መተማመን
27 ቁጥሮች24አማርኛኤር 17:7-8
ምሳ 3:5-6
ዳዊ 56:3
3እኔ ግን ፈራሁ በአንተም ታመንሁ።
ምሳ 16:3
3ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች።
ኢሳ 43:2
2በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።
ዳዊ 143:8
8አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።
1ኛ ዮሐ 5:14
14በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።
ዳዊ 91:1-2
ያዕ 1:6
6ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።
ዳዊ 62:7
7መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው።
ዳዊ 121:3
3እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም።
ማቴ 6:26
26ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
ዳዊ 145:18
18እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።
ዳዊ 73:25
25በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ?
ምሳ 29:25
25ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል።
ዕብ 13:6
6ስለዚህ በድፍረት፦ “ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንላለን።
ዕብ 13:5
5አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ “አልለቅህም ከቶም አልተውህም” ብሎአልና፤
ፊል 4:19
19አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል።
ምሳ 16:20
20ቃልን የሚያዳምጥ መልካም ነገርን ያገኛል፤ በእግዚአብሔር የታመነ ምስጉን ነው።
1ኛ ዮሐ 4:16
16እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል፥ አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
ዳዊ 56:4
4በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ፤ በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?
ዳዊ 37:3
3በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።
1ኛ ዮሐ 4:1
1ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።
ዳዊ 31:19
19በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት፡ ለሚፈሩህም የሰወርሃት፥ ቸርነትህ እንደ ምን በዛች!