ትንቢተ ኢሳይያስ 57

AMHEVGአማርኛ21 ጥቅሶች3:55 አዳምጥ
አዳምጥ 3:55 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጻድቅ ይሞታል፥ በልቡም ነገሩን የሚያኖር የለም፤ ምሕረተኞችም ይወገዳሉ፥ ጽድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም።

2ወደ ሰላም ይገባል፤ በቅንነት የሄደ በአልጋው ላይ ያርፋል።

3እናንተ የአስማተኛይቱ ልጆች፥ የአመንዝራውና የጋለሞታይቱ ዘር፥ ወደዚህ ቅረቡ።

4በማን ታላግጣላችሁ? በማንስ ላይ አፋችሁን ታላቅቃላችሁ? ምላሳችሁንስ በማን ላይ ታስረዝማላችሁ?

5እናንተ በአድባር ዛፎች መካከል በለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች በፍትወት የምትቃጠሉ፥ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ሕፃናትን የምታርዱ፥ የዓመፅ ልጆችና የሐሰት ዘር አይደላችሁምን?

6በሸለቆው ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች እድል ፈንታሽ ናቸው፥ እነርሱም ዕጣሽ ናቸው፤ ለእነርሱም የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፥ የእህልንም ቍርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣምን?

7ከፍ ባለውም በረዘመውም ተራራ ላይ መኝታሽን አደረግሽ፥ መሥዋዕትንም ትሠዊ ዘንድ ወደዚያ ወጣሽ።

8ከመዝጊያውና ከመቃኑ በኋላ መታሰቢያሽን አደረግሽ፤ እኔን ትተሽ ለሌላ ተገልጠሻል፥ ወጥተሽ መኝታሽን አስፍተሻል፤ ቃል ኪዳንም ተጋባሻቸው፥ ባየሽበትም ስፍራ ሁሉ መኝታቸውን ወደድሽ።

9ዘይትም ይዘሽ ወደ ንጉሡ ሄድሽ፥ ሽቱሽንም አበዛሽ፥ መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፥ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ።

10በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፥ ነገር ግን፦ ተስፋ የለም፡ አላልሽም፤ የጕልበትን መታደስ አገኘሽ፥ ስለዚህም አልዛልሽም።

11ሐሰትን የተናገርሺው እኔንም ያላሰብሺው በልብሽም ነገሩን ያላኖርሺው ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔ ብዙ ጊዜ ዝም አልሁ፥ አንቺም አልፈራሽም።

12እኔ ጽድቅሽን እናገራለሁ፥ ሥራሽም አይረባሽም።

13ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፥ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።

14እርሱም፦ ጥረጉ፥ መንገድን አዘጋጁ፥ ከሕዝቤም መንገድ ዕንቅፋትን አውጡ፡ ይላል።

15ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።

16መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘላለም አልጣላም፥ ሁልጊዜም አልቈጣም።

17ስለ ኃጢአቱ ጥቂት ጊዜ ተቈጥቼ ቀሠፍሁት፥ ፊቴን ሰውሬ ተቈጣሁ፤ እርሱም በልቡ መንገድ እያፈገፈገ ሄደ።

18መንገዱን አይቻለሁ እፈውሰውማለሁ፥ እመራውማለሁ፥ ለእርሱና ስለ እርሱም ለሚያለቅሱ መጽናናትን እመልሳለሁ።

19የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ፤ በሩቅም በቅርብም ላለው ሰላም ሰላም ይሁን፥ እፈውሰውማለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

20ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፥ ውኆቹም ጭቃና ጕድፍ ያወጣሉና።

21ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል አምላኬ።

ማብራሪያ

57:1,2 ጻድቃን ከሞት መውጊያ ይድናሉ እንጂ ከሞት ምት አያመልጡም። ግድ የለሽው ዓለም ይህንን ችላ ይላል። እንደ ሕዝባዊ ኪሳራ የሚያለቅሱለት ጥቂቶች ናቸው፤ እንደ ሕዝባዊ ማስጠንቀቂያም የሚያስተውሉት እጅግ ጥቂቶች ናቸው። እነርሱም ክፋትን እንዳያዩ፣ በእርሱም እንዳይካፈሉ፣ እንዲሁም በእርሱም እንዳይፈተኑ ዘንድ በምሕረት ይወሰዳሉ። ጻድቁ ሰው ሲሞት ወደ ሰላምና ዕረፍት ይገባል።

