ራእይ ዮሃንስ 6

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:36 አዳምጥ
አዳምጥ 3:36 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በጉም ከሰባቱ ማኅተሞች የመጀመሪያውን ሲፈታ አየሁ፤ ከዚያም ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን አንዱ፣ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ “ና!” ሲል ሰማሁ።

2እኔም ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ ነጭ ፈረስ ቆሞ ነበር፤ ተቀምጦበት የነበረውም ቀስት ይዞ ነበር፤ አክሊልም ተሰጠው፤ እርሱም እንደ ድል አድራጊ ድል ለመንሣት ወጣ።

3በጉ ሁለተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ ሁለተኛው ሕያው ፍጡር፣ “ና!” ሲል ሰማሁ።

4ሌላ ፍም የሚመስል ቀይ ፈረስም ወጣ፤ ተቀምጦበት የነበረው ሰላምን ከምድር ላይ እንዲወስድና ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ለማድረግ ሥልጣን ተሰጠው፤ ትልቅም ሰይፍ ተሰጠው።

5በጉ ሦስተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር፣ “ና!” ሲል ሰማሁ። እኔም ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ ጥቍር ፈረስ ቆሞ አየሁ፤ ተቀምጦበት የነበረውም በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር።

6ከዚያም ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን መካከል፣ “አንድ እርቦ ስንዴ ለአንድ ቀን ደመወዝ፤ ሦስት እርቦ ገብስም ለአንድ ቀን ደመወዝ ይሁን፤ ዘይቱንና የወይን ጠጁን አትጒዳ” የሚል ድምፅ ሰማሁ።

7በጉ አራተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ አራተኛው ሕያው ፍጡር፣ “ና!” ሲል ሰማሁ።

8እኔም ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ ግራጫ ፈረስ ቆሞ አየሁ፤ ተቀምጦበት የነበረው ስሙ ሞት ነበር፤ ሲኦልም ከኋላ ይከተለው ነበር። እነርሱም በሰይፍ፣ በራብ፣ በመቅሠፍትና በምድር አራዊት እንዲገድሉ በምድር አንድ አራተኛ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

9አምስተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁትም ምስክርነት የታረዱትን ሰዎች ነፍሶች ከመሠዊያው በታች አየሁ።

10እነርሱም በታላቅ ድምፅ፣ “ሁሉን የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፤ እስከ መቼ አትፈርድም? እስከ መቼስ ደማችንን በምድር በሚኖሩት ላይ አትበቀልም?” አሉ።

11ከዚያም ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ ወደ ፊት እንደ እነርሱ የሚገደሉ የአገልጋይ ባልንጀሮቻቸውና ወንድሞቻቸው ቊጥር እስኪሞላ ድረስ ጥቂት ጊዜ እንዲታገሡ ተነገራቸው።

12ስድስተኛውን ማኅተም ሲፈታ ተመለከትሁ፤ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሓይም እንደ ማቅ ጠቈረች። ጨረቃም በሙሉ እንደ ደም ቀላች፤

13የበለስ ዛፍ በብርቱ ነፋስ ስትወዛወዝ ያልበሰለው ፍሬ ከእርሷ እንደሚረግፍ፣ የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ረገፉ።

14ሰማይ እንደ ጥቅልል መጽሐፍ ተጠቅልሎ ዐለፈ፤ ተራሮችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወገዱ።

15ከዚህ በኋላ የምድር ነገሥታትና ገዦች፣ የጦር መኰንኖች፣ ሀብታሞች፣ ብርቱዎች፣ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለት ውስጥ ተሸሸጉ፤

16ተራሮቹንና ዐለቶቹንም፣ “በላያችን ውደቁ፤ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቊጣ ሰውሩን፤

17ታላቁ የቊጣቸው ቀን መጥቶአልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል?” አሏቸው።

ማብራሪያ

ራእይ 6:1-8

በግ የሆነው ክርስቶስ የመጀመሪያውን ማኅተም ሲፈታ ምን እንደታየ እንመልከት። ነጭ ፈረስ የሚጋልብ ፈረሰኛ። ይህ ነጭ ፈረስ በመውጣቱ፣ የሰላም ዘመን፣ ወይም የክርስትና ሃይማኖት የመጀመሪያ ዕድገት የታሰበ ይመስላል፤ ሰማያዊ መስራቹ ሐዋርያቱን ሁሉንም ሕዝቦች እንዲያስተምሩ በላከበት ጊዜ፣ ‹እነሆ! እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ› በማለት የገባውን ቃል እንደሚያረጋግጥ፣ በንጽህና መውጣቱን ያሳያል። መለኮታዊው ሃይማኖት ዘውድ ደፍሮ ይወጣል፣ መለኮታዊ ሞገስ በላዩ ላይ ያረፈበት፣ በመንፈሳዊ መንገድ ጠላቶቹን የታጠቀ፣ በመጨረሻም ድል አድራጊ እንዲሆን የታሰበ ነው።

