መጽሐፈ መክብብ 5

AMHEVGአማርኛ20 ጥቅሶች3:26 አዳምጥ
አዳምጥ 3:26 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይበልጣልና፤ እነርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና።

2እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።

3ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል፤ እንዲሁም የሰነፍ ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል።

4ሰነፎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ፤ የተሳልኸውን ፈጽመው።

5ተስለህ የማትፈጽም ብትሆን ባትሳል ይሻላል።

6ሥጋህን በኃጢአት እንዳያስተው ለአፍህ አርነት አትስጥ፥ በመልአክም ፊት፦ “ስሕተት ነበረ፡” አትበል፤ እግዚአብሔር በቃልህ ይቈጣ ዘንድ የእጅህንም ሥራ ያጠፋ ዘንድ ስለምን ትሻለህ?

7ብዙ ሕልም ባለበት ዘንድ፥ እንዲሁም ደግሞ ብዙ ቃል ባለበት ስፍራ በዚያ ብዙ ከንቱ ነገር አለ፤ አንተ ግን እግዚአብሔርን ፍራ።

8ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይመለከታልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በአገሩ ድሆች ሲገፉ፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ባየህ ጊዜ በዚህ ነገር አታድንቅ።

9በጠቅላላው ግን የአገሩ ጥቅም እርሻን የሚወድድ ንጉሥ ቢኖር ነው።

10ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፤ ባለጠግነትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

11ሀብት ሲበዛ የሚበሉት ይበዛሉ፤ ሀብቱን በዓይኑ ብቻ ከማየት በቀር ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል?

12እጅግ ወይም ጥቂት ቢበላ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው የባለጠጋ ጥጋብ ግን እንቅልፍን ይከለክለዋል።

13ከፀሐይ በታች የሚያሳዝን ክፉ ነገር አየሁ፤ ለመከራው በባለቤቱ ዘንድ የተቈጠበች ባለጠግነት ናት።

14ያችም ባለጠግነት በክፉ ነገር ትጠፋለች፤ ልጅንም ቢወልድ በእጁ ምንም የለውም።

15ከእናቱ ሆድ ራቁቱን እንደ ወጣ እንዲሁ እንደ መጣው ይመለሳል፤ ከጥረቱም በእጁ ሊወስድ የሚችለውን ምንም አያገኝም።

16ይህም ደግሞ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ነው፤ እንደ መጣ እንዲሁ ይሄዳል፤ ድካሙም ለነፋስ ከሆነ ጥቅሙ ምንድር ነው?

17ዘመኑን ሁሉ በጨለማ በኀዘን በብስጭት በደዌና በቍጣ ነው።

18እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ እድል ፈንታው ነውና።

19እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።

20እግዚአብሔር በልቡ ደስታን ስለ ሰጠው እርሱ የሕይወቱን ዘመን እጅግ አያስብም።

ማብራሪያ

5:1-3 ራስህን ወደ እግዚአብሔር አምልኮ አቅና፤ ለዚህም ራስህን ለማዘጋጀት ጊዜ ውሰድ። ሐሳቦችህ ከመንከራተትና ከመባዘን ጠብቅ፤ ፍላጎቶችህም ወደ ተሳሳቱ ነገሮች እንዳይሳቡ ተጠንቀቅ። ከንቱ ድግግሞሾችን ልንርቅ ይገባል። ብዙ ጸሎቶች እዚህ አይወገዙም፣ ነገር ግን ትርጉም የሌላቸው ናቸው። ምን ያህል ጊዜ የሚንከራተቱ ሐሳቦቻችን በመለኮታዊ ሥርዓቶች ላይ የምናደርገውን ተሳትፎ ከሰነፎች መሥዋዕትነት እምብዛም አይሻልም። በጸሎት ውስጥ የሚነገሩ ብዙና የተጣደፉ ቃላት በልብ ውስጥ ያለውን ሞኝነት፣ ስለ እግዚአብሔር ያለንን ዝቅተኛ ሐሳብ፣ እንዲሁም ስለ ነፍሶቻችንም ያለንን ግድ የለሽነት ያሳያሉ።