57:3-12 ጌታ እዚህ ላይ ከሃዲዎችንና ግብዞችን በፊቱ እንዲቀርቡ ይጠራል። ስለ ኃጢአታቸው በተገሰጹ ጊዜና በፍርድ ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው፣ የእግዚአብሔርን ቃል አፌዙበት። አይሁድ ከምርኮ በፊት በጣዖት አምልኮ ጥፋተኞች ነበሩ፤ ነገር ግን ከዚያ መከራ በኋላ አልነበሩም። የሐሰት አማልክትን በማምለክ ያሳዩት ቅንዓት፣ እውነተኛውን አምላክ በማምለክ ረገድ ያለብንን ግድየለሽነት ሊያሳፍር ይችላል። የኃጢአት አገልግሎት አሳፋሪ ባርነት ነው። በዚህ መንገድ ራሳቸውን ወደ ገሃነም የሚያዋርዱትም በዚያ ድርሻቸውን በትክክል ያገኛሉ። ሰዎች ያልተቀደሱ ፍትወቶቻቸውን የሚያቀጣጥል ሃይማኖት ይመርጣሉ። ወንጀላቸውን እንደሚያስተሰርይላቸው ወይም ለሚወዱት ምኞት ይቅርታ እንደሚያስገኝላቸው ካሰቡ፣ ምንም ያህል ታላቅ ወይም አስቀያሚ ቢሆንም ማንኛውንም ክፉ ነገር እንዲያደርጉ ይመራቸዋል። ይህ አረማዊ፣ አይሁዳዊ ወይም ከክርስቶስ ተቃዋሚ የሆኑትን የጣዖት አምልኮ ዓይነቶች ያብራራል። ነገር ግን ከእግዚአብሔር ይልቅ ማንኛውንም ነገር ለተስፋቸውና ለመታመኛቸው የሚያቆሙ ሰዎች ትክክለኛ ፍጻሜ ላይ ፈጽሞ አይደርሱም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The righteous perish, and no one ponders it in his heart; devout men are taken away, and no one understands that the ri… English BCV ፃድቕ ይመውት፥ ግና ነቲ ነገር ብልቡ ዘስተውዕሎ የለን፤ ምሕረት ዝገብሩ ሰባት ይውሰዱ፤ ፃድቃን ካብ ክፉእ ምእንቲ ኽድሕኑ ኸም ዝውሰዱ፥ ዘስተብህል የለን። ትግርኛ GAZBIB “Namni qajeelaan in du'a, namni Waaqayyoof of kennu, wanti hamaan akka isa irra hin geenyeef in fudhatama; namni kana y… Afaan Oromoo BCV GIZ ርኢክሙሂ ከመ ተሀጕለት ጽድቅ ወኢኀለይክሙ በልብክሙ ወአእተቱ ዕደወ ጻድቃነ፤ ወአልቦ ዘአእመረ እስመ እምገጸ ዐመፃ ተአተተ። giz GAZGAZ “Namni qajeelaan in du'a, namni Waaqayyoof of kennu, wanti hamaan akka isa irra hin geenyeef in fudhatama; namni kana y… Afaan Oromoo BCV aksum ፃድቕ ይመውት፥ ግና ነቲ ነገር ብልቡ ዘስተውዕሎ የለን፤ ምሕረት ዝገብሩ ሰባት ይውሰዱ፤ ፃድቃን ካብ ክፉእ ምእንቲ ኽድሕኑ ኸም ዝውሰዱ፥ ዘስተብህል የለን። ትግርኛ AMHNIV ጻድቅ ይሞታል፤ ይህን ግን ማንም ልብ አይልም፤ ለእግዚአብሔር ያደሩ ሰዎች ይወሰዳሉ፤ ጻድቃን ከክፉ ይድኑ ዘንድ፣ መወሰዳቸውን፣ ማንም አያስተውልም። አማርኛ SWAHSUV Mwenye haki hupotea, wala hakuna atiaye hayo moyoni; na watu watauwa huondolewa, wala hakuna afikiriye ya kuwa mwenye h… Kiswahili