የሐዋርያት ሥራ 16

AMHNIVአማርኛ40 ጥቅሶች7:22 አዳምጥ
አዳምጥ 7:22 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጳውሎስ ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራን ደረሰ። በዚያም እናቱ አይሁዳዊት ሆና በጌታ ያመነች፣ አባቱ ግን የግሪክ ሰው የሆነ፣ ጢሞቴዎስ የተባለ አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ።

2እርሱም በልስጥራንና በኢቆንዮን በነበሩት ወንድሞች ዘንድ መልካም ምስክርነት ነበረው።

3ጳውሎስም ይህ ሰው ከእርሱ ጋር እንዲሄድ ፈለገ፤ ስለዚህ በዚያ አካባቢ በነበሩ አይሁድ ምክንያት ይዞ ገረዘው፤ እነዚህ አይሁድ በሙሉ የጢሞቴዎስ አባት የግሪክ ሰው እንደሆነ ያውቁ ነበርና።

4እነርሱም ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው በሚያልፉበት ጊዜ፣ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች በኢየሩሳሌም ያሳለፉትን ውሳኔ ተቀብለው እንዲጠብቁ ለምእመናኑ ይሰጡ ነበር።

5አብያተ ክርስቲያናትም በእምነት እየበረቱና ዕለት ዕለትም በቍጥር እየጨመሩ ይሄዱ ነበር።

6ጳውሎስና ባልደረቦቹ ቃሉን በእስያ እንዳይሰብኩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው፣ በፍርግያና በገላትያ አገር ዐልፈው ሄዱ።

7ወደ ሚስያም በተቃረቡ ጊዜ፣ ወደ ቢታኒያ ሊገቡ ሞከሩ፤ ነገር ግን የኢየሱስ መንፈስ አልፈቀደላቸውም፤

8ስለዚህ በሚስያ በኩል አድርገው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ።

9ጳውሎስም ሌሊት በራእይ አንድ የመቄዶንያ ሰው ቆሞ፣ “ወደ መቄዶንያ ተሻግረህ ርዳን” ብሎ ሲለምነው አየ።

10ጳውሎስ ይህን ራእይ ካየ በኋላ፣ እግዚአብሔር ወንጌልን እንድንሰብክላቸው ጠርቶናል ብለን በመወሰን ወዲያው ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ፈለግን።

11ከጢሮአዳ በመርከብ ተነሥተን በቀጥታ ተጒዘን ወደ ሳሞትራቄ መጣን፤ በማግስቱም ጒዞአችንን ወደ ናጱሌ ቀጠልን፤

12ከዚያም የሮማውያን ቅኝና የአካባቢው የመቄዶንያ ግዛት ዋና ከተማ ወደሆነችው ወደ ፊልጵስዩስ ገባን፤ በዚያም አያሌ ቀን ተቀመጥን።

13በሰንበት ቀንም፣ የጸሎት ስፍራ በመፈለግ፣ ከከተማዪቱ በር ወጥተን ወደ አንድ ወንዝ ወረድን፤ በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩት ሴቶች መናገር ጀመርን።

14ከሚያዳምጡትም ሴቶች መካከል ልድያ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም እግዚአብሔርን የምታመልክና ከትያጥሮን ከተማ የመጣች የቀይ ሐር ነጋዴ ነበረች። ጌታም፣ ጳውሎስ የሚናገረውን በማስተዋል ትሰማ ዘንድ፣ ልቧን ከፈተላት።

15እርሷና ቤተ ሰዎቿ ከተጠመቁ በኋላም፣ “በጌታ ማመኔን በርግጥ ከተረዳችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ጥቂት ተቀመጡ” በማለት አጥብቃ ለመነችን።

16አንድ ቀን ወደ ጸሎት ስፍራ ስንሄድ፣ በጥንቈላ መንፈስ ትንቢት የምትናገር አንዲት የቤት አገልጋይ አገኘችን፤ እርሷም በዚህ የጥንቈላ ሥራዋ ለአሳዳሪዎችዋ ብዙ ገንዘብ ታስገኝላቸው ነበር።

17ይህችው አገልጋይ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፣ “እነዚህ ሰዎች የመዳንን መንገድ የሚነግሯችሁ፣ የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው!” በማለት ትጮኽ ነበር፤

18ይህንም ብዙ ቀን ደጋገመችው፤ ጳውሎስ ግን በዚህ እጅግ በመታወኩ ዘወር ብሎ ያን መንፈስ፣ “ከእርሷ እንድትወጣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ” አለው፤ መንፈሱም በዚያው ቅጽበት ወጣላት።

19አሳዳሪዎቿም የገንዘብ ማግኛ ተስፋቸው ወጥቶ መሄዱን በተረዱ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው እየጐተቱ ባለ ሥልጣኖች ወዳሉበት ወደ ገበያ ቦታ አመጧቸው።

