ትንቢተ ኢሳይያስ 33

AMHEVGአማርኛ24 ጥቅሶች4:00 አዳምጥ
አዳምጥ 4:00 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ በአንተም ላይ ወንጀል ሳይደረግ ወንጀል የምታደርግ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ ትጠፋለህ፤ መወንጀልንም በተውህ ጊዜ ይወነጅሉሃል።

2አቤቱ፥ ማረን፤ አንተን ተማምነናል፤ ጥዋት ጥዋት ክንድ በመከራም ጊዜ ማዳን ሁነን።

3ከፍጅት ድምፅ ወገኖች ሸሹ፥ በመነሣትህም አሕዛብ ተበተኑ።

4አንበጣ እንደሚሰበስብ ምርኮአችሁ ትሰበሰባለች፥ ኩብኩባም እንደሚዘልል ሰዎች ይዘልሉበታል።

5እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በፍርድና በጽድቅ ሞላት።

6የዘመንህም ጸጥታ፥ የመድኃኒት ብዛት፥ ጥበብና እውቀት ይሆናል፤ እግዚአብሔርን መፍራት መዝገቡ ነው።

7እነሆ፥ ኃይለኞቻቸው በሜዳ ይጮኻሉ፤ የሰላም መልእክተኞች መራራ ልቅሶ ያለቅሳሉ።

8መንገዶች ባድማ ሆኑ፥ ተላላፊም ቀረ፤ እርሱም ቃል ኪዳንን አፈረሰ ከተሞችንም ናቀ ሰውንም አልተመለከተም።

9ምድሪቱ አለቀሰች ከሳችም፤ ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፤ ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ።

10አሁን እነሣለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ አሁን እከበራለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ።

11ገለባን ትፀንሳላችሁ፥ እብቅንም ትወልዳላችሁ፤ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት።

12አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፥ ተቈርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ።

13እናንተ በሩቅ ያላችሁ የሠራሁትን ስሙ፥ እናንተም በቅርብ ያላችሁ ኃይሌን እወቁ።

14በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎቹን ያዘ፤ ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? ለዘላለምም ከምትነድድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ?

15በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቍር፥ ክፋትንም ከማየት ዓይኖቹን የሚጨፍን ነው።

16እርሱ ከፍ ባለ ስፍራ ይቀመጣል፤ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።

17ዓይኖችህ ንጉሥን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ያዩአታል።

18ልብህም፦ ጸሐፊ ወዴት አለ? መዛኝስ ወዴት አለ? ግንቦቹንስ የቈጠረ ወዴት አለ? ብሎ የሚያስፈራ ነገር ያስባል።

19ጨካኝን ሕዝብ፥ ቋንቋው ለማስተዋል ጥልቅ የሆነውንና አንደበቱ ለማስተዋል ጸያፍ የሆነውን ሕዝብ፥ አታይም።

20የበዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዓይኖችህ የሰላም ማደሪያ፥ ካስማውም ለዘላለም የማይነቀል አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ፥ የማይወገድ ድንኳን የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ።

21እግዚአብሔር በዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ ከእኛ ጋር በግርማ ይሆናል፤ የሚቀዘፉ መርከቦች አይገቡባትም፥ ታላላቆችም መርከቦች አያልፉባትም።

22እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፥ እግዚአብሔር ሕግን ሰጪያችን ነው፥ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።

23ገመዶችህ ላልተዋል፥ ደቀላቸውንም አላጸኑም፥ ሸራውንም መዘርጋት አልቻሉም። በዚያም ጊዜ የብዙ ምርኮ ብዝበዛ ተከፈለ፤ አንካሶች እንኳ ብዝበዛውን በዘበዙ።

24በዚያም የሚቀመጥ፦ ታምሜአለሁ፡ አይልም፥ በእርስዋም ለሚቀመጡ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።

