ትንቢተ ኢሳይያስ 52

AMHEVGአማርኛ15 ጥቅሶች2:43 አዳምጥ
አዳምጥ 2:43 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።

2ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያን አራግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀመጪ፤ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።

3እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በከንቱ ተሽጣችሁ ነበር፥ ያለ ገንዘብም ትቤዣላችሁ።

4ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወገኔ በዚያ እንግዳ ሆኖ ይቀመጥ ዘንድ አስቀድሞ ወደ ግብፅ ወረደ፥ አሦርም ያለ ምክንያት በደለው።

5ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል እግዚአብሔር፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ስሜም ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ይሰደባል።

6ስለዚህ ወገኔ ስሜን ያውቃል፥ ስለዚህም የምናገር እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ፤ እነሆ፥ እኔ ነኝ።

7የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል፡ የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።

8እነሆ፥ ጕበኞችሽ ጮኸዋል፤ እግዚአብሔር ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ በአንድነትም ይዘምራሉ።

9እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፥ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፥ በአንድነትም ዘምሩ።

10እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፥ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ።

11እናንተ የእግዚአብሔር ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፥ እልፍ በሉ፥ ከዚያ ውጡ፥ ርኩስን ነገር አትንኩ፥ ከመካከልዋ ውጡ፥ ንጽሐን ሁኑ።

12እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም።

13እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል።

14ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤

15ያልተነገረላቸውንም ያያሉና፥ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ።

ማብራሪያ

52:1-12 ወንጌል በፍርሃት ለታሰሩት ነጻነትን ያውጃል። በኃጢአት ሸክም ደክመውና ከብደው ያሉት በክርስቶስ እፎይታን ያግኙ፤ የጥርጣሬያቸውንና የፍርሃታቸውን አቧራ ከራሳቸው ላይ ያራግፉ፤ ከእነዚያም ማሰሪያዎች ራሳቸውን ይፍቱ። ቤዛው ለድነታችን የከፈለው ዋጋ ብር ወይም ወርቅ፣ ወይም በሚያልፉ ነገሮች አልነበረም፤ ነገር ግን የራሱ ክቡር ደም ነበር። የዚህን ድነት ነጻነት ስንመለከት፣ እንዲሁም ኃጢአቶች ለጊዜያዊ ምቾት ምን ያህል ጎጂ እንደሆኑ ስናስብ፣ በክርስቶስ ያለውን ቤዛነት ይበልጥ እናደንቃለን። የእግዚአብሔር ክብር በእያንዳንዱ የክርስቶስ ተከታይ ውስጥ ቅድስናን እንደሚፈልግ እያስታወስን፣ በየኃጢአቱ ሁሉ ላይ ድልን እንፈልጋለንን? መልካሙ ዜና ጌታ ኢየሱስ ይነግሣል የሚለው ነው። ክርስቶስ ራሱ እነዚህን የምሥራች ዜናዎች መጀመሪያ አመጣ። አገልጋዮቹ እነዚህን መልካም ዜናዎች ያውጃሉ፤ ከዓለም ብልሹነት ራሳቸውን ንጹሕ በማድረግ፣ ለተላኩላቸው ሰዎች ውብ ናቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Awake, awake, O Zion, clothe yourself with strength. Put on your garments of splendor, O Jerusalem, the holy city. The … English BCV ኣቲ ፅዮን ተስኢ፤ ተስኢ፤ ሓይልኺ ልበሲ፤ ኣቲ ቕድስቲ ኸተማ ኢየሩሳሌም፥ ናይ መዓርግ ልብስኺ ልበሲ፤ ድሕሪ ሕዚ ዘይተገርዘን ርኹስን፥ ናባኺ ኣይኣቱን እዩ እሞ። ትግርኛ GAZBIB Dammaqi yaa Xiyoon, humna godhadhuutii ka'i! Yaa Yerusaalem mandara qulqulluu nana, ka'ii uffata miidhaginaa keetii uff… Afaan Oromoo BCV GIZ ተንሥኢ ተንሥኢ ጽዮን ልበሲ ኀይለኪ ወእንቲኒ ኢየሩሳሌም ልበሲ ትርሲተኪ ሀገር ቅደስት፤ ወኢየኀልፍ እንከ እንተ ኀቤኪ ቈላፍ ወርኩስ። giz GAZGAZ Dammaqi yaa Xiyoon, humna godhadhuutii ka'i! Yaa Yerusaalem mandara qulqulluu nana, ka'ii uffata miidhaginaa keetii uff… Afaan Oromoo BCV aksum ኣቲ ፅዮን ተስኢ፤ ተስኢ፤ ሓይልኺ ልበሲ፤ ኣቲ ቕድስቲ ኸተማ ኢየሩሳሌም፥ ናይ መዓርግ ልብስኺ ልበሲ፤ ድሕሪ ሕዚ ዘይተገርዘን ርኹስን፥ ናባኺ ኣይኣቱን እዩ እሞ። ትግርኛ AMHNIV ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ኀይልን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ! የክብር ልብስሽን ልበሺ፤ ያልተገረዘ የረከሰም ከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም። አማርኛ SWAHSUV Amka, amka, jivike nguvu zako, Ee Sayuni; Jivike mavazi yako mazuri, Ee Yerusalemu, mji mtakatifu; Kwa maana tokea sasa… Kiswahili