20ገዦቹም ፊት አቅርበዋቸው እንዲህ አሉ፤ “እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ሳሉ፣ ከተማችንን አውከዋል፤

21ደግሞም እኛ ሮማውያን መቀበል ወይም መፈጸም የማይገባንን ልማድ በሕዝቡ መካከል ይነዛሉ።”

22ሕዝቡም ተባብረው በጳውሎስና በሲላስ ላይ ተነሡባቸው፤ ገዦቹም ልብሳቸው ተገፎ በበትር እንዲደበደቡ አዘዙ።

23ክፉኛ ከተደበደቡ በኋላም ወደ ወህኒ ቤት አስገቧቸው፤ የወህኒ ቤት ጠባቂውም ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።

24እርሱም ይህን የመሰለ ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ፣ ወደ ወህኒ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገብቶ እግራቸውን ከግንድ ጋር አጣብቆ አሰራቸው።

25እኩለ ሌሊት አካባቢ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎቹ እስረኞችም ያዳምጧቸው ነበር።

26ድንገትም የወህኒ ቤቱን መሠረት የሚያናውጥ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፤ ወዲያውም የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ።

27የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ከእንቅልፉ ነቅቶ የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፍተው ባየ ጊዜ፣ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ለመግደል ሰይፉን መዘዘ።

28ጳውሎስ ግን ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “እኛ ሁላችን እዚሁ ስላለን፣ በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርስ!” ብሎ ጮኸ።

29የወህኒ ቤቱ ጠባቂም መብራት ለምኖ ወደ ውስጥ ዘሎ ገባ፤ እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ እግር ላይ ወደቀ፤

30ይዞአቸው ከወጣ በኋላ፣ “እናንት ሰዎች፤ እድን ዘንድ ምን ላድርግ?” አላቸው።

31እነርሱም፣ “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት።

32ከዚያም ለእርሱና በቤቱ ላሉት ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ተናገሩ።

33የወህኒ ቤት ጠባቂውም ሌሊት በዚያኑ ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፤ ወዲያውም እርሱና ቤተ ሰቡ ሁሉ ተጠመቁ።

34የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ወደ ቤቱ ወስዶ ማእድ አቀረበላቸው፤ ከቤተ ሰቡም ሁሉ ጋር በእግዚአብሔር በማመኑ በደስታ ተሞላ።

35ሲነጋም፣ ገዦቹ፣ “እነዚያን ሰዎች ፈተህ ልቀቃቸው” ብለው መኰንኖቻቸውን ላኩበት።

36የወህኒ ቤት ጠባቂውም፣ “ገዦቹ እንድትፈቱ አዘዋል፤ ስለዚህ ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ብሎ ለጳውሎስ ነገረው።

37ጳውሎስ ግን፣ “እኛ የሮም ዜጎች ሆነን ሳለን፣ በሕዝብ ፊት ያለ ፍርድ ደብድበው ወደ እስር ቤት ወረወሩን፤ ታዲያ አሁን በስውር ሊያስወጡን ይፈልጋሉ? ይህማ አይሆንም፤ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን!” አላቸው።

38መኰንኖቹም ይህንኑ ቃል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ እነርሱም ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜጎች መሆናቸውን ሲሰሙ ደነገጡ፤

39እነርሱ ራሳቸውም መጥተው ይቅርታ ጠይቀው ከወህኒ ቤቱ አወጧቸው፤ ከተማውንም ለቀው እንዲሄዱ ለመኗቸው።

40ጳውሎስና ሲላስ ከእስር ቤቱ ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ሄዱ፤ በዚያም ወንድሞችን አግኝተው አበረታቷችው፤ ከዚያም በኋላ ሄዱ።

ማብራሪያ

16:1-5 ቤተ ክርስቲያን እንደ ጢሞቴዎስ ባለው መንፈስ የተነሱ ወጣት አገልጋዮች ብዙ አገልግሎት እንዲያደርጉላት መጠበቅ ተገቢ ነው። ነገር ግን ሰዎች በምንም ነገር ለመታዘዝም ሆነ ለመተባበር ፈቃደኛ ካልሆኑ፥ የክርስቲያናዊ ባሕርይ መሠረታዊ ነገሮች የጎደሉ ይመስላሉ፤ እናም የወንጌል ትምህርቶችና ትእዛዛት በተሳካ ሁኔታ አይስተምሩም ብሎ ለማመን ትልቅ ምክንያት አለ። የውሳኔው ዓላማ የሥርዓቱን ሕግና ሥጋዊ ሥርዓቶቹን ለማስቀረት ስለነበር፥ አማኞች ለእግዚአብሔርም ለሰውም ባሕርይ የሚገባ መንፈሳዊ የአምልኮ መንገድ ስላቋቋመ በክርስቲያናዊ እምነት ጸኑ። በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያን በየቀኑ በቁጥር ጨመረች።

