የሉቃስ ወንጌል 20

AMHEVGአማርኛ45 ጥቅሶች5:39 አዳምጥ
አዳምጥ 5:39 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አንድ ቀንም ሕዝቡን በመቅደስ ሲያስተምር ወንጌልንም ሲሰብክላቸው፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ ቀረቡና፦

2“እስኪ ንገረን፤ እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ ወይስ ይህን ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” ብለው ተናገሩት።

3መልሶም እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፥ እናንተም ንገሩኝ፤

4የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረችን ወይስ ከሰው?”

5እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ፦ “ከሰማይ ብንል፣ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤

6ከሰው ብንል ግን ሕዝቡ ሁሉ ይወግሩናል፤ ዮሐንስ ነቢይ እንደ ነበረ ሁሉ ያምኑ ነበርና።” አሉ።

7መልሰውም፦ “ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም” አሉት።

8ኢየሱስም፦ “እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።

9ይህንም ምሳሌ ለሕዝቡ ይላቸው ጀመር፦ “አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፡ ለገበሬዎችም አከራይቶ ለብዙ ዘመን ወደ ሌላ አገር ሄደ።

10በጊዜውም ከወይኑ አትክልት ፍሬ እንዲሰጡት አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎች ላከ፤ ገበሬዎቹ ግን ደበደቡት ባዶውንም ሰደዱት።

11ጨምሮም ሌላውን ባሪያ ላከ፤ እነርሱም ያን ደግሞ ደበደቡት አዋርደውም ባዶውን ሰደዱት።

12ጨምሮም ሦስተኛውን ላከ፤ እነርሱም ይህን ደግሞ አቍሰለው አወጡት።

13የወይኑም አትክልት ጌታ፦ ‘ምን ላድርግ? የምወደውን ልጄን እልካለሁ፤ ምናልባት እርሱን አይተው ያፍሩታል፡’ አለ።

14“ገበሬዎቹ ግን አይተውት እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ፦ ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ርስቱ ለእኛ እንዲሆን ኑ እንግደለው፡’ አሉ።

15ከወይኑም አትክልት ወደ ውጭ አውጥተው ገደሉት። እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋቸዋል?

16ይመጣል፡ እነዚህንም ገበሬዎች ያጠፋል፥ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል።” ይህንም በሰሙ ጊዜ፦ “ይህስ አይሁን፡” አሉ።

17እርሱ ግን ወደ እነርሱ ተመልክቶ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ’ ተብሎ የተጻፈው ይህ ምንድር ነው?

18በዚያም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይቀጠቀጣል፤ የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ይፈጨዋል።”

19የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።

20ሲጠባበቁም ወደ ገዢ ግዛትና ሥልጣን አሳልፈው እንዲሰጡት ጻድቃን መስለው በቃሉ የሚያጠምዱትን ሸማቂዎች ሰደዱበት።

21ጠይቀውም፦ “መምህር ሆይ፥ እውነትን እንድትናገርና እንድታስተምር ለሰው ፊትም እንዳታደላ እናውቃለን፥ በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ ታስተምራለህ እንጂ፤

22ለቄሣር ግብር ልንሰጥ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም?” አሉት።

23እርሱ ግን ተንኰላቸውንም ተመልክቶ፦ “ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ? አንድ ዲናር አሳዩኝ፤

24መልኩ ጽሕፈቱስ የማን ነው?” አላቸው። መልሰውም፦ “የቄሣር ነው፡” አሉት።

25እርሱም፦ “እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ፡” አላቸው።

26በሕዝቡም ፊት በቃሉ ሊያጠምዱት አልቻሉም በመልሱም እየተደነቁ ዝም አሉ።

27ትንሣኤ ሙታንንም የሚክዱ ከሰዱቃውያን አንዳንዶቹ ቀርበው ጠየቁት፥

28እንዲህ ሲሉ፦ “መምህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ሚስት ያለችው የአንድ ሰው ወንድም ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፡ ብሎ ጻፈልን።

29እንግዲያስ ሰባት ወንድማማች ነበሩ፤ የፊተኛውም ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤

30ሁለተኛውም አገባት፥ ሦስተኛውም፥ እንዲሁም ሰባቱ ደግሞ ልጅ ሳይተዉ ሞቱ።

32“ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ደግሞ ሞተች።

33እንግዲህ ሰባቱ አግብተዋታልና ሴቲቱ በትንሣኤ ከእነርሱ ለማንኛቸው ሚስት ትሆናለች?”

34ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “የዚህ ዓለም ልጆች ያገባሉ ይጋባሉም፥

35ያን ዓለምና ከሙታን ትንሣኤ ሊያገኙ የሚገባቸው እነዚያ ግን አያገቡም አይጋቡምም፥ እንደ መላእክት ናቸውና፥

36ሊሞቱም ወደ ፊት አይቻላቸውም፥ የትንሣኤም ልጆች ስለ ሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።

37ሙታን እንዲነሡ ግን ሙሴ ደግሞ በቍጥቋጦው ዘንድ ጌታን፦ ‘የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ’ በማለቱ አስታወቀ፤

38ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።”

39ከጻፎችም አንዳንዶቹ መልሰው፦ “መምህር ሆይ፥ መልካም ተናገርህ፡” አሉት።

40ወደ ፊትም አንድ ነገር ስንኳ ሊጠይቁት አልደፈሩም።

41እንዲህም አላቸው፦ “ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው፡ እንዴት ይላሉ?

