም።
1ኛ ዮሐ 4:19
19እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
ፊል 4:13
13ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።
1ኛ ዮሐ 4:16
16እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል፥ አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
2ኛ ሳሙ 7:22
22ስለዚህም፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ የለምና፥ በጆሮአችንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለምና አንተ ታላቅ ነህ።
ዕብ 3:4
4እያንዳንዱ ቤት በአንድ ሰው ተዘጋጅቶአልና፥ ሁሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሔር ነው።
ዳዊ 34:8
8እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።
ኢሳ 60:1
1ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ።
ገላ 6:7
7አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤
1ኛ ዮሐ 4:20
20ማንም፦ “እግዚአብሔርን እወዳለሁ፥” እያለ ወንድሙን ቢጠላ፥ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
ምሳ 8:35
35እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና። ከእግዚአብሔርም ሞገስን ያገኛልና።
1ኛ ዮሐ 4:12
12እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።
ኢሳ 55:8
8አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር።
ያዕ 4:10
10በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።
ፊል 4:4
4ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።
ዳዊ 16:2
2እግዚአብሔርን፦ “አንተ ጌታዬ ነህ፡” አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።
1ኛ ሳሙ 2:2
2እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።
ዘጸ 20:12
12“አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።