ተአምራት

32 ቁጥሮች20አማርኛ

ማር 10:27

27ኢየሱስም ተመለከታቸውና፦ “ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላልና፡” አለ።

ሉቃ 18:27

27እርሱ ግን፦ “በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል” አለ።

ማር 9:23

23ኢየሱስም፦ “ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡” አለው።

ኤር 32:27

27እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን?

ዳዊ 139:13-14

13አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል።

14ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።

ሉቃ 1:37

37ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።”

ማቴ 19:26

26ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ፦ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል፡” አላቸው።

ማቴ 17:20

20ኢየሱስም፦ “ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ‘ከዚህ ወደዚያ እለፍ’ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።

ሉቃ 9:16-17

16አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ፥ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረካቸው ቆርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛርሙርቱ ሰጠ።

17ሁሉም በልተው ጠገቡ፥ ከእነርሱም የተረፈውን ቍርስራሽ አሥራ ሁለት መሶብ ወሰዱ።

ሉቃ 8:50

50ኢየሱስ ግን ሰምቶ፦ “አትፍራ፤ እመን ብቻ ትድንማለች” ብሎ መለሰለት።

ሉቃ 13:10-17

10በሰንበትም በአንድ ምኵራብ ያስተምር ነበር።

11እነሆም፥ ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባት ሴት ነበረች፥ እርስዋም ጐባጣ ነበረች ቀንታም ልትቆም ከቶ አልተቻላትም።

12ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና፦ “አንቺ ሴት፥ ከድካምሽ ተፈትተሻል” አላት፥

13እጁንም ጫነባት፤ ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።

14የምኵራብ አለቃ ግን ኢየሱስ በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ መለሰና ሕዝቡን፦ “ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይደለም፡” አለ።

15ጌታም መልሶ፦ “እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውኃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን?

16ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን?” አለው።

17ይህንም ሲናገር ሳለ የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ሁሉ ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው።

ማር 6:49-50

49እነርሱ ግን በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምትሀት መሰላቸውና ጮኹ፥

50ሁሉ አይተውታልና፥ ታወኩም። ወዲያውም ተናገራቸውና፦ “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፥ አትፍሩ፡” አላቸው።

ዳዊ 9:1

1አቤቱ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።

ማቴ 21:21

21ኢየሱስም መልሶ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት ይሆናል፤

ሐሥ 22:7

7በምድርም ላይ ወድቄ፦ ‘ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ?’ የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ።

ሐሥ 1:9

9ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው።

ማቴ 1:22-23

22በነቢዩ ከጌታ ዘንድ፦

23“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም፦ ‘አማኑኤል፡’ ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ነው፤ ትርጓሜውም፦ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር፡” ነው።

ሐሥ 4:31

31ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ።

ኢሳ 7:14

14ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም፡ አማኑኤል፡ ብላ ትጠራዋለች።

ዮሐ 20:8-9

8በዚያን ጊዜ አስቀድሞ ወደ መቃብር የመጣውም ሌላው ደቀ መዝሙር ደግሞ ገባ፥ አየም፥ አመነም፤

9ከሙታን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው የሚለውን የመጽሐፉን ቃል ገና አላወቁም ነበርና።