እቅድ ማውጣት

18 ቁጥሮች17አማርኛ

ምሳ 16:3

3ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች።

ኤር 29:11

11ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።

ሉቃ 14:28

28ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ከሳራውን የማይቈጥር ማን ነው?

ዳዊ 20:4

4እንደ ልብህ ይስጥህ፡ ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።

ምሳ 16:9

9የሰው ልብ መንገዱ ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቀናለታል።

ዳዊ 143:8

8አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።

ምሳ 15:22

22ምክር ከሌለች ዘንድ የታሰበው ሳይሳካ ይቀራል፤ መካሮች በበዙበት ዘንድ ግን ይጸናል።

ምሳ 19:21

21በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል።

መክ 3:1

1ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።

ምሳ 23:4

4ባለጠጋ ለመሆን አትድከም፤ የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው።

ኢሳ 55:8

8አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር።

ኢሳ 28:29

29ይህም ደግሞ ድንቅ ምክር ከሚመክር በግብሩም ማለፊያ ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል።

ዳዊ 90:12

12በልብ ጥበብን እንድንማር፥ ቀኝህን እንዲህ አስታውቀን።

ኢሳ 55:9

9ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።

አሞ 3:7

7በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።

ምሳ 3:31-32

31በግፈኛ ሰው አትቅና፥ መንገዱንም ሁሉ አትምረጥ።

32ጠማማ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ርኩስ ነውና፤ ወዳጅነቱ ግን ከቅኖች ጋር ነው።

1ኛ ቆሮ 2:10

10መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።