መጽሐፍ ቅዱስ

19 ቁጥሮች17አማርኛ

ሉቃ 4:21

21እርሱም፦ “ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ፡” ይላቸው ጀመር።

ዮሐ 2:22

22ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።

ዮሐ 7:42

42ክርስቶስ ከዳዊት ዘር ዳዊትም ከነበረባት መንደር ከቤተ ልሔም እንዲመጣ መጽሐፍ አላለምን?” አሉ።

ዮሐ 13:18

18“ስለ ሁላችሁ አልናገርም፤ እኔ የመረጥኋቸውን አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ፦ ‘እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣብኝ’ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።

ዮሐ 17:12

12ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን በስምህ እኔ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም መጽሐፉም እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።

ዮሐ 19:28

28ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ፡ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፦ “ተጠማሁ” አለ።

ዮሐ 19:36-37

36ይህ የሆነ፦ “ከእርሱ አጥንት አይሰበርም፡” የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው።

37ደግሞም ሌላው መጽሐፍ፦ “የወጉትን ያዩታል” ይላል።

ዮሐ 20:9

9ከሙታን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው የሚለውን የመጽሐፉን ቃል ገና አላወቁም ነበርና።

ሐሥ 1:16

16“ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤

ሐሥ 8:32

32ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፥ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

ሮሜ 4:3

3መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።

ሮሜ 9:17

17መጽሐፍ ፈርዖንን፦ “ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ፡” ይላልና።

ገላ 3:8

8መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፦ “በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ፡” ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ።

1ኛ ጢሞ 5:18

18መጽሐፍ፦ “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፥” ደግሞ፦ “ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል፡” ይላልና።

ያዕ 2:8-9

8ነገር ግን መጽሐፍ፦ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡” እንደሚል የንጉሥን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤

9ለሰው ፊት ግን ብታደሉ ኃጢአትን ትሠራላችሁ፥ ሕግም እንደ ተላላፊዎች ይወቅሳችኋል።

ያዕ 4:5

5ወይስ መጽሐፍ፦ “በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል፡” ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?

2ኛ ጴጥ 1:20

20ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