መጽሐፈ ምሳሌ 14

AMHEVGአማርኛ35 ጥቅሶች3:07 አዳምጥ
አዳምጥ 3:07 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ብልሃተኛ ሴት ቤትዋን ትሠራለች፤ ሰነፍ ሴት ግን በእጅዋ ታፈርሰዋለች።

2በቅን የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይንቀዋል።

3በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ፤ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።

4በሬ በሌለበት ስፍራ እህል አይገኝም፤ ብዙ ሲሳይ ግን በበሬዎች ኃይል ነው።

5የታመነ ምስክር አይዋሽም፤ የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል።

6ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል አያገኛትም፤ ለአስተዋይ ግን እውቀትን ማግኘት አያስቸግረውም።

7ከሰነፍ ሰው ፊት ራቅ፥ በእርሱ ዘንድ የእውቀትን ከንፈር አታገኝምና።

8የብልህ ሰው ጥበብ መንገዱን ያስተውል ዘንድ ነው፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ሽንገላ ነው።

9ሰነፍ በኃጢአት ያፌዛል፤ በቅኖች መካከል ግን ቸርነት አለች።

10የራሱን ኀዘን ልብ ያውቃል፤ ከደስታውም ጋር ሌላ ሰው አይገናኝም።

11የኅጥኣን ቤት ይፈርሳል፤ የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል።

12ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፡ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው።

13በሳቅ ደግሞ ልብ ያዝናል፥ የደስታም ፍጻሜ ልቅሶ ነው።

14ልቡን ከጽድቅ የሚመልስ ሰው ከመንገዱ ፍሬ ይጠግባል፥ ጻድቅም ሰው ደግሞ በራሱ።

15የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።

16ጠቢብ ሰው ይፈራል ከክፉም ይሸሻል፤ ሰነፍ ግን ራሱን ታምኖ ይኰራል።

17ቍጡ ሰው በስንፍና ይሠራል፤ አስተዋይ ግን ይታገሣል።

18አላዋቂዎች ሰዎች ስንፍናን ይወርሳሉ፤ ብልሆች ግን እውቀትን እንደ ዘውድ ይጭናሉ።

19ኃጢአተኞች በደጎች ፊት ይጐነበሳሉ፥ ኀጥኣንም በጻድቃን በር።

20ድሀ በባልንጀራው ዘንድ የተጠላ ነው፡ የባለጠጋ ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው።

21ባልንጀራውን የሚንቅ ይበድላል፡ ለድሀ ግን የሚራራ ምስጉን ነው።

22ክፉ የሚያደርጉ ይስታሉ፤ ምሕረትና እውነት ግን መልካምን ለሚያደርጉ ናቸው።

23በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል፤ ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ።

24የጠቢባን ዘውድ ባለጠግነታቸው ነው፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ስንፍና ነው።

25እውነተኛ ምስክር ነፍሶችን ያድናል፤ በሐሰት የሚናገር ግን ሸንጋይ ነው።

26እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጠንካራ መታመን አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያ ይኖራል።

27ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ፡ እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው።

28የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤ በሰው ጥቂትነት ግን የገዥ ጥፋት አለ።

29ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፤ ቍጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል።

30ትሑት ልብ የሥጋ ሕይወት ነው፤ ቅንዓት ግን አጥንትን ያነቅዛል።

31ድሀን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ይሰድባል፤ ለድሀ ምሕረትን የሚያደርግ ግን ያከብረዋል።

32ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል፤ ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል።

33በአዋቂ ልብ ጥበብ ትቀመጣለች፤ በሰነፎች ውስጥ ግን አትታወቅም።

34ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ ኃጢአት ግን ሕዝብን ታስነውራለች።

35አስተዋይ አገልጋይ በንጉሥ ዘንድ ይወደዳል፤ በሚያሳፍር ላይ ግን ቍጣው ይሆናል።

ማብራሪያ

14:1 እግዚአብሔርን የማትፈራ፣ የገዛ ፈቃዷን የምትከተልና አባካኝ የሆነች፣ እንዲሁም ለራሷ ምቾት የምትገዛ ሴት ቤቷን እንደምታፈርስ ሁሉ ቤተሰቧንም በእርግጥ ታፈርሳለች።

2. እውነተኛ የጸጋና የኃጢአት መልክ እዚህ ይታያል። የእግዚአብሔርን ትእዛዛትና ተስፋዎች የሚንቁ ሰዎች እግዚአብሔርን፣ ሁሉንም ኀይሉንና ምሕረቱንም ይንቃሉ።

3. ትዕቢት በልብ ውስጥ ካለው የመራርነት ሥር ይበቅላል። ያ ሥር መነቀል አለበት፤ አለዚያም ይህንን ቅርንጫፍ ማሸነፍ አንችልም። የጠቢባን ጥንቁቅ ቃላት ከችግሮች ያወጧቸዋል።

4. ትንሽ ነገር ቢሆንም እንኳ ሰነፉን የሚያስፈራ ነገር ከሌለ ምንም ጥቅም ሊገኝ አይችልም።

5. ኅሊናዊ ምስክር ከሚያውቀው ውጪ የሆነን ነገር ለመግለጽ አይደፍርም።

6. ተሳዳቢ መለኮታዊ ነገሮችን በንቀት ይመለከታል። የራሱን ድንቁርናና ብቁ አለመሆን የተረዳ ሰው ግን መጻሕፍትን በትሑት መንፈስ ይመረምራል።

7. ንግግሩ የአምልኮ መንፈስ የሌለው ከሆነ ክፉ ሰውን እናውቃለን።

8. እኛ ተጓዦች ነን፤ ጭንቀታችንም ድንቆችን መመልከት ሳይሆን ጉዟችንን ወደ ፍጻሜ ማድረስ ነው። የምንሄድባቸውን ሕጎች፣ እንዲሁም የምንሄድላቸውን መዳረሻዎች መረዳት ይገባናል። ክፉ ሰው ራሱን ያታልላል፣ በስህተቱም ይቀጥላል።

9. ሰነፎችና ሃይማኖት የለሾች ሰዎች ኃጢአትን ቀላል ነገር አድርገው ይመለከታሉ፤ ሊያዝኑበት ይልቅ ሊያቃልሉት ይመርጣሉ። ሰነፎች በኃጢአት መሥዋዕት ያፌዛሉ፤ ነገር ግን ኃጢአትን ቀላል አድርገው የሚመለከቱ ክርስቶስንም ቀላል አድርገው ይመለከቱታል።

10. የበለጸገውን ኃጢአተኛ የሚያሠቃዩትን የኅሊና ውጋቶች ወይም የሚያቃጥሉ ምኞቶች አናውቅም። እንዲሁም ዓለም በድህነትና በበሽታ ውስጥ እንኳ በቁም ነገር ያለ ክርስቲያን የሚያገኘውን የአእምሮ ሰላም አያውቅም።

11.

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6