የዮሐንስ ወንጌል 18

AMHNIVአማርኛ40 ጥቅሶች6:36 አዳምጥ
አዳምጥ 6:36 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሆኖ የቄድሮንን ሸለቆ ተሻገረ፤ ማዶ ወደ ነበረውም የአትክልት ስፍራ ገቡ።

2ብዙውን ጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚያ ስለሚገናኝ፣ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ቦታውን ያውቅ ነበር።

3ይሁዳም ወታደሮችን እንዲሁም ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን የተላኩ ሎሌዎችን እየመራ ወደ አትክልቱ ስፍራ መጣ፤ እነርሱም ችቦ፣ ፋኖስና የጦር መሣሪያ ይዘው ነበር።

4ኢየሱስም የሚደርስበትን ሁሉ ዐውቆ ወጣና፣ “የምትፈልጉት ማንን ነው?” አላቸው።

5እነርሱም፣ “የናዝሬቱን ኢየሱስን” አሉት። ኢየሱስም፣ “እርሱ እኔ ነኝ” አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ነበር።

6ኢየሱስም፣ “እርሱ እኔ ነኝ” ባለ ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው መሬት ላይ ወደቁ።

7እንደ ገናም፣ “የምትፈልጉት ማንን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “የናዝሬቱን ኢየሱስን” አሉት።

8ኢየሱስም መልሶ፣ “ ‘እርሱ እኔ ነኝ’ ብያችኋለሁ እኮ፤ እኔን የምትፈልጉ ከሆነ፣ እነዚህ ይሂዱ ተዉአቸው” አለ፤

9ይህ የሆነው፣ “ከሰጠኸኝ ከእነዚህ አንድም አልጠፋብኝም” ብሎ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው።

10ሰይፍ ይዞ የነበረው ስምዖን ጴጥሮስም፣ ሰይፉን መዞ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ቀኝ ጆሮ ቈረጠ፤ የአገልጋዩም ስም ማልኮስ ይባል ነበር።

11ኢየሱስም ጴጥሮስን፣ “ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ! አብ የሰጠኝን ጽዋ አልጠጣምን?” አለው።

12ወታደሮቹም ከአዛዣቸውና ከአይሁድ ሎሌዎች ጋር በመሆን ኢየሱስን ያዙት፤ አስረውም፣

13በመጀመሪያ፣ የቀያፋ አማት ወደ ነበረው ወደ ሐና አመጡት፤ ቀያፋም የዓመቱ ሊቀ ካህናት ነበር።

14ቀያፋም፣ ‘ለሕዝቡ ሲባል አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል’ ብሎ አይሁድን የመከረ ነበር።

15ስምዖን ጴጥሮስና አንድ ሌላ ደቀ መዝሙር ኢየሱስን ተከተሉት። ይህም ደቀ መዝሙር በሊቀ ካህናቱ ይታወቅ ስለ ነበር፣ ከኢየሱስ ጋር ወደ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ገባ፤

16ጴጥሮስ ግን ከበሩ ውጭ ቀረ። በሊቀ ካህናቱ የታወቀው ሌላው ደቀ መዝሙርም ተመለሰና በር ጠባቂዋን አነጋግሮ ጴጥሮስን ይዞት ገባ።

17በር ጠባቂዋም ጴጥሮስን፣ “አንተ ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህምን?” አለችው። እርሱም፣ “አይደለሁም” አለ።

18ብርድ ስለ ነበር አገልጋዮቹና ሎሌዎቹ ባያያዙት የከሰል ፍም ዙሪያ ለመሞቅ ቆመው ሳሉ፣ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋር ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር።

19በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀው።

20ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለዓለም በግልጽ ተናግሬአለሁ፤ አይሁድ በተሰበሰቡበት ምኵራብ፣ በቤተ መቅደስም ሁል ጊዜ አስተምሬአለሁ፤ በስውር የተናገርሁት የለም።

21ለምን እኔን ትጠይቀኛለህ? የሰሙኝን ጠይቃቸው፤ እነሆ፤ የተናገርሁትን እነርሱ ያውቃሉ።”

22ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ፣ አጠገቡ ቆመው ከነበሩት ሎሌዎች አንዱ፣ “ለሊቀ ካህናቱ የምትመልሰው እንዲህ ነውን?” ብሎ በጥፊ መታው።

