ትንቢተ አሞጽ 7

AMHEVGአማርኛ16 ጥቅሶች2:42 አዳምጥ
አዳምጥ 2:42 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ የኋለኛው ሣር በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፤ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ የበቀለ የገቦ ነበረ።

2የምድሩንም ሣር በልተው ከጨረሱ በኋላ፥ እኔ፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ታናሽ ነውና እንዴት ይቆማል?” አልሁ።

3እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ ይህ አይሆንም፥ ይላል እግዚአብሔር።

4ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ፤ እርስዋም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች።

5እኔም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንድትተው እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ታናሽ ነውና እንዴት ይቆማል?” አልሁ።

6እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ ይህ ደግሞ አይሆንም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

7እንዲህም አሳየኝ፤ እነሆም፥ ጌታ ቱንቢውን ይዞ በቱንቢ በተሠራ ቅጥር ላይ ቆሞ ነበር።

8እግዚአብሔርም፦ “አሞጽ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው?” አለኝ። እኔም፦ “ቱንቢ ነው፡” አልሁ። ጌታም፦ “እነሆ፥ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱንቢ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ደግሞ አላልፋቸውም፤

9የይስሐቅም የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፥ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ፡” አለ።

10የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም ልኮ፦ “አሞጽ፦ ‘ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፥ እስራኤልም ከአገሩ ተማርኮ ይሄዳል፡’ ብሎአልና አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል ዐምፆብሃል፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም፡” አለ።

12አሜስያስም አሞጽን፦ “ባለ ራእዩ ሆይ፥ ሂድ ወደ ይሁዳም ምድር ሽሽ፥ በዚያም እንጀራን ብላ፥

13በዚያም ትንቢትን ተናገር፤ ነገር ግን ቤቴል የንጉሥ መቅደስና የመንግሥት ቤት ናትና ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትንቢት አትናገር፡” አለው።

14አሞጽም መልሶ አሜስያስን አለው፦ “እኔ ላም ጠባቂና ወርካ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤

15እግዚአብሔርም በጎቹን ከመከተል ወሰደኝ፥ እግዚአብሔርም፦ ሂድ፥ ለሕዝቤም ለእስራኤል ትንቢት ተናገር፡” አለኝ።

16አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ አንተ፦ “በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ፡” ብለሃል፤

17ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፥ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።”

ማብራሪያ

7:1-9

እግዚአብሔር ለረጅም ጊዜ ይታገሳል፣ ነገር ግን የሚያስቆጣን ሕዝብ ለዘላለም አይታገስም። ቀደም ሲል የተቀበልናቸውን ምሕረቶች ማስታወስ፣ ልክ እንደ መጀመሪያው የምድር ፍሬ፣ በኋለኛው የምርት ወቅት ብስጭት ሲያጋጥመን ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንድንገዛ ሊያደርገን ይገባል። ጌታ ኃጢአተኛን ሕዝብ የሚያዋርድባቸው ብዙ መንገዶች አሉት። በየትኛውም ችግር ውስጥ ብንሆን፣ ኃጢአት ይቅር እንዲለን ወደ እግዚአብሔር በእጅጉ ልንተጋ ይገባል። ኃጢአት ብዙም ሳይቆይ ታላቅ ሕዝብን ጥቂት ያደርጋል። ሊያነሳው የሚገባው እጅ በእርሱ ላይ ቢዘረጋ ለእስራኤል ምን ይሆን? የጸሎትን ኃይል ተመልከቱ። የሚጸልዩ ሰዎች ለአገር ምን ያህል በረከት እንደሆኑ ተመልከቱ። እግዚአብሔር ምሕረትን ለማሳየት ምን ያህል ፈጣንና ዝግጁ እንደሆነ፣ ጸጋን ለመስጠት እንዴት እንደሚጠብቅ ተመልከቱ። እስራኤል እግዚአብሔር ራሱ ለመቅደሱ መጠበቂያ አድርጎ የገነባው ጠንካራ ግንብ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV This is what the Sovereign Lord showed me: He was preparing swarms of locusts after the king's share had been harvested… English BCV እግዚኣብሄር ኣምላኽ፥ ነዙይ ኣርኣየኒ፦ እንሆ እቲ ዳሕረዋይ ናይ ንጉስ ዝኾነ ሳዕሪ ምስ ተዓፅደ፥ ገና ምጭላድ ክጅምር እንተሎ፥ እግዚኣብሄር ኣንበጣ ፈጠረ፤ እንሆ ድሕሪ ዓፂድ እቲ ንጉስ ዝ… ትግርኛ GAZBIB Wanta Waaqayyo gooftaan mul'ataan anatti argisiise isinitti himuufan jira. Kunoo! Marga isa duraa mootichaaf erga haama… Afaan Oromoo BCV GIZ እስመ ከመዝ አርአየኒ እግዚአብሔር፤ ወናሁ ይመጽእ አንበጣ በጽባሕ ወአሐዱ ደጎብያ ጎግ ንጉሥ። giz GAZGAZ Wanta Waaqayyo gooftaan mul'ataan anatti argisiise isinitti himuufan jira. Kunoo! Marga isa duraa mootichaaf erga haama… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ኣምላኽ፥ ነዙይ ኣርኣየኒ፦ እንሆ እቲ ዳሕረዋይ ናይ ንጉስ ዝኾነ ሳዕሪ ምስ ተዓፅደ፥ ገና ምጭላድ ክጅምር እንተሎ፥ እግዚኣብሄር ኣንበጣ ፈጠረ፤ እንሆ ድሕሪ ዓፂድ እቲ ንጉስ ዝ… ትግርኛ AMHNIV ጌታ እግዚአብሔር ይህን አሳየኝ፤ የንጉሡ የመከር እህል ከተሰበሰበ በኋላ ገቦው መብቀል በጀመረ ጊዜ፣ እርሱ የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ። አማርኛ SWAHSUV Haya ndiyo aliyonionyesha Bwana MUNGU; tazama, aliumba nzige mwanzo wa kuchipuka kwake mimea wakati wa vuli; na tazama,… Kiswahili