ትንቢተ ኢሳይያስ 57

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:24 አዳምጥ
አዳምጥ 4:24 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጻድቅ ይሞታል፤ ይህን ግን ማንም ልብ አይልም፤ ለእግዚአብሔር ያደሩ ሰዎች ይወሰዳሉ፤ ጻድቃን ከክፉ ይድኑ ዘንድ፣ መወሰዳቸውን፣ ማንም አያስተውልም።

2በቅንነት የሚሄዱ፣ ሰላም ይሆንላቸዋል፤ መኝታቸው ላይ ያርፋሉ።

3“እናንት የአስማተኛዪቱ ልጆች ግን፣ እናንት የአመንዝራውና የጋለሞታዪቱ ዘር፤ እናንት፣ ወዲህ ኑ፤

4የምትሣለቁት በማን ላይ ነው? የምታሽሟጥጡት ማንን ነው? ምላሳችሁንስ አውጥታችሁ የምታሾፉት በማን ላይ ነው? እናንት የዐመፀኞች ልጆች፣ የሐሰተኞች ዘር አይደላችሁምን?

5በባሉጥ ዛፎች መካከል፣ ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሥር በዝሙት የምትቃጠሉ፣ በሸለቆዎች፣ በዐለት ስንጣቂዎችም ውስጥ ልጆቻችሁን የምትሠዉ አይደላችሁምን?

6በሸለቆው በሚገኙት ለስላሳ ድንጋዮች ውስጥ ያሉት ጣዖቶች የአንቺ ናቸው፤ እነርሱም ዕጣ ፈንታዎችሽ ናቸው፤ ርግጥ ነው፣ በእነርሱ ላይ የመጠጥ ቊርባን አፍስሰሻል፤ የእህል ቍርባንም አቅርበሻል፤ ታዲያ፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዝም እላለሁን?

7ዐልጋሽን ከፍ ባለውና በረጅሙ ኰረብታ ላይ አነጠፍሽ፤ በዚያም መሥዋዕትሽን ልታቀርቢ ወጣሽ።

8ከመዝጊያሽና ከመቃንሽ ጀርባ፣ የጣዖት ምስሎችሽን ሰቀልሽ፤ እኔን ትተሽ መኝታሽን ገላለጥሽ፤ በላይም ወጥተሽ በጣም ገለጥሽው፤ መኝታቸውን ከወደድሽላቸው ጋር ስምምነት አደረግሽ፤ ዕርቃናቸውንም አየሽ።

9የወይራ ዘይት ይዘሽ፣ ሽቶ በላዩ ጨምረሽ ወደ ሞሎክ ሄድሽ፤ መልእክተኞችሽን ወደ ሩቅ አገር ላክሽ፤ እስከ ራሱ እስከ ሲኦልም ዘለቅሽ።

10በመንገድ ብዛት ደከምሽ፤ ነገር ግን ‘ተስፋ የለውም’ አላልሽም፤ የጒልበት መታደስ አገኘሽ፤ ስለዚህም አልዛልሽም።

11“እኔን የዋሸሽኝ፤ ማንን ፈርተሽ፣ ማንንስ ሠግተሽ ነው? እኔን ያላስታወስሽው፣ ይህንንም በልብሽ ያላኖርሽው፣ እኔን ያልፈራሽው፣ ዝም ስላልሁ አይደለምን?

12ጽድቅሽንና ሥራሽን አጋልጣለሁ፤ እነርሱም አይጠቅሙሽም።

13ለርዳታ በምትጮኺበት ጊዜ፣ የሰበሰብሻቸው ጣዖቶች እስቲ ያድኑሽ! ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤ ሽውሽውታም ይበትናቸዋል። እኔን መጠጊያው ያደረገ ሰው ግን፣ ምድሪቱን ይወርሳል፤ የተቀደሰ ተራራዬንም ገንዘቡ ያደርገዋል።”

14እንዲህ ይባላል፤ “አብጁ፤ አብጁ፤ መንገድ አዘጋጁ፤ ከሕዝቤ መንገድ ዕንቅፋት አስወግዱ።”

15ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤ “የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤ የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋር እሆናለሁ።

