ትንቢተ ኤርምያስ 29

AMHEVGአማርኛ32 ጥቅሶች6:00 አዳምጥ
አዳምጥ 6:00 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ነቢዩ ኤርምያስ ወደ ተረፉት የምርኮ ሽማግሌዎች፥ ወደ ካህናቱም፥ ወደ ነቢያቱም፥ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃል ይህ ነው።

2ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን እናቱም እቴጌይቱ ጃንደረቦቹም የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች ጠራቢዎችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው።

3ኤርምያስ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን እንዲህ ሲል ላከው፦

4የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ላስማረክኋቸው ምርኮኞች ሁሉ እንዲህ ይላል፦

5ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፥ አታክልትም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ፤

6ተጋቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፥ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ።

7በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።

8የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመካከላችሁ ያሉት ነቢያቶቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፥ እናንተም የምታልሙትን ሕልም አትስሙ።

9በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና፤ እኔም አልላክኋቸውም።

10እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።

11ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።

12እናንተም ትጠሩኛላችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ።

13እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።

14ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ።

15እናንተም፦ እግዚአብሔር በባቢሎን ነቢያትን አስነሥቶልናል፡ ብላችኋልና፤

16እግዚአብሔር በዳዊት ዙፋን ስለ ተቀመጠ ንጉሥ ከእናንተም ጋር ስላልተማረኩት ወንድሞቻችሁ፥ በዚህች ከተማ ስለሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ እንዲህ ይላልና፦

17የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሰይፍንና ራብን ቸነፈርንም እሰድድባቸዋለሁ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉ በለስ አደርጋቸዋለሁ።

18በሰይፍም በራብም በቸነፈርም አሳዳድዳቸዋለሁ፥ ባሳደድሁባቸውም አሕዛብ ሁሉ ዘንድ ለጥላቻና ለመደነቂያ ለማፍዋጫም ለመሰደቢያም እንዲሆኑ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።

19ይህም የሆነው ቃሌን ስላልሰሙ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በማለዳ ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ወደ እነርሱ ሰድጃለሁና፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።

20ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን የሰደድኋችሁ ምርኮኞች ሁሉ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

21የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ስለሚናገሩላችሁ ስለ ቆላያ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ መዕሤያ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፥ በዓይኖቻችሁም ፊት ይገድላቸዋል።

22ከእነርሱም የተነሣ በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ፦ የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደ ጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ እግዚአብሔር ያድርግህ የምትባል እርግማንን ያነሣሉ፤ እኔም አውቃለሁ ምስክርም ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።

23በእስራኤል ዘንድ ስንፍና አድርገዋልና፥ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፥ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና።

24ለኔሔላማዊው ለሸማያ እንዲህ በል፦

25የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህኑም ወደ መዕሤያ ልጅ ወደ ሶፎንያስ፥ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በስምህ እንዲህ ስትል ልከሃል፦

26እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በእግር ግንድና በዛንጅር ታኖረው ዘንድ በእግዚአብሔር ቤት አለቃ እንድትሆን እግዚአብሔር በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።

27አሁንስ ትንቢት ተናጋሪውን የዓናቶቱን ሰው ኤርምያስን ስለ ምን አትዘልፈውም?

28እርሱ፦ ምርኮው የረዘመው ነውና ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፥ አታክልትንም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ፡ ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢሎን ልኮአልና።

29ካህኑም ሶፎንያስ ይህን ደብዳቤ በነቢዩ በኤርምያስ ጆሮ አነበበው።

30የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦

31እግዚአብሔር ስለ ኔሔላማዊው ስለ ሸማያ እንዲህ ይላል ብለህ ወደ ምርኮኞች ሁሉ ላክ፦ እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችኋልና፥ በሐሰትም እንድትታመኑ አድርጎአችኋልና፤

32ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ኔሔላማዊውን ሸማያንና ዘሩን እቀጣለሁ፤ እኔም የማደርግላችሁን መልካምን ነገር የሚያይ ሰው በመካከላችሁ አይኖርላቸውም።

