ትንቢተ ኢሳይያስ 43

AMHEVGአማርኛ26 ጥቅሶች4:22 አዳምጥ
አዳምጥ 4:22 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።

2በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።

3እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብፅን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።

4በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ።

5እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፥ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።

6ሰሜንን፦ መልሰህ አምጣ፥ ደቡብንም፦ አትከልክል፤ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፥ በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ፡ እለዋለሁ።

8ዓይኖች ያሉአቸውን ዕውሮችን ሕዝብ፥ ጆሮችም ያሉአቸውን ደንቆሮቹን አውጣ።

9አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ ወገኖችም ይከማቹ፤ ከመካከላቸው፤ ይህን የሚናገር፥ የቀድሞውንስ ነገር የሚያሳየን ማን ነው? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፥ ሰምተውም፦ እውነት ነው፡ ይበሉ።

10ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም።

11እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።

12ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ አሳይቼማለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፤ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እኔም አምላክ ነኝ።

13ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፥ የሚከለክልስ ማን ነው?

14የእስራኤል ቅዱስ፥ የሚቤዣችሁ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፥ ከለዳውያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ።

15ቅዱሳችሁ፥ የእስራኤል ፈጣሪ፥ ንጉሣችሁ፥ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።

16እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛም ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ያደርጋል፤

17እግዚአብሔር ሰረገላውንና ፈረሱን ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል፤ እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፥ አይነሡም፤ ቀርተዋል፥ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

18የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ፥ የጥንቱንም ነገር አታስቡ።

19እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለህ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ እናንተም አታውቁትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ።

20ምስጋናዬን እንዲናገሩ ለእኔ የፈጠርሁት ሕዝብ፥ የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረ በዳ ውኃን በበረሀም ወንዞችን ሰጥቻለሁና የምድረ በዳ አራዊት፥ ቀበሮችና ሰጎኖች፥ ያከብሩኛል።

22ያዕቆብ ሆይ፥ አንተ ግን አልጠራኸኝም፥ አንተም እስራኤል ሆይ፥ በእኔ ዘንድ ደክመሃል።

23ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎችህን አላቀረብህልኝም በሌላም መሥዋዕትህ አላከበርኸኝም፤ በእህልም ቍርባን አላስቸገርሁህም በዕጣንም አላደከምሁህም።

24ዕጣንም በገንዘብ አልገዛህልኝም በመሥዋዕትህም ስብ አላጠገብኸኝም፤ ነገር ግን በኃጢአትህ አስቸገርኸኝ፥ በበደልህም አደከምኸኝ።

25መተላለፍህን፦ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ፤ ኃጢአትህንም አላስብም።

26አሳስበኝ፥ በአንድነትም ሆነን እንፋረድ፤ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር።

27ፊተኛው አባትህ ኃጢአት ሠርቶአል፥ መምህሮችህም በድለውኛል።

28ስለዚህ የመቅደሱን አለቆች አረከስሁ፥ ያዕቆብንም እርግማን፥ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ።

ማብራሪያ

43:1-7 የእግዚአብሔር ሞገስና በጎ ፈቃድ ለሕዝቡ ለሁሉም አማኞች እጅግ ብዙ መጽናናትን ይናገራል። አዲሱ ፍጥረት የትም ቢሆን፣ የእግዚአብሔር አሠራር ነው። በልጁ ደም የተቤዠጉት ሁሉ፣ እርሱ ለራሱ ለይቷቸዋል። እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የሆነላቸው፣ ማን ወይም ምን ሊቃወማቸው ቢችልም መፍራት የለባቸውም። ግብፅና ኢትዮጵያ፣ ሕይወታቸውና ሀብታቸው ሁሉ፣ ከክርስቶስ ደም ጋር ሲወዳደሩ ምንድናቸው? እውነተኛ አማኞች በእግዚአብሔር ፊት የከበሩ ናቸው፤ እርሱም ከየትኛውም ሕዝብ በላይ በእነርሱ ላይ ደስታው ነው። በእሳትና በውሃ ውስጥ እንዳለፉ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እስከሆነ ድረስ ምንም ክፉ ነገር አይፈሩም፤ ይደገፋሉ እንዲሁም ይወጣሉ። ታማኞቹ ይበረታታሉ። ከየአቅጣጫው ይሰበሰባሉ። ይህንን ደስ የሚያሰኝ እይታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ነቢዩ ደግሞም ከሚያስጨንቁ ፍራቻዎች ያርቃል።

43:8-13 ጣዖት አምላኪዎች ለጣዖቶቻቸው እንዲከላከሉ እንዲቀርቡ ተጠርተዋል። የሚሠሩአቸውና በእነሱ የሚታመኑ እነሱኑ ይመስላሉ። የሰው መልክና ችሎታዎች አሏቸው፤ ነገር ግን የማስተዋል ችሎታ የላቸውም። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ የጸጋውን ኃይል፣ የመጽናናቱን ጣዕም፣ የመለኮታዊ አርአያነቱን ደግ እንክብካቤ፣ እና የተስፋ ቃሉን እውነት ያውቃሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV But now, this is what the Lord says– he who created you, O Jacob, he who formed you, O Israel: “Fear not, for I have re… English BCV ሕዚ ግና ኦ ያእቆብ፥ እቲ ዝፈጠረካ፥ ኦ እስራኤል፥ እቲ ዝሰርሐካ፥ እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል ኣሎ፦ “ተቤዚወካ እየ እሞ፥ ኣይትፍራሕ፤ ብስምካ ፀዋዕኩኻ፤ ንስኻ ናተይ ኢኻ። ትግርኛ GAZBIB Amma garuu yaa Yaaqoob, yaa Israa'el, Waaqayyo inni si uume, inni si tolches, “Ani si fureera hin sodaatin, “Ati kan ko… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይእዜኒ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር አምላክ ዘገብረኪ ያዕቆብ ወዘፈጠረከ እስራኤል፦ ኢትፍራህ እንከ እስመ አድኀንኩከ ወሰመይኩ ስመከ ወዚአየ አንተ። giz GAZGAZ Amma garuu yaa Yaaqoob, yaa Israa'el, Waaqayyo inni si uume, inni si tolches, “Ani si fureera hin sodaatin, “Ati kan ko… Afaan Oromoo BCV aksum ሕዚ ግና ኦ ያእቆብ፥ እቲ ዝፈጠረካ፥ ኦ እስራኤል፥ እቲ ዝሰርሐካ፥ እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል ኣሎ፦ “ተቤዚወካ እየ እሞ፥ ኣይትፍራሕ፤ ብስምካ ፀዋዕኩኻ፤ ንስኻ ናተይ ኢኻ። ትግርኛ AMHNIV አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ! የፈጠረህ፤ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤ አማርኛ SWAHSUV Lakini sasa, Bwana aliyekuhuluku, Ee Yakobo, yeye aliyekuumba, Ee Israeli, asema hivi, Usiogope, maana nimekukomboa; ni… Kiswahili