5:4-8 አንድ ሰው በችኮላ ቃልኪዳን ሲያደርግ፣ አፉ ለሥጋው ኃጢአት ምክንያት ሆነ። ይህ ሁኔታ የሚያመለክተው አንድ ሰው ወደ ካህን ቀርቦ፣ ቃልኪዳኑን በችኮላ እንደፈጸመውና እሱን መፈጸም ስህተት እንደሆነ በማስመሰል ነበር። እንዲህ ያለው እግዚአብሔርን ማሾፍ፣ የእግዚአብሔርን ቁጣ ያስከትል ነበር፤ ይህም ባልተገባ መንገድ የያዘውን ሁሉ ሊያጠፋው ይችላል። የሰውን ፍርሃት መግታት አለብን። እግዚአብሔርን ከፊትህ አስቀድም። ያንጊዜም የድሆችን ጭቆና ባየህ ጊዜ፣ መለኮታዊውን አሳቢነት አትነቅፍም። ዓላማዎቹ በዚህ መንገድ ሲዛቡ ባየህ ጊዜም፣ የአስተዳደር ሥርዓትን አታጣጥልም፤ ሰዎችን ከበደል ለመጠበቅ እንደማይችል ስታይም ሃይማኖትን አትነቅፍም። ጨቋኞች ደኅንነት ያላቸው ቢመስሉም፣ እግዚአብሔር ግን ሁሉንም ይጠይቃል።

5:9-17 የእግዚአብሔር አቅርቦት መልካምነት በግዴለሽነት ለሚያይ ሰው ከሚታየው በላይ በተመጣጣኝ ሁኔታ የተከፋፈለ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Guard your steps when you go to the house of God. Go near to listen rather than to offer the sacrifice of fools, who do… English BCV ናብ ቤት እግዚኣብሄር እንትትኣቱ እግርኻ ሓሉ፤ ክፉእ ከም ዝገብሩ ኣይፈልጡን እዮምሞ ኻብ መስዋእቲ ሰነፋት፥ ክትሰምዕ ምቕራብ ይሐይሽ። ትግርኛ GAZBIB Mana Waaqayyootti yommuu ol lixxu miilla kee eeggadhu! Dhaga'uudhaaf ol lixi! Dhaga'uun aarsaa isa warri gowwoonni dhi'… Afaan Oromoo BCV GIZ ዕቀብ እገሪከ ሶበ ተሐውር ኀበ እግዚአብሔር ወቅረብ ለሰሚዕ እምነ ሀብቶሙ ለአብዳን መሥዋዕተከ እስመ ኢኮኑ ማእምራነ ለገቢረ ሠናይ። giz GAZGAZ Mana Waaqayyootti yommuu ol lixxu miilla kee eeggadhu! Dhaga'uudhaaf ol lixi! Dhaga'uun aarsaa isa warri gowwoonni dhi'… Afaan Oromoo BCV aksum ናብ ቤት እግዚኣብሄር እንትትኣቱ እግርኻ ሓሉ፤ ክፉእ ከም ዝገብሩ ኣይፈልጡን እዮምሞ ኻብ መስዋእቲ ሰነፋት፥ ክትሰምዕ ምቕራብ ይሐይሽ። ትግርኛ AMHNIV ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትሄድ እግርህን ጠብቅ። ለመስማት መቅረብ የሰነፎችን መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤ እነርሱ ክፉ እንደሚሠሩ አያውቁምና። አማርኛ SWAHSUV Jitunze mguu wako uendapo nyumbani kwa Mungu; Maana ni heri kukaribia ili usikie, Kuliko kutoa kafara ya wapumbavu; Amb… Kiswahili