ሀብት
48 ቁጥሮች19አማርኛዘዳ 31:20
20ለአባቶቻቸው ወደ ማልሁላቸው፥ ወተትና ማር ወደ ምታፈስሰው ምድር ካገባኋቸው በኋላ፥ ከበሉም ከጠገቡም ከደነደኑም በኋላ፥ ሌሎችን አማልክት ተከትለው ያመልካሉ፥ እኔንም ይንቃሉ፥ ቃል ኪዳኔንም ያፈርሳሉ።
1ኛ ሳሙ 2:7
7እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ዳዊ 37:16
16ለጻድቅ ያለው ጥቂት፡ ከብዙ ከኃጢአተኞች ሀብት ይበልጣል።
ዳዊ 52:1-7
1ኃያል ሆይ፥ በክፋት ለምን ትጓደዳለህ? ሁልጊዜስ በመተላለፍ?
2አንደበትህ ኃጢአትን ያስባል፤ እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግህ።
3ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዓመፃን ወደድህ።
4የሚያጠፉ ቃልን ሁሉ፥ የሽንገላ ምላስን ወደድህ።
5ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ያፈርስሃል፤ ከቤትህም ይነቅልሃል ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
6ጻድቃን አይተው ይፈራሉ፤ በእርሱም ይሥቃሉ እንዲህም ይላሉ፦
7“እግዚአብሔርን ረዳቱ ያላደረገ፥ በባለጠግነቱም ብዛት የታመነ፥ በከንቱ ነገርም የበረታ ያ ሰው እነሆ።”
ዳዊ 73:3-22
3የኃጢአተኞችን ሰላም አይቼ፡ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
4ለሞታቸው መጣጣር የለውምና፤ ኃይላቸውም ጠንካራ ነውና።
5እንደ ሰው በድካም አልሆኑም፥ ከሰው ጋርም አልተገረፉም።
6ስለዚህ ትዕቢት ያዛቸው፤ ኃጢአትንና በደልን ተጐናጸፉአት።
7ዓይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ፤ ልባቸውም ከምኞታቸው ይልቅ አገኘ።
8አስበው ክፉ ነገርን ተናገሩ፤ ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ።
9አፋቸውን በሰማይ አኖሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ።
10ስለዚህ ሕዝቤ ወደዚህ ይመለሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላያቸው ይገኛል፤
11“እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለ?” ይላሉ።
12እነሆ፥ እነዚህ ኃጢአተኞች ይደሰታሉ፥ ሁልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያበዛሉ።
13እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።
14ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው።
15እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር።
16አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ።
17ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥ ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ።
18በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፥ ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው።
19እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ ስለ ኃጢአታቸውም ጠፉ።
20ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ ምልክታቸውን ታስነውራለህ።
21ልቤ ነድዶአልና፥ ኵላሊቴም ቀልጦአልና፤
22እኔ የተናቅሁ ነኝ አላውቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
ምሳ 10:2
2በኃጢአት የተገኘ መዝገብ ጥቅም የለውም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል።
ምሳ 10:22
22የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርስዋ ጋር አይጨምርም።
ምሳ 11:28
28በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፡ ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ።
ምሳ 13:7-8
ምሳ 14:24
24የጠቢባን ዘውድ ባለጠግነታቸው ነው፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ስንፍና ነው።
ምሳ 16:8
8በጽድቅ የሚገኝ ጥቂት ነገር፡ በዓመፅ ከሚገኝ ከብዙ ትርፍ ይሻላል።
ምሳ 18:23
23ድሀ በትሕትና እየለመነ ይናገራል፤ ባለጠጋ ግን በድፍረት ይመልሳል።
ምሳ 21:6
6በሐሰተኛ ምላስ መዝገብ ማከማቸት የሚበንን ጉም ነው፤ ይህን የሚፈልጉ ሞትን ይፈልጋሉ።
ምሳ 23:4-5
ምሳ 27:23-24
ምሳ 28:8
8በአራጣ ብዛትና በቅሚያ ሀብቱን የሚያበዛ፡ ለድሀ ለሚራራ ያከማችለታል።
ምሳ 28:11
11ባለጠጋ ሰው ለራሱ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል፤ አስተዋይ ድሀ ግን ይመረምረዋል።
ምሳ 28:20
20የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም።