የሐዋርያት ሥራ 16

AMHEVGአማርኛ40 ጥቅሶች5:46 አዳምጥ
አዳምጥ 5:46 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራንም ደረሰ። እነሆም፥ በዚያ የአንዲት ያመነች አይሁዳዊት ልጅ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፤ አባቱ ግን የግሪክ ሰው ነበረ።

2ለእርሱም በልስጥራንና በኢቆንዮን ያሉ ወንድሞች መሰከሩለት።

3ጳውሎስ ይህ ከእርሱ ጋር ይወጣ ዘንድ ወደደ፥ በእነዚያም ስፍራዎች ስለ ነበሩ አይሁድ ይዞ ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ሁሉ ያውቁ ነበርና።

4በከተማዎችም ሲዞሩ በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የቈረጡትን ሥርዓት ይጠብቁ ዘንድ ሰጡአቸው።

5አብያተ ክርስቲያናትም በሃያማኖት ይበረቱ ነበር፥ በቍጥርም ዕለት ዕለት ይበዙ ነበር።

6በእስያም ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አለፉ፤

7በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ ዘድን ሞከሩ፥ የኢየሱስ መንፈስም አልፈቀደላቸውም፤

8በሚስያም አጠገብ አልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ።

9ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው፦ “ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን” እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር።

10ራእዩንም ካየ በኋላ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ልንወጣ ፈለግን፥ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናልና።

11ከጢሮአዳም ተነሥተን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ በነገውም ወደ ናጱሌ በመርከብ ሄድን፤

12ከዚያም ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ እርስዋም የመቄዶንያ ከተማ ሆና የወረዳ ዋና ከተማና ቅኝ አገር ናት፤ በዚህችም ከተማ አንዳንድ ቀን እንቀመጥ ነበር።

13በሰንበት ቀንም ከከተማው በር ውጭ የጸሎት ስፍራ በዚያ መሆኑን ስላሰብን ወደ ወንዝ አጠገብ ወጣን፤ ተቀምጠንም ለተሰበሰቡት ሴቶች ተናገርን።

14ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ የሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።

15እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፡” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።

16ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።

17እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፦ “የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው፡” ብላ ትጮኽ ነበር።

18ይህንም እጅግ ቀን አደረገች። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱን፦ “ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ” አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።

19ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤

20ወደ ገዢዎችም አቅርበው፦ “እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ።

21እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ፡” አሉ።

22ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤

23በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።

24እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው።

25በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር።

26ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።

27የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።

28ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ “ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡” ብሎ ጮኸ።

29መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤

30ወደ ውጭም አውጥቶ፦ “ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” ኣላቸው።

31እነርሱም፦ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፤ አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ” አሉት።

32ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው።

33በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤

34ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ።

35በነጋም ጊዜ ገዢዎቹ፦ “እነዚያን ሰዎች ፍታቸው” ብለው ሎሌዎቻቸውን ላኩ።

36የወኅኒውም ጠባቂ፦ “ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው።

37ጳውሎስ ግን፦ “እኛ የሮሜ ሰዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበው በወኅኒ ጣሉን፤ አሁንም በስውር ይጥሉናልን? አይሆንም ራሳቸው ግን መጥተው ያውጡን፡” አላቸው።

38ሎሌዎቹም ይህን ነገር ለገዢዎች ነገሩ። የሮሜ ሰዎችም እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ፤

39መጥተውም ማለዱአቸው፥ አውጥተውም ከከተማ ይወጡ ዘንድ ለመኑአቸው።

40ከወኅኒውም ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፥ ወንድሞችንም ባዩ ጊዜ አጽናኑአቸውና ሄዱ።

ማብራሪያ

16:1-5 ቤተ ክርስቲያን እንደ ጢሞቴዎስ ባለው መንፈስ የተነሱ ወጣት አገልጋዮች ብዙ አገልግሎት እንዲያደርጉላት መጠበቅ ተገቢ ነው። ነገር ግን ሰዎች በምንም ነገር ለመታዘዝም ሆነ ለመተባበር ፈቃደኛ ካልሆኑ፥ የክርስቲያናዊ ባሕርይ መሠረታዊ ነገሮች የጎደሉ ይመስላሉ፤ እናም የወንጌል ትምህርቶችና ትእዛዛት በተሳካ ሁኔታ አይስተምሩም ብሎ ለማመን ትልቅ ምክንያት አለ። የውሳኔው ዓላማ የሥርዓቱን ሕግና ሥጋዊ ሥርዓቶቹን ለማስቀረት ስለነበር፥ አማኞች ለእግዚአብሔርም ለሰውም ባሕርይ የሚገባ መንፈሳዊ የአምልኮ መንገድ ስላቋቋመ በክርስቲያናዊ እምነት ጸኑ። በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያን በየቀኑ በቁጥር ጨመረች።

