ወደ ኤፌሶን 4

AMHEVGአማርኛ31 ጥቅሶች3:44 አዳምጥ
አዳምጥ 3:44 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤

2በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤

3በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።

4በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤

5አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤

6ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።

7ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን።

8ስለዚህ፦ “ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ፡ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ፡” ይላል።

9ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፥ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው?

10ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው።

11እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤

12ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።

14እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥

15ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤

16ከእርሱም የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።

17እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።

18እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤

19ደንዝዘውም በመመኘት ርኵሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ።

20እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤

21በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤

22ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥

23በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥

24ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።

25ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።

26ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤

27በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።

28የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።

29ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።

30ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።

31መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።

32እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።

ማብራሪያ

4:1-6 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቶስ ወደ መንግሥቱና ወደ ክብሩ ለጠራቸው ሰዎች እንደሚገባ መመላለስ ከምንም ነገር በላይ በብርቱ የሚመከር ነው። በትሕትና፣ ለትዕቢት ተቃራኒ የሆነውን ትሑት መሆንን እንረዳለን። በየዋህነት ደግሞ፣ ሰውን ለማስቀየም ፈቃደኛ የማያደርግና በቀላሉ የማይናደድ ወይም የማይከፋ እጅግ ግሩም የሆነ የነፍስ ባሕርይ ነው። እኛ ራሳችን ይቅር ለማለት የሚያስቸግሩን ብዙ ነገሮች በውስጣችን እናገኛለንና፤ ስለዚህ በሌሎች ላይ ይቅር ለማለት ከባድ ነው የምንላቸውን ነገሮች ብናገኝ ልንደነቅ አይገባም። ሁሉም አማኞች ተስፋ የሚያደርጉበት አንድ ክርስቶስ አለ፤ ሁሉም የሚጠብቁትም አንድ ሰማይ አለ፤ ስለዚህ በአንድ ልብ ሊሆኑ ይገባል። ሁሉም ስለ ዓላማው፣ ስለ ፈጣሪው፣ ስለ ባሕርዩና ስለ ኃይሉ አንድ እምነት ነበራቸው። ሁሉም ስለ ሃይማኖት ታላላቅ እውነቶች አንድ ዓይነት ያምኑ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ጥምቀት፣ በውኃ ተጠምቀው ወደ ቤተ ክርስቲያን ተቀብለዋል፤ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስምም ነበር፤ ይህም የ'እንደገና መወለድ' ምልክት ነው። በሁሉም አማኞች ውስጥ እግዚአብሔር አብ በቅዱስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ እንደሚኖር ሁሉ፣ በመንፈሱና በልዩ ጸጋው አማካኝነት ይኖራል።

ኤፌሶን 4:7-16 ለእያንዳንዱ አማኝ እርስ በእርስ ለመተጋገዝ የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶታል፡፡ የተሰጠውም ሁሉ ክርስቶስ እንደተመቸው ለእያንዳንዱ ሰው ሊሰጥ ነው፡፡ እርሱ ለእነርሱ ተቀበለ፣ እርሱም ለእነርሱ የተትረፈረፉ ስጦታዎችንና ጸጋዎችን እንዲሰጣቸው ነው፤ በተለይም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ፡፡ ይህ ስጦታ የቃል እውቀት ብቻ ወይም ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ዝም ብሎ ማመን ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን እምነትንና መታዘዝን የሚያመጣ ነው፡፡ በክርስቶስ ሙላት አለ፣ ከዚያም ሙላት በእግዚአብሔር ምክር መሰረት ለእያንዳንዱ አማኝ አንድ መጠን ተሰጥቶታል፤ ነገር ግን ፍጹም ወደሆነው መጠን ወደ ሰማይ እስክንመጣ ድረስ አንደርስም፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች በዚህ ዓለም እስከሆኑ ድረስ ያድጋሉ፤ የክርስቲያንም ዕድገት ወደ ክርስቶስ ክብር ያመራል፡፡ አንድ ሰው በቦታው ላይ ለመሻሻል፣ እንዲሁም እንደ መጠኑ የተቀበለውን ሁሉ ለሌሎች መንፈሳዊ ጥቅም ለማዋል በተነሳሳ ቁጥር፣ በልቡ ውስጥ የእውነተኛ ፍቅርና በጎ አድራጎት ጸጋ ሰርጾበታል ብሎ በበለጠ እርግጠኝነት ሊያምን ይችላል፡፡

4:17-24 ሐዋርያው ኤፌሶናውያንን በጌታ በኢየሱስ ስም እና ስልጣን እንዲህ ሲል አሳሰባቸው፡ ወንጌልን ከተናዘዙ በኋላ፣ በከንቱ አስተሳሰቦችና ሥጋዊ ምኞቶች ይሄዱ እንደነበሩት ካልተለወጡት አሕዛብ መሆን የለባቸውም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6