ማብራሪያ

33:1-14 እዚህ ጋር ትዕቢተኛውና ሐሰተኛው አጥፊ ለፈጸመው ማታለልና ግፍ ሁሉ በጽድቅ ፍርድ የተጠየቀበትን እናያለን። ጻድቁ አምላክ ብዙ ጊዜ ኃጢአተኞችን በሠራውት ሥራ ልክ ይመልስላቸዋል። በእምነት በትሕትና እግዚአብሔርን የሚጠብቁት እርሱም ጸጋ የሞላበት ሆኖ ያገኙታል። ቀኑ እንደ ሆነ እንዲሁ ኃይሉ ይሁንላቸው። እግዚአብሔር በማንኛውም ማለዳ ለራሳችን ቢተወን እንጠፋለን። በየማለዳው ራሳችንን ለእርሱ አሳልፈን መስጠት አለብን፤ እንዲሁም የቀኑን ሥራ ለመሥራት በእርሱ ኃይል መውጣት አለብን። እግዚአብሔር ሲነሳ ጠላቶቹም ይበተናሉ። እውነተኛ ጥበብና እውቀት ወደ ድነት ኃይል ይመራሉ፤ ይህም በእግዚአብሔር መንገዶች ጸንተን እንድንቆም ያደርገናል። እውነተኛ እግዚአብሔርን መምሰልም በፍጹም የማይዘረፍ ወይም የማይባክን ብቸኛው ሀብት ነው። ኢየሩሳሌም የገባችበት ጭንቀት ተገልጿል። እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚገለጥበት ጊዜ ሌሎች ረዳቶች ሁሉ ሲጠፉ ነው። እግዚአብሔር ያደረገውን የሚሰሙ ሁሉ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደሚችል ይገንዘቡ። በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ከሌሎች ኃጢአተኞች የበለጠ የሚመልሱት ብዙ ነገር ይኖራቸዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Woe to you, O destroyer, you who have not been destroyed! Woe to you, O traitor, you who have not been betrayed! When y… English BCV ኣታ እንተይጠፋእኻ እተጥፍእ፥ ኣታ እንተይተጠለምካ እትጠልም ወይለኻ! ምጥፋእ ምስ ሓደግካ ኽትጠፍእ ኢኻ፤ ወንጀል ምስ ሓደግካ ኽትውንጀል ኢኻ። ትግርኛ GAZBIB Yaa isa warra kaan balleessituu, ati ofii keetii amma iyyuu hin badne'o siif wayyoo! Utuu namni dabarsee si hin kennin,… Afaan Oromoo BCV GIZ አሌ ሎሙ ለእለ ያኀስሩክሙ ወለክሙሰ አልቦ ዘያኀስረክሙ፤ ዘሂ ዐለወ አኮ ኪያክሙ ዘዐለወ፤ ወይሠገሩ ዐላዊያን ወይእኅዝዎሙ ወከመ ቍንቍኔ ልብስ ከማሁ ይትበልዑ። giz GAZGAZ Yaa isa warra kaan balleessituu, ati ofii keetii amma iyyuu hin badne'o siif wayyoo! Utuu namni dabarsee si hin kennin,… Afaan Oromoo BCV aksum ኣታ እንተይጠፋእኻ እተጥፍእ፥ ኣታ እንተይተጠለምካ እትጠልም ወይለኻ! ምጥፋእ ምስ ሓደግካ ኽትጠፍእ ኢኻ፤ ወንጀል ምስ ሓደግካ ኽትውንጀል ኢኻ። ትግርኛ AMHNIV አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣ አንት አጥፊ፣ ወዮልህ! አንተ ሳትካድ የምትክድ፣ አንት ከዳተኛ፣ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ፣ ትጠፋለህ፤ ክሕደትህንም በተውህ ጊዜ ትከዳለህ። አማርኛ SWAHSUV Ole wako uharibuye ila hukuharibiwa, utendaye hila wala hukutendwa hila! Utakapokwisha kuharibu, utaharibiwa wewe; na u… Kiswahili