ስርቆት።
26 ቁጥሮች9አማርኛዘጸ 20:15
15“አትስረቅ።
ዘሌ 6:1-4
ዘሌ 19:11
11“ ‘አትስረቁ፥ አትካዱም፥ ከእናንተም እርስ በርሳችሁ ሐሰት አትነጋገሩ።
ዘዳ 5:19
19አትስረቅ።
ሆሴ 4:1-3
ማቴ 19:16-19
ማር 7:15-23
15ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም።
16የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ፡” አላቸው።
17ከሕዝቡ ዘንድ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ምሳሌውን ጠየቁት።
18እርሱም፦ “እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን?
19ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምና፤ መብልን ሁሉ እያጠራ፥” አላቸው።
20እርሱም አለ፦ “ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው።
21ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥
22ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤
23ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።”
ሉቃ 6:29-30
ኤፌ 4:28
28የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።