የዮሐንስ ወንጌል 18

AMHEVGአማርኛ40 ጥቅሶች5:51 አዳምጥ
አዳምጥ 5:51 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ኢየሱስም ይህን ብሎ አትክልት ወዳለበት ስፍራ ወደ ቄድሮን ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ እርሱም ደቀ መዛሙርቱም በዚያ ገቡ።

2ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱም ብዙ ጊዜ ወደዚያ ስለ ተሰበሰቡ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ደግሞ ስፍራውን ያውቅ ነበር።

3ስለዚህ ይሁዳ ጭፍሮችንና ከካህናት አለቆች ከፈሪሳውያንም ሎሌዎችን ተቀብሎ በችቦና በፋና በጋሻ ጦርም ወደዚያ መጣ።

4ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና፦ “ማንን ትፈልጋላችሁ?” አላቸው።

5“የናዝሬቱን ኢየሱስን” ብለው መለሱለት። ኢየሱስ፦ “እኔ ነኝ” አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ነበር።

6እንግዲህ፦ “እኔ ነኝ” ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ወደቁ።

7ደግሞም፦ “ማንን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፦ “የናዝሬቱን ኢየሱስን” አሉት።

8ኢየሱስ መልሶ፦ “እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ እንግዲህ እኔን ትፈልጉ እንደ ሆናችሁ እነዚህ ይሂዱ ተዉአቸው” አለ፤

9ይህም፦ “ከእነዚህ ከሰጠኸኝ አንዱን ስንኳ አላጠፋሁም፡” ያለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።

10ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ስለ ነበረው መዘዘው፥ የሊቀ ካህናቱንም ባርያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የባርያውም ስም ማልኮስ ነበረ።

11ኢየሱስም ጴጥሮስን፦ “ሰይፍህን ወደ ሰገባው ክተተው፤ አብ የሰጠኝን ጽዋ አልጠጣትምን?” አለው።

12እንግዲህ የሻለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሎሌዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት፥

13አስቀድመውም ወደ ሐና ወሰዱት፤ በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ለነበረው ለቀያፋ አማቱ ነበርና።

14ቀያፋም፦ “አንድ ሰው ስለ ሕዝብ ይሞት ዘንድ ይሻላል፡” ብሎ ለአይሁድ የመከራቸው ነበረ።

15ስምዖን ጴጥሮስም ሌላውም ደቀ መዝሙር ኢየሱስን ተከተሉ። ያም ደቀ መዝሙር በሊቀ ካህናቱ ዘንድ የታወቀ ነበረ፥ ወደ ሊቀ ካህናቱም ግቢ ከኢየሱስ ጋር ገባ፤

16ጴጥሮስ ግን በውጭ በበሩ ቆሞ ነበር። እንግዲህ በሊቀ ካህናቱ ዘንድ የታወቀው ሌላው ደቀ መዝሙር ወጣ፥ ለበረኛይቱም ነግሮ ጴጥሮስን አስገባው።

17በረኛ የነበረችይቱም ገረድ ጴጥሮስን፦ “አንተ ደግሞ ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህምን?” አለችው። እርሱ፦ “አይደለሁም” አለ።

18ብርድ ነበረና ባሮችና ሎሌዎች የፍም እሳት አንድደው ቆሙ፡ ይሞቁም ነበር፤ ጴጥሮስም ደግሞ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ይሞቅ ነበር።

19ሊቀ ካህናቱም ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀው።

20ኢየሱስም መልሶ አለው፦ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ እኔ ሁልጊዜ አስተማርሁ፥ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።

21ስለምን ትጠይቀኛለህ? ለእነርሱ የተናገርሁትን የሰሙትን ጠይቅ፤ እነሆ፥ እነዚህ እኔ የነገርሁትን ያውቃሉ” አለው።

22ይህንም ሲል በዚያ ቆሞ የነበረው ከሎሌዎች አንዱ፦ “ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልሳለህን?” ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው።