16:6-15 የአገልጋዮች አገልግሎት ቦታ መቀያየርና መዘዋወር፣ እንዲሁም በእነርሱ አማካኝነት የጸጋ መንገዶች መሰጠት በተለይ በእግዚአብሔር መሪነትና አቅጣጫ ሥር ናቸው። የእግዚአብሔርን አርምሞ መከተል አለብን፤ ምን ለማድረግ ብንፈልግም፣ እርሱ ካልፈቀደልን፣ መገዛትና ለበጎ እንደሆነ ማመን አለብን። ሰዎች ለነፍሳቸው እርዳታ እጅግ ያስፈልጋቸዋልና፣ እርሱን መፈለግ ግዴታቸው ነው፤ እንዲሁም ሊረዷቸው የሚችሉትን በእነርሱ ዘንድ ያሉትን መጋበዝ አለባቸው። የእግዚአብሔርም ጥሪዎች በፍጥነትና በፈቃደኝነት መታዘዝ አለባቸው።

የእግዚአብሔር አምላኪዎች ከተቻለ፣ በሰንበት ቀን የተከበረ ጉባኤ ሊኖራቸው ይገባል። የምኩራብ ሕንፃዎች ባይኖሩንም፣ ይበልጥ ለግል ስፍራዎች አመስጋኞች መሆንና ወደ እነርሱም መሄድ አለብን፤ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መሰብሰብን መተው የለብንምና። ከጳውሎስ ሰሚዎች መካከል ሊዲያ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች። ሐቀኛ የሥራ መስክ ነበራት፤ ይህንንም ታሪክ ጸሐፊው ሊያመሰግናት አስተዋለ። ምንም እንኳን የምታከናውነው የንግድ ሥራ ቢኖርባትም፣ ለነፍሷ የሚሆኑ ጥቅሞችን ለመጠቀም ጊዜ አገኘች። ሥራ አለብን ብለን መናገራችን እግዚአብሔራዊ ግዴታዎችን ከመወጣት አያድነንም፤ እኛም የምናገለግለው አምላክና የምንጠብቃት ነፍስ የለንምን? ሃይማኖት ከዓለማዊ ሥራችን አይጠራንም፣ ነገር ግን በውስጡ ይመራናል።

ትዕቢት፣ ጭፍን ጥላቻና ኃጢአት የእግዚአብሔርን እውነቶች ያግዳሉ፤ ይህም የእርሱ ጸጋ ወደ አእምሮአችንና የልብ ፍላጎታችን መንገድ እስኪከፍትላቸው ድረስ ነው። ጌታ ብቻውን ልብን ቃሉን ለመቀበልና ለማመን ሊከፍት ይችላል። በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን አለብን፤ ወደ እግዚአብሔር እንደ አባት መቅረብ የሚቻለው በአማላጁ ወልድ አማካኝነት ካልሆነ በስተቀር ሌላ መንገድ የለም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV He came to Derbe and then to Lystra, where a disciple named Timothy lived, whose mother was a Jewess and a believer, bu… English BCV ካብኡ ጳውሎስ፥ ኣብ ደርቤንን ኣብ ልስጥራንን በፅሐ፤ ኣብኡ ኸዓ፥ ካብ ሓንቲ ኣይሁዳዊት ኣማኒት ሰበይትን፥ ካብ ሓደ ግሪካዊ ሰብኣይን ዝተወለደ፥ ጢሞቴዎስ ዝበሃል ደቀ መዝሙር ነበረ። ትግርኛ GAZBIB Phaawulos karaa isaa itti fufee mandara Derbee dhaqee, mandara Lisxiraattis darbe. Achi immoo Ximotewos kan jedhamu dar… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበጽሐ ሀገረ ደርቤን ወልስጥራን ወረከበ አሐደ ረድአ ዘስሙ ጢሞቴዎስ፤ ወእሙሰ አይሁዳዊት ወአምነት ወአቡሁሰ አረማዊ። giz GAZGAZ Phaawulos karaa isaa itti fufee mandara Derbee dhaqee, mandara Lisxiraattis darbe. Achi immoo Ximotewos kan jedhamu dar… Afaan Oromoo BCV aksum ካብኡ ጳውሎስ፥ ኣብ ደርቤንን ኣብ ልስጥራንን በፅሐ፤ ኣብኡ ኸዓ፥ ካብ ሓንቲ ኣይሁዳዊት ኣማኒት ሰበይትን፥ ካብ ሓደ ግሪካዊ ሰብኣይን ዝተወለደ፥ ጢሞቴዎስ ዝበሃል ደቀ መዝሙር ነበረ። ትግርኛ AMHNIV ጳውሎስ ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራን ደረሰ። በዚያም እናቱ አይሁዳዊት ሆና በጌታ ያመነች፣ አባቱ ግን የግሪክ ሰው የሆነ፣ ጢሞቴዎስ የተባለ አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ። አማርኛ SWAHSUV Basi akafika Derbe na Listra, na hapo palikuwa na mwanafunzi mmoja jina lake Timotheo, mwana wa mwanamke Myahudi aliyea… Kiswahili