ትንቢተ አሞጽ 6

AMHEVGአማርኛ13 ጥቅሶች2:35 አዳምጥ
አዳምጥ 2:35 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በጽዮን ላሉ ዓለመኞች፥ በሰማርያም ተራራ ላይ ተዘልለው ለተቀመጡ፥ የእስራኤልም ቤት ወደ እነርሱ ለመጡባቸው ለአሕዛብ አለቆች ወዮላቸው!

2ወደ ካልኔ አልፋችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን?

3ክፉውን ቀን ከእናንተ ለምታርቁ፥ የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ፥

4ከዝሆን ጥርስ በተሠራ አልጋ ላይ ለምትተኙ፥ በምንጣፋችሁም ላይ ተደላድላችሁ ለምትቀመጡ፥ ከበጎችም መንጋ ጠቦትን ከጋጥም ውስጥ ጥጃን ለምትበሉ፥

5በመሰንቆም ድምፅ ለምትንጫጩ፥ እንደ ዳዊትም የዜማን ዕቃ ለምታዘጋጁ፥

6በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፥ እጅግ ባማረ ሽቱም ለምትቀቡ፥ ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ለእናንተ ወዮላችሁ!

7ስለዚህ በምርኮ መጀመሪያ ይማረካሉ፥ ተደላድለው ከተቀመጡትም ዘንድ ዘፈን ይርቃል።

8ጌታ እግዚአብሔር፦ “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ አዳራሾቹንም ጠልቻለሁ፤ ስለዚህ ከተማይቱንና የሚኖሩባትን ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ፡ ብሎ በራሱ ምሎአል፥” ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር።

9እንዲህም ይሆናል፤ አሥር ሰዎች በአንድ ቤት ውስጥ ቢቀሩ እነርሱ ይሞታሉ።

10አጥንቱንም ከቤቱ ያወጡ ዘንድ የሰው ዘመድና አቃጣዩ ባነሡት ጊዜ፥ በቤቱም ውስጥ ያለውን፦ “እስከ አሁን ድረስ ገና ሰው በአንተ ዘንድ አለን?” ባለው ጊዜ፥ እርሱም፦ “ማንም የለም፡” ባለ ጊዜ፤ ያን ጊዜ፦ “የእግዚአብሔርን ስም እንጠራ ዘንድ አይገባንምና ዝም በል፡” ይለዋል።

11እነሆም፥ እግዚአብሔር ያዝዛል፤ ታላቁንም ቤት በማፍረስ፥ ታናሹንም ቤት በመሰባበር ይመታል።

12ፍርድን ወደ ሐሞት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ እሬት የለወጣችሁ፥ በከንቱም ነገር ደስ የሚላችሁ፦ “በኃይላችን ቀንድ የወሰድን አይደለምን?” የምትሉ፥ እናንተ ሆይ፥ በውኑ ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይጋልባሉን? ወይስ በሬዎች በዚያ ላይ ያርሳሉን?

14የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ ሕዝብን አስነሣባችኋለሁ፥ ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር፤ እነርሱም ከሐማት መግቢያ ጀምረው እስከ ዓረባ ወንዝ ድረስ ያስጨንቋችኋል።

ማብራሪያ

6:1-7 ለሥጋቸው ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጡ ሰዎች ለራሳቸው መልካም የሚያደርጉ ይመስላሉ፤ ነገር ግን በዚህ ክፍል ውስጥ ምቾታቸው ምን እንደሆነና ወዮላቸውም ምን እንደሆነ ተገልጾልናል። እዚህ ላይ እግዚአብሔር የሚጠይቅባቸውን ትዕቢት፣ መዘናጋትና ሥጋዊ ምኞት ገለጻ ቀርቦአል። ቸልተኛ ኃጢአተኞች በየትኛውም ስፍራ በአደጋ ውስጥ ናቸው፤ ነገር ግን በጽዮን ውስጥ ያሉት፣ የደነዘዙት፣ በከንቱ የሚተማመኑትና መብቶቻቸውን አላግባብ የሚጠቀሙት እጅግ በከፋ አደጋ ውስጥ ናቸው። ሆኖም በኃጢአት ውስጥ የሚኖሩና ከዓለም ጋር የሚስማሙ ብዙዎች ራሳቸውን የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Woe to you who are complacent in Zion, and to you who feel secure on Mount Samaria, you notable men of the foremost nat… English BCV እቶም ኣብ ፅዮን ሃዲኦም ዝቕመጡ፥ ኣብ እምባ ሰማርያ ድማ ተኣማሚኖም ዝነብሩ ቤት እስራኤል፥ ናብኣቶም ዝመፁዎም፥ መራሕቲ ኣህዛብ ወይለኦም! ትግርኛ GAZBIB Isin gurguddoonni saba isa saba warra kaan irra caalu, warri namoonni Israa'el gorsaaf gara keessan dhufanii, isin Xiyo… Afaan Oromoo BCV GIZ አሌ ሎሙ ለእለ ይሜንንዋ ለጽዮን ወለእለ ይትአመኑ በደብረ ሰማርያ ይቅስምዎሙ መላእክተ አሕዛብ። giz GAZGAZ Isin gurguddoonni saba isa saba warra kaan irra caalu, warri namoonni Israa'el gorsaaf gara keessan dhufanii, isin Xiyo… Afaan Oromoo BCV aksum እቶም ኣብ ፅዮን ሃዲኦም ዝቕመጡ፥ ኣብ እምባ ሰማርያ ድማ ተኣማሚኖም ዝነብሩ ቤት እስራኤል፥ ናብኣቶም ዝመፁዎም፥ መራሕቲ ኣህዛብ ወይለኦም! ትግርኛ AMHNIV በጽዮን ተዘልላችሁ የምትቀመጡ፣ በሰማርያ ተራራ ያለ ሥጋት የምትኖሩ፣ የእስራኤልም ሕዝብ ለርዳታ ወደ እናንተ የሚመጡባችሁ፣ እናንት የአሕዛብ አለቆች ሆይ፤ ወዮላችሁ! አማርኛ SWAHSUV Ole wao wanaostarehe katika Sayuni, na hao wanaokaa salama katika mlima wa Samaria, watu mashuhuri wa taifa lililo la k… Kiswahili