23ኢየሱስም መልሶ፦ “ክፉ ተናግሬ እንደ ሆንሁ ስለ ክፉ መስክር፤ መልካም ተናግሬ እንደ ሆንሁ ግን ሰለ ምን ትመታኛለህ?” አለው።

24ስለዚህ ሐና እንደ ታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ሰደደው።

25ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። እንግዲህ፦ “አንተ ደግሞ ከደቀ መዛሙርቱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም፦ “አይደለሁም” ብሎ ካደ።

26ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ዘመድ የሆነ ከሊቀ ካህናቱ ባሮች አንዱ፦ “በአትክልቱ ከእርሱ ጋር እኔ አይቼህ አልነበረምን?” አለው።

27ጴጥሮስም እንደ ገና ካደ፥ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።

28ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ገዡ ግቢ ወሰዱት፤ ማለዳም ነበረ፤ እነርሱም የፋሲካ በግ ይበሉ ዘንድ እንጂ እንዳይረክሱ ወደ ገዡ ግቢ አልገቡም።

29ስለዚህ ጲላጦስ ወደ ውጭ ወደ እነርሱ ወጥቶ፦ “ይህን ሰው ስለ ምን ትከሱታላችሁ፡” አላቸው።

30እነርሱም መልሰው፦ “ይህስ ክፉ አድራጊ ባይሆን ወደ አንተ አሳልፈን ባልሰጠነውም ነበር፡” አሉት።

31ጲላጦስም፦ “እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት፡” አላቸው። አይሁድም፦ “ለእኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፡” አሉት፤

32ኢየሱስ በምን ዓይነት ሞት ሊሞት እንዳለው ሲያመለክት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።

33ጲላጦስም እንደ ገና ወደ ገዡ ግቢ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ፦ “የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው።

34ኢየሱስም መልሶ፦ “አንተ ይህን የምትለው ከራስህ ነውን ወይስ ሌሎች ስለ እኔ ነገሩህን?” አለው።

35ጲላጦስ መልሶ፦ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል?” አለው።

36ኢየሱስም መልሶ፦ “መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴስ ከዚህ ዓለም ብትሆን፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም፡” አለው።

37ጲላጦስም፦ “እንግዲያ ንጉሥ ነህን?” አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ፡ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል፡” አለው።

38ጲላጦስ፦ “እውነት ምንድር ነው?” አለው። ይህንም ብሎ ዳግመኛ ወደ አይሁድ ወጥቶ፦ “እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትም።

39ነገር ግን በፋሲካ አንድ ልፈታላችሁ ልማድ አላችሁ፤ እንግዲህ የአይሁድን ንጉሥ ልፈታላችሁ ትወዳላችሁን?” አላቸው።

40ሁሉም ደግመው፦ “በርባንን እንጂ ይህን አይደለም፡” እያሉ ጮኹ። በርባን ግን ወንበዴ ነበረ።

ማብራሪያ

18:1-12

ኃጢአት የተጀመረው በኤደን ገነት ውስጥ ነው፤ እዚያም መርገም ታወጀ፤ እዚያም ቤዛው ቃል ተገባለት። ያ ተስፋ የተደረገበት ዘር ደግሞ በአንድ ገነት ውስጥ ከጥንቱ እባብ ጋር ወደ ግጭት ገባ። ክርስቶስም በገነት ውስጥ ተቀበረ። እኛም በገነቶቻችን ስንሄድ፣ ክርስቶስ በገነት ውስጥ ስለደረሰበት መከራ ለማሰላሰል ከዚያ አጋጣሚውን እንውሰድ። ጌታችን ኢየሱስ በእርሱ ላይ የሚመጣውን ሁሉ እያወቀ ወጣና፣ “ማንን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቀ። ሕዝቡ ሊያነግሡት በፈለጉ ጊዜ፣ እርሱ ራሱን አገለለ።

