ትንቢተ ኢሳይያስ 62

AMHEVGአማርኛ11 ጥቅሶች2:20 አዳምጥ
አዳምጥ 2:20 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፥ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።

2አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ፤ የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ።

3በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል፥ በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።

4ከእንግዲህ ወዲህ፦ የተተወች፡ አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፦ ውድማ፡ አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፦ ደስታዬ የሚኖርባት፡ ትባያለሽ፥ ምድርሽም፦ ባል ያገባች፡ ትባላለች።

5ጕልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፥ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል፤ ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።

6ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ጕበኞችን በቅጥርሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንና ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምታሳስቡ፥ ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ።

8እግዚአብሔር፦ ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፥ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም፤

9ነገር ግን የሰበሰቡት ይበሉታል፥ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፥ ያከማቹትም በመቅደሴ አደባባይ ላይ ይጠጡታል፡ ብሎ በቀኙና በኃይሉ ክንድ ምሎአል።

10እለፉ፥ በበሮች በኩል እለፉ፤ የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፤ አዘጋጁ፥ ጐዳናውን አዘጋጁ፥ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፤ ለአሕዛብም ዓላማ አንሡ።

11እነሆ፥ እግዚአብሔር ለምድር ዳርቻ አዋጅ እንዲህ ብሎ ነግሮአል፦ ለጽዮን ልጅ፦ እነሆ፥ መድኃኒትሽ ይመጣል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር ሥራውም በፊቱ አለ፡ በሉአት።

12እግዚአብሔር፦ የተቤዣቸው፥ የተቀደሰ ሕዝብ፡ ብለው ይጠሩአቸዋል፤ አንቺም፦ የተፈለገች ያልተተወችም ከተማ፡ ትባያለሽ።

ማብራሪያ

62:1-5 የእግዚአብሔር ልጅ በዚህ ስፍራ የማይነጥፍ ፍቅሩን እና በየትኛውም ፈተናና ችግር ውስጥ ስለቤተ ክርስቲያኑ መማለዱን ያረጋግጥላታል። እርሷም በአዲስ ስም፣ ከቶም ተጠርታበት የማታውቀውን ደስ የሚያሰኝ ስም ትጠራለች። ወንጌል ከመሰበኩ በፊት በዓለም ላይ የነበረው የእውነተኛው ሃይማኖት ሁኔታ ማንም እውነተኛ ትኩረት የሰጠው አይመስልም ነበር። እግዚአብሔር ግን በጸጋው ቤተ ክርስቲያኑን ደስታው እንድትሆን የሚያደርጋትን ነገር በእርሷ ውስጥ አከናውኗል። ከዚህም በመነሳት ለቅድስና የሚያነሳሱ ምክንያቶችን እንማር። ጌታ በእኛ ደስ ከተሰኘ፣ እኛም በአገልግሎቱ ደስ ልንሰኝ ይገባል።

62:6-9 የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሕዝብ ጸሎተኛ ሕዝብ መሆን አለበት።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV For Zion's sake I will not keep silent, for Jerusalem's sake I will not remain quiet, till her righteousness shines out… English BCV ፅድቃ ኸም ድሙቕ ብርሃን፥ ምድሓና ኸዓ፥ ከም ሃልሃልታ ፋና ኽሳዕ ዝወፅእ፥ ስለ ፅዮን ስቕ ኣይብልን፤ ስለ ኢየሩሳሌምውን ኣየዕርፍን እየ። ትግርኛ GAZBIB Qajeelummaan ishee akka biiftuu ganamaa hamma ol ba'utti, fayyinni ishees akka guca bobba'utti hamma ibsutti, ani waa'e… Afaan Oromoo BCV GIZ ወኢያረምም በእንተ ጽዮን ወኢየኅድግ በእንተ ኢየሩሳሌም እስመ ትወፅእ ጽድቅየ ከመ ብርሃን ወተኀቱ መድኀኒትየ ከመ ማኅቶት። giz GAZGAZ Qajeelummaan ishee akka biiftuu ganamaa hamma ol ba'utti, fayyinni ishees akka guca bobba'utti hamma ibsutti, ani waa'e… Afaan Oromoo BCV aksum ፅድቃ ኸም ድሙቕ ብርሃን፥ ምድሓና ኸዓ፥ ከም ሃልሃልታ ፋና ኽሳዕ ዝወፅእ፥ ስለ ፅዮን ስቕ ኣይብልን፤ ስለ ኢየሩሳሌምውን ኣየዕርፍን እየ። ትግርኛ AMHNIV ጽድቋ እንደ ማለዳ ወጋገን እስኪፈነጥቅ፣ ድነቷ እንደሚያንጸባርቅ ፋና እስኪታይ፣ ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም። አማርኛ SWAHSUV Kwa ajili ya Sayuni sitanyamaza, na kwa ajili ya Yerusalemu sitatulia, hata haki yake itakapotokea kama mwangaza, na wo… Kiswahili