ትንቢተ ኢሳይያስ 7

AMHEVGአማርኛ24 ጥቅሶች4:13 አዳምጥ
አዳምጥ 4:13 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፥ ሊያሸንፉአትም አልቻሉም።

2ለዳዊትም ቤት፦ ሶርያ ከኤፍሬም ጋር ተባብረዋል፡ የሚል ወሬ ተነገረ፤ የእርሱም ልብ የሕዝቡም ልብ የዱር ዛፍ በነፋስ እንድትናወጥ ተናወጠ።

3እግዚአብሔርም ኢሳይያስን አለው፦ አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኵሬ መስኖ ጫፍ ውጡ፤

4እንዲህም በለው፦ ተጠበቅ፥ ዝምም በል፤ ስለ እነዚህ ስለሚጤሱ ስለ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች፥ ስለ ሶርያና ስለ ረአሶን ስለ ሮሜልዩም ልጅ ቍጣ አትፍራ፥ ልብህም አይድከም።

5ሶርያና ኤፍሬም የሮሜልዩም ልጅ፦ ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቀውም፥ እንስበረውም፥ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥበት፡ ብለው ክፋት ስለ መከሩብህ፤

7ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም።

8የሶርያ ራስ ደማስቆ ነው፥ የደማስቆም ራስ ረአሶን ነው፤ በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ ኤፍሬም ይሰባበራልና ሕዝብ አይሆንም፤

9የኤፍሬምም ራስ ሰማርያ ነው፥ የሰማርያም ራስ የሮሜልዩ ልጅ ነው። ባታምኑ አትጸኑም።

10እግዚአብሔርም ደግሞ አካዝን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦

11ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ቢሆን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ምልክትን ለምን።

12አካዝም፦ አልለምንም፥ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም፡ አለ።

13እርሱም አለ፦ እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፤ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን? አምላኬን ደግሞ የምታደክሙ፤

14ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም፡ አማኑኤል፡ ብላ ትጠራዋለች።

15ክፉን ለመጥላት መልካሙንም ለመምረጥ ሲያውቅ ቅቤና ማር ይበላል።

16ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች።

17እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።

18በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በግብፅ ወንዝ ዳርቻ ያለውን ዝምብ በአሦርም አገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል።

19ይመጡማል፥ እነርሱም ሁሉ በበረሃ ሸለቆ በድንጋይም ዋሻ ውስጥ በእሾህ ቍጥቋጦ ሁሉ ላይ በማሰማርያውም ሁሉ ላይ ይሰፍራሉ።

20በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይበላል።

21በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሰው አንዲት ጊደርን ሁለት በጎችንም ያሳድጋል፤

22ከሚሰጡት ወተት ብዛት የተነሣ ቅቤ ይበላል፤ በአገሪቱም መካከል የቀረ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላል።

23በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሺህ ብር የተገመተ ሺህ የወይን ግንድ በነበረበት ስፍራ ሁሉ ለኵርንችትና ለእሾህ ይሆናል።

24ኵርንችትና እሾህ በምድር ሁሉ ላይ ነውና በፍላጻና በቀስት ወደዚያ ይገባሉ።

25በመቈፈርያም ወደ ተቈፈሩ ኮረብቶች ሁሉ ከኵርንችትና እሾህ ፍርሃት የተነሣ ወደዚያ አትሄድም፤ ነገር ግን የበሬ ማሰማርያና የበግ መራገጫ ይሆናል።

