ትንቢተ አሞጽ 1

AMHEVGአማርኛ15 ጥቅሶች2:51 አዳምጥ
አዳምጥ 2:51 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በቴቁሔ ከላም ጠባቂዎች መካከል የነበረ አሞጽ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከሆነበቱ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየው ቃል ይህ ነው።

2እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ የእረኞችም ማሰማርያዎች ያለቅሳሉ፥ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።”

3እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ገለዓድን በብረት መንኰራኵር አሂዶአልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የደማስቆ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

4በአዛሄል ቤት እሳትን እሰድዳለሁ፥ የወልደ አዴርንም አዳራሾች ትበላለች።

5የደማስቆንም መወርወሪያ እሰብራለሁ፥ ተቀማጮችንም ከአዌን ሸለቆ አጠፋለሁ፥ በትር የያዘውንም ከዔደን ቤት አጠፋለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ወደ ቂር ይማረካል፥” ይላል እግዚአብሔር።

6እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለኤዶምያስ አሳልፈው ይሰጡአቸው ዘንድ ምርኮኞችን ሁሉ ማርከዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጋዛ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

7በጋዛ ቅጥር ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ አዳራሾችዋንም ትበላለች።

8“ተቀማጮችን ከአዛጦን አጠፋለሁ፥ በትር የያዘውንም ከአስቀሎና አጠፋለሁ፤ እጄንም በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ ከፍልስጥኤማውያንም የቀሩት ይጠፋሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

9እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ምርኮኞችን ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው ሰጥተዋልና፥ የወንድሞችንም ቃል ኪዳን አላሰቡምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢሮስ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

10በጢሮስ ቅጥር ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ አዳራሾችዋንም ትበላለች።”

11እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ ርኅራኄንም ሁሉ ጥሎአልና፥ ቍጣውም ሁልጊዜ ቀድዶአልና፥ መዓቱንም ለዘላለም ጠብቆአልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤዶምያስ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

12በቴማን ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የባሶራንም አዳራሾች ትበላለች።”

13እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዳርቻቸውን ያሰፉ ዘንድ የገለዓድን እርጕዞች ቀድደዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የአሞን ልጆች ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

14በረባት ቅጥር ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ በሰልፍም ቀን በጩኸት በዐውሎ ነፋስም ቀን በሁከት አዳራሾችዋን ትበላለች፤

15ንጉሣቸውም ከአለቆቹ ጋር በአንድነት ይማረካል፥” ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

፩፥፲፰-፳፩ ብዙ መለኮታዊ ተጽዕኖዎች ይኖራሉ፤ ወንጌልም በፍጥነት እስከ ምድር ዳርቻዎች ድረስ ይሰራጫል። እነዚህ ክስተቶች በጠቃሚ ምልክቶች ስር ተተንብየዋል፤ ሁሉ የተሳሳተ ነገር የሚስተካከልበት ቀን ይመጣል። የዚህ ብዛት ምንጭ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው፣ ዥረቶቹም ከዚያ ይፈስሳሉ። ክርስቶስ ይህ ምንጭ ነው፤ መከራው፣ ጽድቁ፣ እና ጸጋው ያጠራሉ፣ ያድሳሉ፣ እና ፍሬያማ ያደርጋሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The words of Amos, one of the shepherds of Tekoa–what he saw concerning Israel two years before the earthquake, when Uz… English BCV እዝ ቓል እዙይ፥ ኣሞፅ፥ ሓደ ኻብቶም ጓሶት ቴቁሔ ዝነበረ፥ ብዘመን ኣዛርያስ ንጉስ ይሁዳን፥ ብዘመን ኢዮርብዓም ወዲ ኢዮኣስ ንጉስ እስራኤልን፥ ክልተ ዓመት ቅድሚ ምንቅጥቃጥ ምድርን፥ ብዛዕ… ትግርኛ GAZBIB Kun dubbii Amos, inni warra mandara Teqo'aa keessatti hoolota horsiisan keessaa tokko ture dubbatee dha; inni bara biyy… Afaan Oromoo BCV GIZ ቃለ እግዚአብሔር ኀበ አሞጽ ዘኮነ በአቃሬም ዘቴቁሔ ዘርእየ በእንተ ኢየሩሳሌም በመዋዕለ ዖዝያን ንጉሠ ይሁዳ ወበመዋዕለ ኢያሮብዓም ወልደ ዮአስ ንጉሠ እስራኤል እምቅድመ ክልኤቱ ዓመት ዘድል… giz GAZGAZ Kun dubbii Amos, inni warra mandara Teqo'aa keessatti hoolota horsiisan keessaa tokko ture dubbatee dha; inni bara biyy… Afaan Oromoo BCV aksum እዝ ቓል እዙይ፥ ኣሞፅ፥ ሓደ ኻብቶም ጓሶት ቴቁሔ ዝነበረ፥ ብዘመን ኣዛርያስ ንጉስ ይሁዳን፥ ብዘመን ኢዮርብዓም ወዲ ኢዮኣስ ንጉስ እስራኤልን፥ ክልተ ዓመት ቅድሚ ምንቅጥቃጥ ምድርን፥ ብዛዕ… ትግርኛ AMHNIV በቴቁሔ ከነበሩት እረኞች መካከል አንዱ የሆነው አሞጽ፣ ዖዝያን የይሁዳ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንዲሁም የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረ ጊዜ፣ ይኸውም የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከ… አማርኛ SWAHSUV Maneno ya Amosi, aliyekuwa mmoja wa wachungaji wa Tekoa; maono aliyoyaona katika habari za Israeli, siku za Uzia, mfalm… Kiswahili