ሀብት
33 ቁጥሮች19አማርኛ1ኛ ሳሙ 2:7-8
ኢዮ 31:24-28
ምሳ 3:9-10
ምሳ 8:8-11
ምሳ 13:11
11በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች።
ምሳ 14:20
20ድሀ በባልንጀራው ዘንድ የተጠላ ነው፡ የባለጠጋ ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው።
ምሳ 15:16
16እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር፡ ሁከት ካለበት ከብዙ መዝገብ ይሻላል።
ምሳ 16:8
8በጽድቅ የሚገኝ ጥቂት ነገር፡ በዓመፅ ከሚገኝ ከብዙ ትርፍ ይሻላል።
ምሳ 18:11
11ለባለጠጋ ሰው ሀብቱ እንደ ጸናች ከተማ ናት፥ በአሳቡም እንደ ረጅም ቅጥር።
ምሳ 19:4
4ባለጠግነት ብዙ ወዳጆች ይጨምራል፤ የድሀ ወዳጅ ግን ከእርሱ ይርቃል።
ምሳ 23:4-5
ምሳ 28:6
6በጠማማ መንገድ ከሚሄድ ባለጠጋ፡ ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል።
ምሳ 28:20
20የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም።
መክ 5:10
10ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፤ ባለጠግነትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።
መክ 7:14
14በመልካም ቀን ደስ ይበልህ፤ በክፉም ቀን ተመልከት፤ ሰው ከእርሱ በኋላ መርምሮ ምንም እንዳያገኝ እግዚአብሔር ይህንም ያንም እንደዚያ ሠርቶአል።
ኤር 17:11
11ያልወለደችውን እንደምታቅፍ ቆቅ፥ እንዲሁ በቅን ሳይሆን ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰው ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፥ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
ማቴ 6:19-21
ሉቃ 6:24-26
1ኛ ጢሞ 6:17
17በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ፥ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።