ትንቢተ አሞጽ 7

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:17 አዳምጥ
አዳምጥ 3:17 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጌታ እግዚአብሔር ይህን አሳየኝ፤ የንጉሡ የመከር እህል ከተሰበሰበ በኋላ ገቦው መብቀል በጀመረ ጊዜ፣ እርሱ የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ።

2አንበጦች የምድሩን ሣር ግጠው ከጨረሱት በኋላ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋመው ይችላል? ታናሽ ነው እኮ!” አልሁ።

3እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ እግዚአብሔርም ይህ አይፈጸምም አለ።

4ጌታ እግዚአብሔር ይህንም አሳየኝ፤ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ሊፈርድ ተዘጋጀ፤ እሳቱም ታላቁን ጥልቅ አደረቀ፤ ምድሪቱንም በላ።

5ከዚያም በኋላ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንድትተወው እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋመው ይችላል? ታናሽ ነው እኮ!” አልሁ።

6እግዚአብሔር ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ ጌታ እግዚአብሔር፣ “ይህም ደግሞ አይፈጸምም” አለ።

7ይህንም ደግሞ አሳየኝ፤ ጌታ በእጁ ቱንቢ ይዞ በቱንቢ በተሠራ ቅጥር አጠገብ ቆሞ ነበር።

8እግዚአብሔር፣ “አሞጽ፣ የምታየው ምንድ ነው?” አለኝ። እኔም፣ “ቱምቢ” አልሁ። ጌታም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱምቢ እዘረጋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ አልምራቸውም።

9“የይስሐቅ ማምለኪያ ኮረብታዎች ባድማ ይሆናሉ፤ የእስራኤል መቅደሶች ይፈርሳሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፌ እነሣለሁ።”

10ከዚህ በኋላ የቤቴል ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሤረ ነው፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም፤

11አሞጽ እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበርና፤ “ ‘ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፤ እስራኤልም በእርግጥ ከትውልድ አገሩ ተማርኮ ይሄዳል።”

12አሜስያስም፣ አሞጽን እንዲህ አለው፤ “አንተ ባለ ራእይ ከዚህ ሂድ! ከይሁዳ ምድር ሽሽ፤ እዚያም እንጀራህን ብላ፤ በዚያም ትንቢት ተናገር።

13ከእንግዲህ ወዲያ ግን በቤቴል ትንቢት አትናገር፤ የንጉሡ መቅደስ፣ የመንግሥቱም መኖሪያ ነውና።”

14አሞጽም ለአሜስያስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ እረኛና የባሉጥ ፍሬ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤

15እግዚአብሔር ግን የበግ መንጋ ከምጠብቅበት ቦታ ወስዶ፣ ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ፤

16እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። አንተ፣ “ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤ በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ’ ትላለህ።

17“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤” ‘ሚስትህ በከተማዪቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም እየተለካ ይከፋፈላል፤ አንተ ራስህ በረከሰ ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከትውልድ አገሩ፣ ተማርኮ ይሄዳል።’ ”

ማብራሪያ

7:1-9

እግዚአብሔር ለረጅም ጊዜ ይታገሳል፣ ነገር ግን የሚያስቆጣን ሕዝብ ለዘላለም አይታገስም። ቀደም ሲል የተቀበልናቸውን ምሕረቶች ማስታወስ፣ ልክ እንደ መጀመሪያው የምድር ፍሬ፣ በኋለኛው የምርት ወቅት ብስጭት ሲያጋጥመን ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንድንገዛ ሊያደርገን ይገባል። ጌታ ኃጢአተኛን ሕዝብ የሚያዋርድባቸው ብዙ መንገዶች አሉት። በየትኛውም ችግር ውስጥ ብንሆን፣ ኃጢአት ይቅር እንዲለን ወደ እግዚአብሔር በእጅጉ ልንተጋ ይገባል። ኃጢአት ብዙም ሳይቆይ ታላቅ ሕዝብን ጥቂት ያደርጋል። ሊያነሳው የሚገባው እጅ በእርሱ ላይ ቢዘረጋ ለእስራኤል ምን ይሆን? የጸሎትን ኃይል ተመልከቱ። የሚጸልዩ ሰዎች ለአገር ምን ያህል በረከት እንደሆኑ ተመልከቱ። እግዚአብሔር ምሕረትን ለማሳየት ምን ያህል ፈጣንና ዝግጁ እንደሆነ፣ ጸጋን ለመስጠት እንዴት እንደሚጠብቅ ተመልከቱ። እስራኤል እግዚአብሔር ራሱ ለመቅደሱ መጠበቂያ አድርጎ የገነባው ጠንካራ ግንብ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ የኋለኛው ሣር በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፤ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ የበቀለ የገቦ ነበረ። አማርኛ ENGNIV This is what the Sovereign Lord showed me: He was preparing swarms of locusts after the king's share had been harvested… English BCV እግዚኣብሄር ኣምላኽ፥ ነዙይ ኣርኣየኒ፦ እንሆ እቲ ዳሕረዋይ ናይ ንጉስ ዝኾነ ሳዕሪ ምስ ተዓፅደ፥ ገና ምጭላድ ክጅምር እንተሎ፥ እግዚኣብሄር ኣንበጣ ፈጠረ፤ እንሆ ድሕሪ ዓፂድ እቲ ንጉስ ዝ… ትግርኛ GAZBIB Wanta Waaqayyo gooftaan mul'ataan anatti argisiise isinitti himuufan jira. Kunoo! Marga isa duraa mootichaaf erga haama… Afaan Oromoo BCV GIZ እስመ ከመዝ አርአየኒ እግዚአብሔር፤ ወናሁ ይመጽእ አንበጣ በጽባሕ ወአሐዱ ደጎብያ ጎግ ንጉሥ። giz GAZGAZ Wanta Waaqayyo gooftaan mul'ataan anatti argisiise isinitti himuufan jira. Kunoo! Marga isa duraa mootichaaf erga haama… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ኣምላኽ፥ ነዙይ ኣርኣየኒ፦ እንሆ እቲ ዳሕረዋይ ናይ ንጉስ ዝኾነ ሳዕሪ ምስ ተዓፅደ፥ ገና ምጭላድ ክጅምር እንተሎ፥ እግዚኣብሄር ኣንበጣ ፈጠረ፤ እንሆ ድሕሪ ዓፂድ እቲ ንጉስ ዝ… ትግርኛ SWAHSUV Haya ndiyo aliyonionyesha Bwana MUNGU; tazama, aliumba nzige mwanzo wa kuchipuka kwake mimea wakati wa vuli; na tazama,… Kiswahili