23ኢየሱስም፣ “ክፉ ተናግሬ ከሆነ ክፉ መናገሬን መስክር፤ እውነት ከተናገርሁ ግን ለምን ትመታኛለህ?” አለው።

24ሐናም ኢየሱስ ታስሮ እንዳለ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው።

25ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ሲሞቅ፣ “አንተ ከእርሱ ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም፣ “አይደለሁም” ሲል ካደ።

26ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮች አንዱ ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመድ፣ “በአትክልቱ ስፍራ አንተን ከእርሱ ጋር አላየሁህም?” ሲል ጠየቀው።

27ጴጥሮስም እንደ ገና ካደ፤ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።

28አይሁድም ኢየሱስን ከቀያፋ ወደ ሮማዊው ገዥ ግቢ ይዘውት ሄዱ፤ ጊዜውም ማለዳ ነበር። አይሁድም ፋሲካን መብላት እንዲችሉ፣ ላለመርከስ ወደ ገዥው ግቢ አልገቡም።

29ስለዚህ ጲላጦስ ወደ እነርሱ ወጥቶ፣ “በዚህ ሰው ላይ የምታቀርቡት ክስ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው።

30እነርሱም፣ “ይህ ሰው ወንጀለኛ ባይሆን ኖሮ፣ አንተ ፊት ባላቀረብነውም ነበር” ብለው መለሱለት።

31ጲላጦስም፣ “እናንተ ራሳችሁ ወስዳችሁ በሕጋችሁ መሠረት ፍረዱበት” አላቸው። አይሁድም፣ “እኛማ በማንም ላይ የሞት ፍርድ ለመፍረድ መብት የለንም” አሉት።

32ይህ የሆነው በምን ዐይነት ሞት እንደሚሞት ለማመልከት ሲል ኢየሱስ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው።

33ጲላጦስም ወደ ግቢው ተመልሶ ኢየሱስን አስጠራና፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው።

34ኢየሱስም፣ “ይህ ሐሳብ የራስህ ነው? ወይስ ሌሎች ስለ እኔ የነገሩህ?” ሲል መለሰለት።

35ጲላጦስም መልሶ፣ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወደ እኔ የላኩህ የራስህ ወገኖችና የካህናት አለቆች ናቸው፤ ለመሆኑ ምን አድርገህ ነው?” አለው።

36ኢየሱስም፣ “የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለም፤ ቢሆንማ ኖሮ አይሁድ እንዳይዙኝ ሎሌዎቼ በተከላከሉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለም” አለው።

37ጲላጦስም፣ “ታዲያ፣ ንጉሥ ነህ ማለት ነዋ!” አለው። ኢየሱስም፣ “እኔ ንጉሥ እንደሆንሁ መናገርህ ትክክል ነው፤ የተወለድሁት፣ ወደዚህም ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመስከር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ይሰማኛል” አለው።

38ጲላጦስም፣ “እውነት ምንድን ነው?” አለው፤ ይህን ከተናገረ በኋላም እንደ ገና ወደ አይሁድ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ የሚያስከስስ በደል አላገኘሁበትም፤

39ነገር ግን በፋሲካ አንድ እስረኛ እንድፈታላችሁ ልማድ አላችሁ፤ ስለዚህ፣ ‘የአይሁድን ንጉሥ’ እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁን?”

40እነርሱም እንደ ገና በመጮኽ፣ “የለም፤ እርሱን አይደለም! በርባንን ፍታልን!” አሉ። በርባን ግን ወንበዴ ነበረ።

ማብራሪያ

18:1-12

ኃጢአት የተጀመረው በኤደን ገነት ውስጥ ነው፤ እዚያም መርገም ታወጀ፤ እዚያም ቤዛው ቃል ተገባለት። ያ ተስፋ የተደረገበት ዘር ደግሞ በአንድ ገነት ውስጥ ከጥንቱ እባብ ጋር ወደ ግጭት ገባ። ክርስቶስም በገነት ውስጥ ተቀበረ። እኛም በገነቶቻችን ስንሄድ፣ ክርስቶስ በገነት ውስጥ ስለደረሰበት መከራ ለማሰላሰል ከዚያ አጋጣሚውን እንውሰድ። ጌታችን ኢየሱስ በእርሱ ላይ የሚመጣውን ሁሉ እያወቀ ወጣና፣ “ማንን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቀ። ሕዝቡ ሊያነግሡት በፈለጉ ጊዜ፣ እርሱ ራሱን አገለለ።

