ትንቢተ ኢሳይያስ 61

AMHEVGአማርኛ11 ጥቅሶች2:31 አዳምጥ
አዳምጥ 2:31 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።

2የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤

3እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።

4ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ይሠራሉ።

5መጻተኞችም ቆመው በጎቻችሁን ያሰማራሉ፥ ሌሎች ወገኖችም አራሾችና ወይን ጠባቂዎች ይሆኑላችኋል።

6እናንተ ግን የእግዚአብሔር ካህናት ትባላላችሁ፥ ሰዎቹም፡ የአምላካችን አገልጋዮች፡ ብለው ይጠሩአችኋል፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፥ በክብራቸውም ትመካላችሁ።

7በእፍረታችሁ ፋንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፥ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፈንታችሁ ደስ ይላቸዋል፤ ስለዚህ በምድራቸው ሁሉ እጥፍ ይገዛሉ፥ የዘላለምም ደስታ ይሆንላቸዋል።

8እኔ እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።

9ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ይገነዘባል።

10አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።

11ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፥ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፥ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል።

ማብራሪያ

61:1-3 ነቢያት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በየጊዜው በእነርሱ ላይ ነበር፤ ምን እንደሚናገሩ ያስተምራቸው እንዲሁም እንዲናገሩ ያደርጋቸው ነበር። ክርስቶስ ግን ለተሾመበት ሥራ፣ እንደ ሰው፣ ብቃት እንዲኖረው ለማድረግ መንፈሱ ሁልጊዜ ያለ ልክ ነበረው። ድሆች ወንጌልን ለመቀበል በአብዛኛው የተሻለ ዝግጁነት አላቸው፣ ያዕ 2:5፤ ሲቀበሉትም በትሕትና ሲሆን ብቻ ሊጠቅመን ይችላል። በመንፈስ ለድሆች፣ ክርስቶስ "የዋሆች ብፁዓን ናቸው" ብሎ ሲናገር የምሥራች ሰበከላቸው። የክርስቶስ ስርየት ተቀባይነት አለው። በውስጣችን ባለው የኃጢአት የበላይነት፣ በሰይጣን ሥልጣን ሥር ታስረናል፤ ነገር ግን ወልድ፣ በመንፈሱ፣ ሙሉ በሙሉ ነፃ ሊያወጣን ዝግጁ ነው፤ ያን ጊዜም በእውነት ነፃ እንሆናለን። ኃጢአትና ሰይጣን ሊጠፉ ተወስኖ ነበር፤ ክርስቶስም በመስቀሉ ላይ በእነርሱ ላይ አሸነፈ። ነገር ግን እነዚህን አቅርቦቶች የሚቃወሙ የሰው ልጆች እንደ ጠላት ይያዛሉ። ክርስቶስ አጽናኝ ሊሆን ነበር፣ እንደዚያውም ነው። የሚያዝኑትን ሁሉ፣ መጽናናትንም ከእርሱ እንጂ ከዓለም የማይፈልጉትን ሊያጽናና ተልኳል። እርሱ ይህን ሁሉ ለሕዝቡ ያደርጋል፣ የጽድቅ ፍሬዎችን ያበዙ ዘንድ፣ እንደ እግዚአብሔር የተተከሉ ቅርንጫፎች ሆነው። የእግዚአብሔር ምሕረት፣ የክርስቶስ ስርየት፣ የጸጋውም ወንጌል ራሳቸውን የቻሉትንና ትዕቢተኞችን አይጠቅማቸውም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The Spirit of the Sovereign Lord is on me, because the Lord has anointed me to preach good news to the poor. He has sen… English BCV ናይ ጐይታ እግዚኣብሄር መንፈስ፥ ኣብ ልዕለይ እዩ፤ ንድኻታት ብስራት ክሰብኽ፥ እግዚኣብሄር ቀቢኡኒ እዩሞ። ንስቡራት ልቢ ኽፅግን፥ ንምሩኻት ሓርነት፥ ንእሱራት ከዓ ምፍታሕ፥ ክእውጅ ለኣኸኒ። ትግርኛ GAZBIB Hafuurri Waaqayyo gooftaa ana irra jira, sagalee misraachoo warra gadadamootti akkan himuuf, Waaqayyo na dibeera; warra… Afaan Oromoo BCV GIZ መንፈሰ እግዚአብሔር ላዕሌየ በእንቲአሁ ዘቀብአኒ ኣስተፈሥሖሙ ለነዳያን ፈነወኒ፤ ወእፈውሶሙ ለቍሱላነ ልብ፤ ወእስብክ ግዕዛነ ለፂዉዋን ወይርአዩ ዕዉራን። giz GAZGAZ Hafuurri Waaqayyo gooftaa ana irra jira, sagalee misraachoo warra gadadamootti akkan himuuf, Waaqayyo na dibeera; warra… Afaan Oromoo BCV aksum ናይ ጐይታ እግዚኣብሄር መንፈስ፥ ኣብ ልዕለይ እዩ፤ ንድኻታት ብስራት ክሰብኽ፥ እግዚኣብሄር ቀቢኡኒ እዩሞ። ንስቡራት ልቢ ኽፅግን፥ ንምሩኻት ሓርነት፥ ንእሱራት ከዓ ምፍታሕ፥ ክእውጅ ለኣኸኒ። ትግርኛ AMHNIV የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች የምሥራች እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛል። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮ… አማርኛ SWAHSUV Roho ya Bwana MUNGU i juu yangu; kwa sababu Bwana amenitia mafuta niwahubiri wanyenyekevu habari njema; amenituma ili k… Kiswahili