የበጎ አድራጎት ድርጅት

19 ቁጥሮች15አማርኛ

ዘዳ 15:7

7አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚኖሩ ከወንድሞችህ አንዱ ቢደኸይ፥ ልብህን አታጽና፥ በድሀው ወንድምህ ላይ እጅህን አትጨብጥ።

ዘዳ 15:11

11ድሆች ከምድሪቱ ላይ አያልቁምና ስለዚህ እኔ፦ በአገርህ ውስጥ ላለው ድሀ ለተቸገረውም ወንድምህ እጅህን ትከፍታለህ፡ ብዬ አዝዝሃለሁ።

ዳዊ 37:25-26

25ጐለመስሁ አረጀሁም፤ ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።

26ሁልጊዜ ይራራል ያበድርማል፥ ዘሩም በበረከት ይኖራል።

ዳዊ 112:9

9በተነ ለችግረኞችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘላለም ዓለም ይኖራል፤ ቀንዱ በክብር ከፍ ከፍ ይላል።

ምሳ 3:27-29

27ለተቸገረው ሰው በጎ ነገርን ማድረግ አትከልክል፥ ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን።

28ወዳጅህን፦ “ሂድና ተመለስ፤ ነገ እሰጥሃለሁ፡” አትበለው። በጎ ነገርን ማድረግ ሲቻልህ።

29በወዳጅህ ላይ ክፉ አትሥራ፥ እርሱ ተማምኖ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ።

ምሳ 11:24-25

24ያለውን የሚበትን ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፤ ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም።

25የምትባረክ ነፍስ ትጠግባለች፥ የረካም እርሱ ደግሞ ይረካል።

ምሳ 14:21

21ባልንጀራውን የሚንቅ ይበድላል፡ ለድሀ ግን የሚራራ ምስጉን ነው።

ምሳ 19:17

17ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።

ምሳ 22:9

9ርኅሩህ የተባረከ ይሆናል፥ ከእንጀራው ለድሀ ሰጥቶአልና።

ኢሳ 58:10

10ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል፥ ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።

ሕዝ 16:49

49እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ፤ ትዕቢት እንጀራን መጥገብ መዝለልና ሥራ መፍታት በእርስዋና በሴቶች ልጆችዋ ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።

ማቴ 5:42

42ለሚለምንህ ስጥ፥ ከአንተም ይበደር ዘንድ ከሚወደው ፈቀቅ አትበል።

ማር 10:21

21ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና እንዲህ አለው፦ “አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፥ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መስቀሉንም ተሸክመህ ና፥ ተከተለኝ።”

1ኛ ቆሮ 13:3

3ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

2ኛ ቆሮ 9:7

7እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።