18:13-27

ስምዖን ጴጥሮስ ጌታውን ካደ። ዝርዝሮቹ በሌሎቹ ወንጌሎች ማብራሪያዎች ውስጥ ተስተውለዋል። የኃጢአት መጀመሪያ ውኃ እንደ መልቀቅ ነው። የውሸት ኃጢአት ፍሬያማ ኃጢአት ነው፤ አንድ ውሸት ሌላውን ለመደገፍ ይፈልጋል፣ ያም ደግሞ ሌላውን። ራሳችንን ለአደጋ እንድንጥል የሚጠራን ጥሪ ግልጽ ከሆነ፣ እግዚአብሔር እርሱን እንድናከብር እንደሚያስችለን ተስፋ ልናደርግ እንችላለን፤ ካልሆነ ግን እግዚአብሔር ራሳችንን እንድንሸርምጥ እንደሚተወን ልንፈራ እንችላለን።

ስለ ኢየሱስ ተአምራት፣ በእነርሱም ብዙ መልካም ስራ እንደሰራ እንዲሁም ትምህርቱንም እንዳረጋገጠ ምንም አልተናገሩም። እንደዚሁም የክርስቶስ ጠላቶች እውነቱን እየተከራከሩ ሳሉ፣ ሆን ብለው ዓይኖቻቸውን በእርሱ ላይ ይጨፍናሉ። እርሱ ወደ ሰሙት ሁሉ ይግባኝ አለ። የክርስቶስ ትምህርት ለሚያውቁት ሁሉ በአስተማማኝ ሁኔታ ይግባኝ ሊል ይችላል፤ በእውነት የሚፈርዱትም ለእርሱ ይመሰክራሉ። በበደል ምክንያት ያለን ቁጣ ፈጽሞ በስሜት የተሞላ መሆን የለበትም። እርሱን ከጎዳው ሰው ጋር በምክንያት ተነጋገረ፤ እኛም እንደዚሁ ማድረግ እንችላለን።

18:28-32 ብዙ መልካም ያደረገውን ሰው ለሞት አሳልፎ መስጠት ኢፍትሐዊ ነበርና፣ ስለዚህ አይሁድ ነቀፋን ለማስወገድ ፈቃደኛ ነበሩ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ኢየሱስም ይህን ብሎ አትክልት ወዳለበት ስፍራ ወደ ቄድሮን ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ እርሱም ደቀ መዛሙርቱም በዚያ ገቡ። አማርኛ ENGNIV When he had finished praying, Jesus left with his disciples and crossed the Kidron Valley. On the other side there was … English BCV ኢየሱስ እዙይ ምስ በለ፥ ምስ ደቀ መዛሙርቱ፥ ናብ ማዕዶ ሩባ ቄድሮን ሰጊሩ፥ ናብታ ኣታኽልቲ ዘለዋ ቦታ ኸደ፤ ምስ ደቀ መዛሙርቱውን ናብኣ ኣተወ። ትግርኛ GAZBIB Yesus dubbii kana erga dubbatee bartoota isaa wajjin ka'ee, iddoo dhaabaa dachaa Qedroon gama jiru tokko dhaqe; inni, b… Afaan Oromoo BCV GIZ ወዘንተ ብሂሎ ወጽአ እግዚእ ኢየሱስ ምስለ አርዳኢሁ ማዕዶተ ቄድሮስ ፈለገ አርዝ። ወቦ ህየ ገነት ዐጸደ ሐምል ወቦአ እግዚእ ኢየሱስ ውስቴታ ምስለ አርዳኢሁ። giz GAZGAZ Yesus dubbii kana erga dubbatee bartoota isaa wajjin ka'ee, iddoo dhaabaa dachaa Qedroon gama jiru tokko dhaqe; inni, b… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሱስ እዙይ ምስ በለ፥ ምስ ደቀ መዛሙርቱ፥ ናብ ማዕዶ ሩባ ቄድሮን ሰጊሩ፥ ናብታ ኣታኽልቲ ዘለዋ ቦታ ኸደ፤ ምስ ደቀ መዛሙርቱውን ናብኣ ኣተወ። ትግርኛ SWAHSUV Alipokwisha kusema hayo, Yesu alitoka pamoja na wanafunzi wake kwenda ng'ambo ya kijito Kedroni, palipokuwapo bustani; … Kiswahili