ማብራሪያ

29:1-7

የእግዚአብሔር የተጻፈው ቃል እንደ ተናገረው ቃል ሁሉ በእግዚአብሔር መንፈስ የተነፈሰ እውነተኛ ቃል ነው። የጌታ ቀናተኛ አገልጋይ ሩቅ ላሉት ሰዎች እንደዚሁም ቅርብ ላሉት ሁሉ ጥቅም ለማምጣት ማንኛውንም መንገድ ይጠቀማል። የመጻፍ ጥበብ ለዚህ ዓላማ እጅግ ጠቃሚ ነው። በማተም ጥበብ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል እውቀት ለማሰራጨት እጅግ በጣም ጠቃሚ እንዲሆን ተደርጓል። እግዚአብሔር በዚህ ደብዳቤ ለምርኮኞች መላኩ ምንም እንኳ ቅር ቢሰኘውና ቢቀጣቸውም እንኳ እንዳልተዋቸው ያሳያል። በእግዚአብሔር ፍርሃት ውስጥ ቢኖሩ፣ በባቢሎን በምቾት መኖር ይችላሉ። በየትኛውም የሕይወት ሁኔታ፣ የምንፈልገውን ሁሉ ስለሌለን ብቻ ያለንን ነገር ምቾት አለመጣል ጥበብና ግዴታችን ነው። ምርኮኞች ሆነው የነበሩበትን የአገሪቱን ደህንነት እንዲሹ ታዘዋል። የባቢሎን ንጉሥ ሲጠብቃቸው በነበረበት ጊዜ፣ በእርሱ ሥር በጸጥታና በሰላም፣ በሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራትና በቅንነት መኖር አለባቸው፤ ትዕግሥት አድርገውም፣ በተገቢው ጊዜ መዳናቸውን ለእግዚአብሔር አደራ እንዲሰጡ ተመክረዋል።

29:8-19 ሰዎች በራሳቸው ፈቃድ የመረጧቸውን ነቢያት እንዴት እንደሚጠሩና የራሳቸውን ምኞቶችና ሕልሞች ከእግዚአብሔር የተሰጡ መገለጦች እንደሆኑ አድርገው እንዴት እንደሚቆጥሩ መጠንቀቅ ይገባቸዋል። ሐሰተኛ ነቢያት ሰዎችን በኃጢአታቸው ያሞግሳሉ፤ ምክንያቱም እነዚያ ሰዎች መወደድን ይወዳሉና። ሰዎቹም ለነቢያቶቻቸው በደግነት ይናገራሉ፣ ይህም ነቢያቶቻቸውም ለእነርሱ በደግነት እንዲናገሩላቸው ነው።

እግዚአብሔር ሰባ ዓመታት ከተፈጸሙ በኋላ እንደሚመለሱ ቃል ገብቷል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV This is the text of the letter that the prophet Jeremiah sent from Jerusalem to the surviving elders among the exiles a… English BCV ነቢይ ኤርሚያስ ነቶም ብህይወት ዝነብሩ ሽማግለታትን፥ ነቶም ካህናትን ነቢያትን፥ ንዅሎም ነቶም ናቡከደነፆር ካብ ኢየሩሳሌም ማሪኹ ናብ ባቢሎን ዝወሰዶም ህዝቢ፥ ዝለኣኸሎም ቃል መልእኽቲ እዙ… ትግርኛ GAZBIB Ani Ermiyaas raajichi jaarsolii warra hafanitti luboota, raajota, guutummaa namoota warra Nebukadnezaar Yerusaalemii bo… Afaan Oromoo BCV GIZ ወከመዝ ውእቱ ነገረ መጽሐፍ ዘፈነወ ኤርምያስ ነቢይ እምኢየሩሳሌም ኀበ እለ ተርፉ ረበናት እለ አፍለስዎሙ፤ ወኀበ ካህናት ወኅበ ሐሳውያነ ነቢያት ወኀበ ኵሉ ሕዝብ ዘአፍለሰ ናቡከደነፆር ንጉ… giz GAZGAZ Ani Ermiyaas raajichi jaarsolii warra hafanitti luboota, raajota, guutummaa namoota warra Nebukadnezaar Yerusaalemii bo… Afaan Oromoo BCV aksum ነቢይ ኤርሚያስ ነቶም ብህይወት ዝነብሩ ሽማግለታትን፥ ነቶም ካህናትን ነቢያትን፥ ንዅሎም ነቶም ናቡከደነፆር ካብ ኢየሩሳሌም ማሪኹ ናብ ባቢሎን ዝወሰዶም ህዝቢ፥ ዝለኣኸሎም ቃል መልእኽቲ እዙ… ትግርኛ AMHNIV ነቢዩ ኤርምያስ በምርኮ ተወስደው በሕይወት ለቀሩት ሽማግሌዎች፣ ለካህናቱ፣ ለነቢያቱና ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ለወሰዳቸው ሕዝብ ሁሉ የላከው የደብዳቤ ቃል ይህ ነው፤ አማርኛ SWAHSUV Maneno haya ndiyo maneno ya waraka, ambao nabii Yeremia aliupeleka toka Yerusalemu, kwa hao waliobaki wa wakuu waliochu… Kiswahili