18:13-27

ስምዖን ጴጥሮስ ጌታውን ካደ። ዝርዝሮቹ በሌሎቹ ወንጌሎች ማብራሪያዎች ውስጥ ተስተውለዋል። የኃጢአት መጀመሪያ ውኃ እንደ መልቀቅ ነው። የውሸት ኃጢአት ፍሬያማ ኃጢአት ነው፤ አንድ ውሸት ሌላውን ለመደገፍ ይፈልጋል፣ ያም ደግሞ ሌላውን። ራሳችንን ለአደጋ እንድንጥል የሚጠራን ጥሪ ግልጽ ከሆነ፣ እግዚአብሔር እርሱን እንድናከብር እንደሚያስችለን ተስፋ ልናደርግ እንችላለን፤ ካልሆነ ግን እግዚአብሔር ራሳችንን እንድንሸርምጥ እንደሚተወን ልንፈራ እንችላለን።

ስለ ኢየሱስ ተአምራት፣ በእነርሱም ብዙ መልካም ስራ እንደሰራ እንዲሁም ትምህርቱንም እንዳረጋገጠ ምንም አልተናገሩም። እንደዚሁም የክርስቶስ ጠላቶች እውነቱን እየተከራከሩ ሳሉ፣ ሆን ብለው ዓይኖቻቸውን በእርሱ ላይ ይጨፍናሉ። እርሱ ወደ ሰሙት ሁሉ ይግባኝ አለ። የክርስቶስ ትምህርት ለሚያውቁት ሁሉ በአስተማማኝ ሁኔታ ይግባኝ ሊል ይችላል፤ በእውነት የሚፈርዱትም ለእርሱ ይመሰክራሉ። በበደል ምክንያት ያለን ቁጣ ፈጽሞ በስሜት የተሞላ መሆን የለበትም። እርሱን ከጎዳው ሰው ጋር በምክንያት ተነጋገረ፤ እኛም እንደዚሁ ማድረግ እንችላለን።

18:28-32 ብዙ መልካም ያደረገውን ሰው ለሞት አሳልፎ መስጠት ኢፍትሐዊ ነበርና፣ ስለዚህ አይሁድ ነቀፋን ለማስወገድ ፈቃደኛ ነበሩ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV When he had finished praying, Jesus left with his disciples and crossed the Kidron Valley. On the other side there was … English BCV ኢየሱስ እዙይ ምስ በለ፥ ምስ ደቀ መዛሙርቱ፥ ናብ ማዕዶ ሩባ ቄድሮን ሰጊሩ፥ ናብታ ኣታኽልቲ ዘለዋ ቦታ ኸደ፤ ምስ ደቀ መዛሙርቱውን ናብኣ ኣተወ። ትግርኛ GAZBIB Yesus dubbii kana erga dubbatee bartoota isaa wajjin ka'ee, iddoo dhaabaa dachaa Qedroon gama jiru tokko dhaqe; inni, b… Afaan Oromoo BCV GIZ ወዘንተ ብሂሎ ወጽአ እግዚእ ኢየሱስ ምስለ አርዳኢሁ ማዕዶተ ቄድሮስ ፈለገ አርዝ። ወቦ ህየ ገነት ዐጸደ ሐምል ወቦአ እግዚእ ኢየሱስ ውስቴታ ምስለ አርዳኢሁ። giz GAZGAZ Yesus dubbii kana erga dubbatee bartoota isaa wajjin ka'ee, iddoo dhaabaa dachaa Qedroon gama jiru tokko dhaqe; inni, b… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሱስ እዙይ ምስ በለ፥ ምስ ደቀ መዛሙርቱ፥ ናብ ማዕዶ ሩባ ቄድሮን ሰጊሩ፥ ናብታ ኣታኽልቲ ዘለዋ ቦታ ኸደ፤ ምስ ደቀ መዛሙርቱውን ናብኣ ኣተወ። ትግርኛ AMHNIV ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሆኖ የቄድሮንን ሸለቆ ተሻገረ፤ ማዶ ወደ ነበረውም የአትክልት ስፍራ ገቡ። አማርኛ SWAHSUV Alipokwisha kusema hayo, Yesu alitoka pamoja na wanafunzi wake kwenda ng'ambo ya kijito Kedroni, palipokuwapo bustani; … Kiswahili