መፈለግ
22 ቁጥሮች21አማርኛኤር 29:13
13እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።
1ኛ ዜና 16:11
11እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
2ኛ ዜና 15:2
2አሳንም ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፦ አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል።
ዳዊ 63:1
1አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች፡ እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።
ማቴ 7:7
7“ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።
ዳዊ 37:4
4በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
ዳዊ 105:4
4እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
ዳዊ 34:4
4እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።
ዳዊ 9:10
10ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።
ምሳ 18:22
22ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል።
ዳዊ 119:2
2ምስክሩን የሚፈልጉ፥ በፍጹም ልብ የሚሹት ምስጉኖች ናቸው፤
ሉቃ 19:10
10የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና።”
ዳዊ 34:10
10ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉትን ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም።
አሞ 5:14
14በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ እንዲህም እናንተ እንደ ተናገራችሁ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።
አሞ 5:4
4እግዚአብሔርም ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ “እኔን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤
ኢሳ 55:6
6እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤
ኤፌ 6:10
10በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።
ኢሳ 65:1
1ላልጠየቁኝ ተገለጥሁ፥ ላልፈለጉኝም ተገኘሁ፤ በስሜም ያልተጠራውን ሕዝብ፦ እነሆኝ፥ እነሆኝ፡ አልሁት።
ዳዊ 119:45
45ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና አስፍቼ እሄዳለሁ።
ምሳ 24:14
14ጥበብም ለነፍስህ እንዲሁ እንደሚሆን እወቅ፤ ብታገኘውም ፍጻሜህ መልካም ይሆናል፥ ተስፋህም አይጠፋም።