42ዳዊትም ራሱ በመዝሙራት መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ ‘ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፡’ አለው።

44እንግዲህ ዳዊት፦ ‘ጌታ’ ብሎ ይጠራዋል፥ እንዴትስ ልጁ ይሆናል?”

45ሕዝቡም ሁሉ ሲሰሙ ደቀ መዛሙርቱን አለ፦

46“ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ፥ በገበያም ሰላምታ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤

47የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ፥ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”

ማብራሪያ

ሉቃስ 20:1-8

ሰዎች ብዙውን ጊዜ የመገለጥን ማስረጃዎችና የወንጌልን እውነት ለመመርመር ያስመስላሉ፤ በእርግጥ ግን ለራሳቸው አለማመንና አለመታዘዝ ሰበብ የሚፈልጉ ብቻ ናቸው። ክርስቶስም እነዚህን ካህናትና ጸሐፍት ስለ ዮሐንስ ጥምቀት በቀላል ጥያቄ መለሰላቸው፤ ይህም ተራው ሕዝብ ሊመልሰው የሚችል ነበር። ሁሉም ከሰማይ እንደሆነ ያውቁ ነበር፤ በውስጡም ምንም ምድራዊ ዝንባሌ አልነበረውም። ያላቸውን እውቀት የሚቀብሩ ሰዎች በትክክል ተጨማሪ እውቀት ይከለከላሉ። ዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ እንደሆነ እያወቁ በእርሱ ያላመኑትንና የሚያውቁትንም እውነት ያልተናዘዙትን ሰዎች ስለ ስልጣኑ መልስ ለመስጠት ክርስቶስ እምቢ ማለቱ ፍትሐዊ ነበር።

20:9-19 ክርስቶስ ይህን ምሳሌ የተናገረው ስልጣኑን ላለመቀበል በቆረጡ ሰዎች ላይ ነበር፤ ማስረጃው እጅግ ብዙ ቢሆንም እንኳ። በእግዚአብሔር ላይ ባላቸው ጥላቻ፣ አገልግሎቱንም በመጥላት፣ ያለ ምንም ገደብ እንደ ምኞታቸው ለመኖር በመሻት፣ ነቢያትን የገደሉትንና ክርስቶስን የሰቀሉትን አይሁድን የሚመስሉ ስንትና ስንት ሰዎች አሉ! የእግዚአብሔር ቃል የተቸራቸው ሁሉ፣ የተሰጣቸውን ጥቅም በአግባቡ እንዲጠቀሙበት ይጠንቀቁ። ወልድን ለሚጥሉ (ለሚከዱትም)፣ እርሱን እንደሚያከብሩ እየተናገሩ (እየመሰሉ) ፍሬን በወቅቱ ለማይሰጡትም ሁሉ፣ የመጨረሻው ፍርድ እጅግ አስከፊ ይሆናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV One day as he was teaching the people in the temple courts and preaching the gospel, the chief priests and the teachers… English BCV ሓደ መዓልቲ ኢየሱስ፥ ኣብ ቤተ መቕደስ ንህዝቢ ኽምህርን፥ ወንጌል ክሰብኽን እንተሎ፥ ሊቃነ ካህናትን መምህራን ሕግን፥ ምስ ዓበይቲ ህዝቢ ኾይኖም ናብኡ መፂኦም፥ ትግርኛ GAZBIB Gaaf tokko Yesus mana qulqullummaa keessatti namoota barsiisaa, wangeelas lallabaa utuu jiruu, luboonni warri angafoonn… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ አሐተ ዕለተ እንዘ ይሜህሮሙ ለሕዝብ በምኵራብ ወይነግሮሙ ቆሙ ላዕሌሁ ሊቃነ ካህናት ወጸሐፍት ወረበናት። giz GAZGAZ Gaaf tokko Yesus mana qulqullummaa keessatti namoota barsiisaa, wangeelas lallabaa utuu jiruu, luboonni warri angafoonn… Afaan Oromoo BCV aksum ሓደ መዓልቲ ኢየሱስ፥ ኣብ ቤተ መቕደስ ንህዝቢ ኽምህርን፥ ወንጌል ክሰብኽን እንተሎ፥ ሊቃነ ካህናትን መምህራን ሕግን፥ ምስ ዓበይቲ ህዝቢ ኾይኖም ናብኡ መፂኦም፥ ትግርኛ AMHNIV አንድ ቀን ኢየሱስ ሕዝቡን በቤተ መቅደስ ሲያስተምርና ወንጌልን ሲሰብክ የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና ሽማግሌዎች ተሰብስበው ወደ እርሱ መጡ፤ አማርኛ SWAHSUV Ikawa siku moja, alipokuwa akiwafundisha watu hekaluni, na kuihubiri habari njema, wakuu wa makuhani na waandishi pamoj… Kiswahili