16:6-15 የአገልጋዮች አገልግሎት ቦታ መቀያየርና መዘዋወር፣ እንዲሁም በእነርሱ አማካኝነት የጸጋ መንገዶች መሰጠት በተለይ በእግዚአብሔር መሪነትና አቅጣጫ ሥር ናቸው። የእግዚአብሔርን አርምሞ መከተል አለብን፤ ምን ለማድረግ ብንፈልግም፣ እርሱ ካልፈቀደልን፣ መገዛትና ለበጎ እንደሆነ ማመን አለብን። ሰዎች ለነፍሳቸው እርዳታ እጅግ ያስፈልጋቸዋልና፣ እርሱን መፈለግ ግዴታቸው ነው፤ እንዲሁም ሊረዷቸው የሚችሉትን በእነርሱ ዘንድ ያሉትን መጋበዝ አለባቸው። የእግዚአብሔርም ጥሪዎች በፍጥነትና በፈቃደኝነት መታዘዝ አለባቸው።

የእግዚአብሔር አምላኪዎች ከተቻለ፣ በሰንበት ቀን የተከበረ ጉባኤ ሊኖራቸው ይገባል። የምኩራብ ሕንፃዎች ባይኖሩንም፣ ይበልጥ ለግል ስፍራዎች አመስጋኞች መሆንና ወደ እነርሱም መሄድ አለብን፤ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መሰብሰብን መተው የለብንምና። ከጳውሎስ ሰሚዎች መካከል ሊዲያ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች። ሐቀኛ የሥራ መስክ ነበራት፤ ይህንንም ታሪክ ጸሐፊው ሊያመሰግናት አስተዋለ። ምንም እንኳን የምታከናውነው የንግድ ሥራ ቢኖርባትም፣ ለነፍሷ የሚሆኑ ጥቅሞችን ለመጠቀም ጊዜ አገኘች። ሥራ አለብን ብለን መናገራችን እግዚአብሔራዊ ግዴታዎችን ከመወጣት አያድነንም፤ እኛም የምናገለግለው አምላክና የምንጠብቃት ነፍስ የለንምን? ሃይማኖት ከዓለማዊ ሥራችን አይጠራንም፣ ነገር ግን በውስጡ ይመራናል።

ትዕቢት፣ ጭፍን ጥላቻና ኃጢአት የእግዚአብሔርን እውነቶች ያግዳሉ፤ ይህም የእርሱ ጸጋ ወደ አእምሮአችንና የልብ ፍላጎታችን መንገድ እስኪከፍትላቸው ድረስ ነው። ጌታ ብቻውን ልብን ቃሉን ለመቀበልና ለማመን ሊከፍት ይችላል። በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን አለብን፤ ወደ እግዚአብሔር እንደ አባት መቅረብ የሚቻለው በአማላጁ ወልድ አማካኝነት ካልሆነ በስተቀር ሌላ መንገድ የለም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራንም ደረሰ። እነሆም፥ በዚያ የአንዲት ያመነች አይሁዳዊት ልጅ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፤ አባቱ ግን የግሪክ ሰው ነበረ። አማርኛ ENGNIV He came to Derbe and then to Lystra, where a disciple named Timothy lived, whose mother was a Jewess and a believer, bu… English BCV ካብኡ ጳውሎስ፥ ኣብ ደርቤንን ኣብ ልስጥራንን በፅሐ፤ ኣብኡ ኸዓ፥ ካብ ሓንቲ ኣይሁዳዊት ኣማኒት ሰበይትን፥ ካብ ሓደ ግሪካዊ ሰብኣይን ዝተወለደ፥ ጢሞቴዎስ ዝበሃል ደቀ መዝሙር ነበረ። ትግርኛ GAZBIB Phaawulos karaa isaa itti fufee mandara Derbee dhaqee, mandara Lisxiraattis darbe. Achi immoo Ximotewos kan jedhamu dar… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበጽሐ ሀገረ ደርቤን ወልስጥራን ወረከበ አሐደ ረድአ ዘስሙ ጢሞቴዎስ፤ ወእሙሰ አይሁዳዊት ወአምነት ወአቡሁሰ አረማዊ። giz GAZGAZ Phaawulos karaa isaa itti fufee mandara Derbee dhaqee, mandara Lisxiraattis darbe. Achi immoo Ximotewos kan jedhamu dar… Afaan Oromoo BCV aksum ካብኡ ጳውሎስ፥ ኣብ ደርቤንን ኣብ ልስጥራንን በፅሐ፤ ኣብኡ ኸዓ፥ ካብ ሓንቲ ኣይሁዳዊት ኣማኒት ሰበይትን፥ ካብ ሓደ ግሪካዊ ሰብኣይን ዝተወለደ፥ ጢሞቴዎስ ዝበሃል ደቀ መዝሙር ነበረ። ትግርኛ SWAHSUV Basi akafika Derbe na Listra, na hapo palikuwa na mwanafunzi mmoja jina lake Timotheo, mwana wa mwanamke Myahudi aliyea… Kiswahili