መንግሥት
17 ቁጥሮች15አማርኛ1ኛ ቆሮ 6:9-10
ማቴ 6:33
33ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
ማቴ 19:14
14ነገር ግን ኢየሱስ፦ “ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና፡” አለ፤
1ኛ ዜና 29:11
11አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።
ሉቃ 12:32
32“አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።
ማቴ 4:17
17ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፡” እያለ ይሰብክ ጀመር።
ዮሐ 3:3
3ኢየሱስም መልሶ፦ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም፡” አለው።
ኤፌ 2:19-20
ዘካ 14:9
9እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።
ኢሳ 52:7
7የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል፡ የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።
ማቴ 5:10
10ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
ሉቃ 10:9
9በእርስዋም ያሉትን ድውዮችን ፈውሱና፦ ‘የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቀረበች’ በሉአቸው።
ዳዊ 24:10
10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የጭፍሮች አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው።
ዮሐ 3:5
5ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
ኢሳ 33:22
22እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፥ እግዚአብሔር ሕግን ሰጪያችን ነው፥ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።