ልብ

30 ቁጥሮች25አማርኛ

ምሳ 4:23

23አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።

ምሳ 27:19

19ፊት በውኃ ላይ ለፊት እንደሚታይ፥ እንዲሁ የሰው ልብ ለሰው ይታያል።

1ኛ ጴጥ 3:3-4

3ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥

4ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።

ኤር 17:9-10

9የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?

10እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።

ዳዊ 20:4

4እንደ ልብህ ይስጥህ፡ ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።

ኤር 29:13

13እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።

ምሳ 3:3-4

3ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው።

4በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም፡ ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ።

ምሳ 3:5-6

5በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤

6በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።

ዳዊ 51:10

10አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።

1ኛ ሳሙ 16:7

7እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል፡ አለው።

ማቴ 22:37

37ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።

ዳዊ 37:4

4በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።

2ኛ ቆሮ 9:7

7እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።

ምሳ 17:22

22ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፤ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች።

ምሳ 3:1-2

1ልጄ ሆይ፥ ሕጌን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።

2ብዙ ዘመናትና ረጅም ዕድሜ፡ ሰላምም ይጨምሩልሃልና።

ምሳ 10:8

8በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝን ይቀበላል፤ በከንፈሩ የሚሰንፍ ግን ይወድቃል።

ዳዊ 31:24

24በእግዚአብሔር የምታምኑ ሁላችሁ፥ በርቱ ልባችሁም ይጥና።

ዳዊ 119:10

10በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።

ዳዊ 19:14

14አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ፡ በፊትህ ያማረ ይሁን።

ኢያ 22:5

5ብቻ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን ታደርጉ ዘንድ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ መንገዱንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጠጉ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩ ዘንድ እጅግ ተጠንቀቁ።

ዳዊ 90:12

12በልብ ጥበብን እንድንማር፥ ቀኝህን እንዲህ አስታውቀን።

ማር 11:23

23እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ቢል ይሆንለታል።

ዳዊ 119:111

111የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘላለም ወረስሁ።

ዳዊ 119:2

2ምስክሩን የሚፈልጉ፥ በፍጹም ልብ የሚሹት ምስጉኖች ናቸው፤

ዳዊ 119:7

7አቤቱ፥ የጽድቅህን ፍርድ ስማር፡ በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።