ሁለተኛውን ማኅተም ሲፈታ ቀይ ፈረስ ታየ፤ ይህ ደግሞ አጥፊ ፍርዶችን ያመለክታል። የጦርነትና የስደት ሰይፍ አስከፊ ፍርድ ነው፤ ከምድር ላይ ታላላቅ በረከቶች አንዱ የሆነውን ሰላምን ይወስዳል፤ እርስ በእርሳቸው መዋደድና መረዳዳት የነበረባቸው ሰዎች እርስ በእርሳቸው ለመገዳደል ተነሱ። እንደነዚህ ያሉት ትዕይንቶች ንጹህ ከሆነው የመጀመሪያ ክርስትና ዘመን በኋላም ተከስተዋል፤ የክርስትና መሪዎች፣ ፍቅርንና የሰላምን ገመድ ችላ ብለው፣ በመካከላቸው ተከፋፍለው፣ ወደ ሰይፍ ተማጽነው፣ በኃጢአት ውስጥ ተጠመዱ።

ሦስተኛውን ማኅተም ሲፈታ ጥቁር ፈረስ ታየ፤ ይህ ቀለም ሐዘንንና ሰቆቃን፣ ጨለማንና ድንቁርናን ያመለክታል። የተቀመጠበትም በእጁ ቀንበር ይዞ ነበር። በደቀ መዛሙርቱ ላይ የአጉል እምነት ሥርዓቶችን ቀንበር ለመጫን ሙከራዎች ተደርገዋል። የክርስትና ወንዝ ከንጹህ ምንጩ በራቀ መጠን፣ እየበሰበሰ ሄደ። ይህ ጥቁር ፈረስ በሚገፋበት ጊዜ፣ የሕይወት ፍላጎቶች በከፍተኛ ዋጋ የሚሸጡ ሲሆን፣ ይበልጥ ውድ የሆኑት ነገሮች ግን አይጎዱም። በትንቢታዊ አነጋገር፣ እነዚህ ነገሮች የሰዎችን ነፍሳት ለዘላለም ሕይወት የሚያቆይ የሃይማኖታዊ እውቀት ምግብን ያመለክታሉ፤ እንደዚህ ያለውን እንድንገዛ በኢሳያስ 55:1 ተጋብዘናል። ነገር ግን ጥቁሩ ፈረስ በሚያመለክተው የድንቁርናና የአጉል እምነት ጨለማ ደመና በክርስትናው ዓለም ላይ ሲሰራጭ፣ የእውነተኛው ሃይማኖት እውቀትና ተግባር ብርቅ ሆነ። ሕዝብ መንፈሳዊ ምግባሩን ሲጠላ፣ እግዚአብሔር የዕለት እንጀራቸውን ማሳጣት ፍትሐዊ ሊሆን ይችላል። የእንጀራ ራብ አስከፊ ፍርድ ነው፤ ነገር ግን የቃሉ ራብ ከዚህ የከፋ ነው።

አራተኛውን ማኅተም ሲፈታ፣ ሌላ ፈረስ ታየ፣ ቀለሙም የገረጣ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ “መጥተህ እይ፡” ሲል ሰማሁ። አማርኛ ENGNIV I watched as the Lamb opened the first of the seven seals. Then I heard one of the four living creatures say in a voice… English BCV እቲ በጊዕ፥ ካብቲ ሸውዓተ ማሕተማት፥ ነቲ ቐዳማይ ክፈትሖ እንተሎ ረአኹ። ሓደ ኻብቶም ኣርባዕተ እንስሳ ድማ፥ ከም ነጐድጓድ ብዝመስል ድምፂ፥ “ነዓ ረአ” እንትብል ሰማዕኹ። ትግርኛ GAZBIB Kana booddee hoolichi mallattoowwan torban keessaa isa tokko utuu banuu nan arge; uumama lubbuu qaban arfan keessaa imm… Afaan Oromoo BCV GIZ ወሶበ ፈትሐ ዝክቱ በግዕ አሐደ ማኅተመ እምነ ሰብዐቱ ማኅተሚሃ ይቤለኒ አሐዱ እምነ እልክቱ አርባዕቱ እንስሳሁ፦ “ነዓ ርኢ”፤ ወሰማዕኩ ቃሎ ከመ ነጐድጓድ። giz GAZGAZ Kana booddee hoolichi mallattoowwan torban keessaa isa tokko utuu banuu nan arge; uumama lubbuu qaban arfan keessaa imm… Afaan Oromoo BCV aksum እቲ በጊዕ፥ ካብቲ ሸውዓተ ማሕተማት፥ ነቲ ቐዳማይ ክፈትሖ እንተሎ ረአኹ። ሓደ ኻብቶም ኣርባዕተ እንስሳ ድማ፥ ከም ነጐድጓድ ብዝመስል ድምፂ፥ “ነዓ ረአ” እንትብል ሰማዕኹ። ትግርኛ SWAHSUV Kisha nikaona napo MwanaKondoo alipofungua moja ya zile muhuri saba, nikasikia mmoja wa wale wenye uhai wanne akisema, … Kiswahili