ማብራሪያ

፯:፩-፱ ኃጢአተኞች ሰዎች ብዙውን ጊዜ እንደራሳቸው በሆኑ ክፉዎች ይቀጣሉ። በታላቅ ጭንቀትና ግራ መጋባት ውስጥ ሆነው፣ አይሁዳውያን ሁሉ ነገር እንደጠፋ ተስፋ ቆረጡ። እግዚአብሔርን ጠላታቸው አድርገው ነበርና፣ እርሱን ወዳጃቸው እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም ነበር። ነቢዩም በእምነትና በእግዚአብሔር ላይ በመደገፍ ጠላቶቻቸውን እንዲንቁ ሊያስተምራቸው ይገባል። አካዝ በፍርሃት እነርሱን ሁለት ኃያላን ነገሥታት ብሎ ገለጻቸው። ነቢዩም፦ አይደለም፤ እነርሱ አስቀድሞ የጠፉ የሚያጨሱ የችቦ ጭራዎች ብቻ ናቸው አላቸው። የሶርያና የእስራኤል ሁለት መንግሥታት ሊጠፉ ተቃርበው ነበር። እግዚአብሔር ለምድር ችቦዎች ሥራ ሲኖረው፣ በፊታቸው ያለውን ሁሉ ያወድማሉ፤ ነገር ግን ሥራቸው ሲፈጸም፣ በጢስ ውስጥ ይጠፋሉ። አካዝ እጅግ የሚያስፈራው ያሰበው ነገር የሽንፈታቸው ምክንያት ሆነ፤ ምክንያቱም በአንተ ላይ ክፉ ምክር ስለመከሩ ነውና፣ ይህም ለእግዚአብሔር በደል ነው። እግዚአብሔር ተሳላቂዎችን ይጸየፋቸዋልና ያ ጥረት እንዳይሳካ ቃሉን ሰጠ። ሰው ያቅዳል እንጂ፣ እግዚአብሔር ግን ያደርጋል። እነርሱ ራሳቸው የጥፋት አፋፍ ላይ እያሉ ጎረቤቶቻቸውን ሊያጠፉ መሞከራቸው የሞኝነት ሥራ ነበር። ኢሳይያስም አይሁዳውያንን በተሰጣቸው ዋስትናዎች እንዲተማመኑ ሊያበረታታቸው ይገባል። በፈተናዎች ጊዜ አእምሮን ለማረጋጋትና ለማሰባሰብ እምነት ፍጹም አስፈላጊ ነው።

፯፡፲-፲፮

ወደ እግዚአብሔር የተሰወረ ልባዊ አለመውደድ ብዙውን ጊዜ ለእርሱ ባለው የአክብሮት ሽፋን ይሸፈናል። እግዚአብሔርን እንደማያምኑ የወሰኑ ሰዎች ግን እርሱን እንደማይፈትኑት ያስመስላሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV When Ahaz son of Jotham, the son of Uzziah, was king of Judah, King Rezin of Aram and Pekah son of Remaliah king of Isr… English BCV ከምዙይ ድማ ኾነ፦ ወዲ ወዱ ንኦዝያን ወዲ ኢዮኣታም ኣካዝ ንጉስ ይሁዳ ኣብ ዝነበረሉ ዘመን፥ ንጉስ ሶርያ ረኣሶንን ንጉስ እስራኤል ወዲ ሮሜልዩ ፋቁሔን ንኢየሩሳሌም ክወግኡ ወፁ፤ ግና ኸሸን… ትግርኛ GAZBIB Bara Ahaaz ilmi Yotaam Uziyaa mootii Yihudaa turetti, Resiin mootiin Sooriyaa fi Pheqaan ilmi Remaaliyaa mootiin Israa'… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ ካዕበ ኮነ በመዋዕለ አካዝ ወልደ ኢዮአታም ወልደ ዖዝያን ንጉሠ ይሁዳ፤ ዓርገ ረአሶን ንጉሠ አራም፤ ወፋቁሔ ወልደ ሮሜልዩ ንጉሠ እስራኤል፤ ይትቃተልዋ ለኢየሩሳሴም ወስእንዋ ቀቲሎታ። giz GAZGAZ Bara Ahaaz ilmi Yotaam Uziyaa mootii Yihudaa turetti, Resiin mootiin Sooriyaa fi Pheqaan ilmi Remaaliyaa mootiin Israa'… Afaan Oromoo BCV aksum ከምዙይ ድማ ኾነ፦ ወዲ ወዱ ንኦዝያን ወዲ ኢዮኣታም ኣካዝ ንጉስ ይሁዳ ኣብ ዝነበረሉ ዘመን፥ ንጉስ ሶርያ ረኣሶንን ንጉስ እስራኤል ወዲ ሮሜልዩ ፋቁሔን ንኢየሩሳሌም ክወግኡ ወፁ፤ ግና ኸሸን… ትግርኛ AMHNIV የዖዝያን የልጅ ልጅ፣ የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን፣ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ነገር ግን ድል ሊያደርጓ… አማርኛ SWAHSUV Hata ikawa katika siku za Ahazi, mwana wa Yothamu, mwana wa Uzia, mfalme wa Yuda, Resini, mfalme wa Shamu, na Peka, mwa… Kiswahili