የሐዋርያት ሥራ 1

AMHEVGአማርኛ23 ጥቅሶች3:50 አዳምጥ
አዳምጥ 3:50 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፥ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው ሁሉ መጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ፤

3ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።

4ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን፦ “ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤

5ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ፡” አለ።

6እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ፦ “ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት።

7እርሱም አለ፦ “አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤

8ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”

9ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው።

10እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤

11ደግሞም፦ “የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል፡” አሉአቸው።

12በዚያን ጊዜ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ እርሱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው።

13በገቡም ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፥ ጴጥሮስና ዮሐንስም፥ ያዕቆብም፥ እንድርያስም፥ ፊልጶስም፥ ቶማስም፥ በርተሎሜዎስም፥ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም።

14እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።

15በዚህም ወራት ጴጥሮስ መቶ ሀያ በሚያህል በሰዎች ማኅበር አብረው በነበሩ በወንድሞቹ መካከል ተነሥቶ አለ፦

16“ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤

17ከእኛ ጋር ተቈጥሮ ነበርና፥ ለዚህም አገልግሎት ታድሎ ነበርና።”

18ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤

19በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው ‘አኬልዳማ’ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም ‘የደም መሬት’ ማለት ነው።

20“በመዝሙር መጽሐፍ፦ ‘መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን የሚኖርባትም አይኑር፤’ ደግሞም፦ ‘ሹመቱን ሌላ ይውሰዳት፥’ ተብሎ ተጽፎአልና።

21ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል።”

23ኢዮስጦስም የሚሉትን በርስያን የተባለውን ዮሴፍንና ማትያስን ሁለቱን አቆሙ።

24ሲጸልዩም፦ “የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ፥ ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው፡” አሉ።

26ዕጣም ተጣጣሉላቸው፥ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀና ከአሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቈጠረ።

ማብራሪያ

1:1-5 ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ሊሠሩት የሚገባውን ሥራ ነገራቸው። ሐዋርያት በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ነበር፤ ክርስቶስም ከዚያ እንዳይወጡ ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስን መፍሰስ እንዲጠብቁ አዝዟቸው ነበር። ይህ በመንፈስ ቅዱስ የሚደረግ ጥምቀት ሲሆን፣ ተአምራት እንዲሠሩ ኃይልን የሚሰጣቸው፣ ነፍሳቸውንም የሚያበራና የሚቀድስ ነበር። ይህም መለኮታዊውን የተስፋ ቃል ያረጋግጣል፤ ከክርስቶስ ሰምተነዋልና በእርሱ ላይ እንድንደገፍ ያበረታታናል። ምክንያቱም በእርሱ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ሁሉ አዎንና አሜን ናቸውና።

ከ1:6-11 ጌታቸው እንዲፈልጉት ፈጽሞ ባላዘዛቸው ወይም ባላበረታታቸው ነገር ላይ በጋለ ስሜት ይጠይቁ ነበር። ጌታችን ዕርገቱና የመንፈስ ቅዱስ ትምህርት እነዚህን ተስፋዎች በቅርቡ እንደሚያስወግድ ያውቅ ነበርና የገሠጻቸው ብቻ ነበር፤ ነገር ግን የተከለከለውን እውቀት የመፈለግ ፍላጎትን እንዲጠነቀቅ በሁሉም ዘመናት ለቤተ ክርስቲያኑ ማስጠንቀቂያ ነው። ደቀ መዛሙርቱን ከሞቱም በፊትም ሆነ ከትንሣኤው በኋላ ግዴታቸውን እንዲወጡ መመሪያዎችን ሰጥቷቸው ነበር፤ ይህ እውቀትም ለክርስቲያን በቂ ነው። ለእምነተኞች ለፈተናዎቻቸውና ለአገልግሎቶቻቸው የሚመጥን ኃይል እንደሚሰጥ ቃል መግባቱ በቂ ነው፤ በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ሥር ሆነው በሆነ መንገድ በምድር ላይ ለክርስቶስ ምስክሮች ሊሆኑ ይችላሉ፤ እርሱ ግን በሰማይ ጉዳያቸውን በፍጹም ጥበብ፣ እውነትና ፍቅር ሲያስተዳድ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In my former book, Theophilus, I wrote about all that Jesus began to do and to teach English BCV ኦ ቴዎፍሎስ፥ ኣብቲ ቐዳማይ ፅሑፈይ፥ ብዛዕባ እቲ ኢየሱስ ካብ መጀመርታ ሒዙ፥ ነቶም ብመንፈስ ቅዱስ ዝሓረዮም ሃዋርያት ኣዚዙ፥ ክሳዕ እታ ንሰማይ ዝዓረገላ መዓልቲ፥ ዝገበሮን ዝመሃሮን ፅሒ… ትግርኛ GAZBIB Yaa ulfaataa Tewofilos! Macaafa koo isa kanaan duraa keessatti, waan Yesus hojjetee fi barsiise hundumaa caafeera. Afaan Oromoo BCV GIZ ቀዳሚ ጸሐፍኩ ለከ መጽሐፈ ኦ! ታኦፊላ። በኵሉ ግብር ዘአኀዘ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ይግበር ወይምሀር። giz GAZGAZ Yaa ulfaataa Tewofilos! Macaafa koo isa kanaan duraa keessatti, waan Yesus hojjetee fi barsiise hundumaa caafeera. Afaan Oromoo BCV aksum ኦ ቴዎፍሎስ፥ ኣብቲ ቐዳማይ ፅሑፈይ፥ ብዛዕባ እቲ ኢየሱስ ካብ መጀመርታ ሒዙ፥ ነቶም ብመንፈስ ቅዱስ ዝሓረዮም ሃዋርያት ኣዚዙ፥ ክሳዕ እታ ንሰማይ ዝዓረገላ መዓልቲ፥ ዝገበሮን ዝመሃሮን ፅሒ… ትግርኛ AMHNIV ቴዎፍሎስ ሆይ፤ ኢየሱስ ለማድረግና ለማስተማር የጀመረውን ሁሉ ቀደም ባለው መጽሐፌ ጽፌልሃለሁ፤ አማርኛ SWAHSUV Kitabu kile cha kwanza nalikiandika, Theofilo, katika habari ya mambo yote aliyoanza Yesu kufanya na kufundisha, Kiswahili