ትንሣኤ
46 ቁጥሮች16አማርኛኢዮ 14:12-15
ኢዮ 19:25-27
ዳዊ 16:9-10
ዳዊ 17:15
15እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።
ዳዊ 49:15
15ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና፡ ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል።
ኢሳ 25:8
8ሞትን ለዘላለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
ኢሳ 26:19
19ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።
ዳን 12:2-3
ማቴ 22:23-30
23በዚያን ቀን፦ “ትንሣኤ ሙታን የለም” የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ቀረቡ፥
24እንዲህም ብለው ጠየቁት፦ “መምህር ሆይ፥ ሙሴ አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ሲሞት ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፡ አለ።
25ሰባት ወንድማማች በእኛ ዘንድ ነበሩ፤ ፊተኛውም ሚስት አግብቶ ሞተ፥ ዘርም ስለሌለው ሚስቱን ለወንድሙ ተወለት፤
26እንዲሁ ደግሞ ሁለተኛው ሦስተኛውም፥ እስከ ሰባተኛው ድረስ።
27ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ሞተች።
28ሁሉ አግብተዋታልና በትንሣኤ ቀንስ፥ ከሰባቱ ለማናቸው ሚስት ትሆናለች?”
29ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።
30በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም።
ማቴ 24:31
31መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።”
ማቴ 25:1-13
1“በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።
2ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።
3ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤
4ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።
5ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
6እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
7በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።”
8“ሰነፎቹም ልባሞቹን፦ ‘መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን’ አሉአቸው።
9ልባሞቹ ግን መልሰው፦ ‘ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ’ አሉአቸው።
10ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ።
11“በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና፦ ‘ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን፡’ አሉ።
12እርሱ ግን መልሶ፦ ‘እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም’ አለ።
13ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
ማቴ 27:52-53
ሉቃ 14:14
14የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።”
ሉቃ 20:35-38
ዮሐ 5:21
21አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
ዮሐ 6:44
44የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።