ትንቢተ ኢሳይያስ 61

AMHNIVአማርኛ11 ጥቅሶች2:48 አዳምጥ
አዳምጥ 2:48 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች የምሥራች እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛል። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል፤

2የተወደደውን የእግዚአብሔርን ዓመት፣ የአምላካችንንም የበቀል ቀን እንዳውጅ፣ የሚያለቅሱትን ሁሉ እንዳጽናና ልኮኛል፤

3በጽዮን ያዘኑትን እንዳረጋጋ፣ በዐመድ ፈንታ፣ የውበት አክሊል እንድደፋላቸው፣ በልቅሶ ፈንታ፣ የደስታ ዘይት በራሳቸው ላይ እንዳፈስላቸው፣ በትካዜ መንፈስ ፈንታ፣ የምስጋና መጐናጸፊያ እንድደርብላቸው ልኮኛል፤ እነርሱም የክብሩ መግለጫ እንዲሆኑ፣ እግዚአብሔር የተከላቸው፣ የጽድቅ ዛፎች ተብለው ይጠራሉ።

4የጥንት ፍርስራሾችን መልሰው ይሠራሉ፤ በቀድሞ ጊዜ የወደሙትን መልሰው ያቆማሉ፤ ከብዙ ትውልድ በፊት የወደሙትን ፍርስራሽ ከተሞች እንደ ገና ይሠራሉ።

5መጻተኞች የበግ መንጎቻችሁን ያግዳሉ፤ ባዕዳን በዕርሻችሁና በወይን ተክል ቦታችሁ ላይ ይሠሩላችኋል።

6እናንተም የእግዚአብሔር ካህናት ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤ የአምላካችን ባሮች ትባላላችሁ፤ የመንግሥታትን ሀብት ትመገባላችሁ፤ በብልጽግናቸውም ትኰራላችሁ።

7ሕዝቤ በኀፍረታቸው ፈንታ፣ ዕጥፍ ይቀበላሉ፤ በውርደታቸው ፈንታ፣ በርስታቸው ደስ ይላቸዋል፤ የምድራቸውንም ዕጥፍ ርስት ይወርሳሉ፤ ዘላለማዊ ደስታም የእነርሱ ይሆናል።

8“እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን ስለምወድ፣ ዝርፊያንና በደልን እጠላለሁ፤ በታማኝነቴም የሚገባቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።

9ዘሮቻቸው በመንግሥታት፣ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ፤ የሚያዩአቸውም ሁሉ፣ እግዚአብሔር የባረካቸው ሕዝብ እንደሆኑ ያውቃሉ።

10በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፤ ነፍሴ በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች፤ ሙሽራ ራሱን እንደሚያሳምር፣ ሙሽራዪቱም በዕንቆቿ እንደምታጌጥ፣ የድነትን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።

11ምድር ቡቃያ እንደምታበቅል፣ የተክል ቦታ ችግኝ እንደሚያፈላ፣ ጌታ እግዚአብሔርም በመንግሥታት ሁሉ ፊት፣ ጽድቅንና ምስጋናን ያበቅላል።

ማብራሪያ

61:1-3 ነቢያት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በየጊዜው በእነርሱ ላይ ነበር፤ ምን እንደሚናገሩ ያስተምራቸው እንዲሁም እንዲናገሩ ያደርጋቸው ነበር። ክርስቶስ ግን ለተሾመበት ሥራ፣ እንደ ሰው፣ ብቃት እንዲኖረው ለማድረግ መንፈሱ ሁልጊዜ ያለ ልክ ነበረው። ድሆች ወንጌልን ለመቀበል በአብዛኛው የተሻለ ዝግጁነት አላቸው፣ ያዕ 2:5፤ ሲቀበሉትም በትሕትና ሲሆን ብቻ ሊጠቅመን ይችላል። በመንፈስ ለድሆች፣ ክርስቶስ "የዋሆች ብፁዓን ናቸው" ብሎ ሲናገር የምሥራች ሰበከላቸው። የክርስቶስ ስርየት ተቀባይነት አለው። በውስጣችን ባለው የኃጢአት የበላይነት፣ በሰይጣን ሥልጣን ሥር ታስረናል፤ ነገር ግን ወልድ፣ በመንፈሱ፣ ሙሉ በሙሉ ነፃ ሊያወጣን ዝግጁ ነው፤ ያን ጊዜም በእውነት ነፃ እንሆናለን። ኃጢአትና ሰይጣን ሊጠፉ ተወስኖ ነበር፤ ክርስቶስም በመስቀሉ ላይ በእነርሱ ላይ አሸነፈ። ነገር ግን እነዚህን አቅርቦቶች የሚቃወሙ የሰው ልጆች እንደ ጠላት ይያዛሉ። ክርስቶስ አጽናኝ ሊሆን ነበር፣ እንደዚያውም ነው። የሚያዝኑትን ሁሉ፣ መጽናናትንም ከእርሱ እንጂ ከዓለም የማይፈልጉትን ሊያጽናና ተልኳል። እርሱ ይህን ሁሉ ለሕዝቡ ያደርጋል፣ የጽድቅ ፍሬዎችን ያበዙ ዘንድ፣ እንደ እግዚአብሔር የተተከሉ ቅርንጫፎች ሆነው። የእግዚአብሔር ምሕረት፣ የክርስቶስ ስርየት፣ የጸጋውም ወንጌል ራሳቸውን የቻሉትንና ትዕቢተኞችን አይጠቅማቸውም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገ… አማርኛ ENGNIV The Spirit of the Sovereign Lord is on me, because the Lord has anointed me to preach good news to the poor. He has sen… English BCV ናይ ጐይታ እግዚኣብሄር መንፈስ፥ ኣብ ልዕለይ እዩ፤ ንድኻታት ብስራት ክሰብኽ፥ እግዚኣብሄር ቀቢኡኒ እዩሞ። ንስቡራት ልቢ ኽፅግን፥ ንምሩኻት ሓርነት፥ ንእሱራት ከዓ ምፍታሕ፥ ክእውጅ ለኣኸኒ። ትግርኛ GAZBIB Hafuurri Waaqayyo gooftaa ana irra jira, sagalee misraachoo warra gadadamootti akkan himuuf, Waaqayyo na dibeera; warra… Afaan Oromoo BCV GIZ መንፈሰ እግዚአብሔር ላዕሌየ በእንቲአሁ ዘቀብአኒ ኣስተፈሥሖሙ ለነዳያን ፈነወኒ፤ ወእፈውሶሙ ለቍሱላነ ልብ፤ ወእስብክ ግዕዛነ ለፂዉዋን ወይርአዩ ዕዉራን። giz GAZGAZ Hafuurri Waaqayyo gooftaa ana irra jira, sagalee misraachoo warra gadadamootti akkan himuuf, Waaqayyo na dibeera; warra… Afaan Oromoo BCV aksum ናይ ጐይታ እግዚኣብሄር መንፈስ፥ ኣብ ልዕለይ እዩ፤ ንድኻታት ብስራት ክሰብኽ፥ እግዚኣብሄር ቀቢኡኒ እዩሞ። ንስቡራት ልቢ ኽፅግን፥ ንምሩኻት ሓርነት፥ ንእሱራት ከዓ ምፍታሕ፥ ክእውጅ ለኣኸኒ። ትግርኛ SWAHSUV Roho ya Bwana MUNGU i juu yangu; kwa sababu Bwana amenitia mafuta niwahubiri wanyenyekevu habari njema; amenituma ili k… Kiswahili