16የሰው መንፈስ በፊቴ እንዳይዝል፣ የፈጠርሁትም ሰው እስትንፋስ እንዳይቆም፣ ለዘላለም አልወቅስም፤ ሁልጊዜም አልቈጣም።

17ኀጢአት ስለ ሞላበት ስግብግብነቱ ተቈጣሁት፤ ቀጣሁት፤ ፊቴንም በቍጣ ከእርሱ ሸሸግሁ፤ ያም ሆኖ በገዛ መንገዱ ገፋበት።

18መንገዶቹን አይቻለሁ፤ ቢሆንም እፈውሰዋለሁ፤ እመራዋለሁ፤ ለእርሱና ስለ እርሱ ለሚያለቅሱትም መጽናናትን እመልሳለሁ፤

19በእስራኤል አልቃሾች ከንፈር ላይ ምስጋና እፈጥራለሁ። በቅርብና በሩቅ ላሉት ሰላም፣ ሰላም ይሁን፤ እኔ እፈውሳቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

20ክፉዎች ግን ማዕበሉ ጭቃና ጒድፍ እንደሚያወጣ፣ ጸጥ ማለት እንደማይችል፣ እንደሚናወጥ ባሕር ናቸው።

21አምላኬ፣ “ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል።

ማብራሪያ

57:1,2 ጻድቃን ከሞት መውጊያ ይድናሉ እንጂ ከሞት ምት አያመልጡም። ግድ የለሽው ዓለም ይህንን ችላ ይላል። እንደ ሕዝባዊ ኪሳራ የሚያለቅሱለት ጥቂቶች ናቸው፤ እንደ ሕዝባዊ ማስጠንቀቂያም የሚያስተውሉት እጅግ ጥቂቶች ናቸው። እነርሱም ክፋትን እንዳያዩ፣ በእርሱም እንዳይካፈሉ፣ እንዲሁም በእርሱም እንዳይፈተኑ ዘንድ በምሕረት ይወሰዳሉ። ጻድቁ ሰው ሲሞት ወደ ሰላምና ዕረፍት ይገባል።

57:3-12 ጌታ እዚህ ላይ ከሃዲዎችንና ግብዞችን በፊቱ እንዲቀርቡ ይጠራል። ስለ ኃጢአታቸው በተገሰጹ ጊዜና በፍርድ ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው፣ የእግዚአብሔርን ቃል አፌዙበት። አይሁድ ከምርኮ በፊት በጣዖት አምልኮ ጥፋተኞች ነበሩ፤ ነገር ግን ከዚያ መከራ በኋላ አልነበሩም። የሐሰት አማልክትን በማምለክ ያሳዩት ቅንዓት፣ እውነተኛውን አምላክ በማምለክ ረገድ ያለብንን ግድየለሽነት ሊያሳፍር ይችላል። የኃጢአት አገልግሎት አሳፋሪ ባርነት ነው። በዚህ መንገድ ራሳቸውን ወደ ገሃነም የሚያዋርዱትም በዚያ ድርሻቸውን በትክክል ያገኛሉ። ሰዎች ያልተቀደሱ ፍትወቶቻቸውን የሚያቀጣጥል ሃይማኖት ይመርጣሉ። ወንጀላቸውን እንደሚያስተሰርይላቸው ወይም ለሚወዱት ምኞት ይቅርታ እንደሚያስገኝላቸው ካሰቡ፣ ምንም ያህል ታላቅ ወይም አስቀያሚ ቢሆንም ማንኛውንም ክፉ ነገር እንዲያደርጉ ይመራቸዋል። ይህ አረማዊ፣ አይሁዳዊ ወይም ከክርስቶስ ተቃዋሚ የሆኑትን የጣዖት አምልኮ ዓይነቶች ያብራራል። ነገር ግን ከእግዚአብሔር ይልቅ ማንኛውንም ነገር ለተስፋቸውና ለመታመኛቸው የሚያቆሙ ሰዎች ትክክለኛ ፍጻሜ ላይ ፈጽሞ አይደርሱም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ጻድቅ ይሞታል፥ በልቡም ነገሩን የሚያኖር የለም፤ ምሕረተኞችም ይወገዳሉ፥ ጽድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም። አማርኛ ENGNIV The righteous perish, and no one ponders it in his heart; devout men are taken away, and no one understands that the ri… English BCV ፃድቕ ይመውት፥ ግና ነቲ ነገር ብልቡ ዘስተውዕሎ የለን፤ ምሕረት ዝገብሩ ሰባት ይውሰዱ፤ ፃድቃን ካብ ክፉእ ምእንቲ ኽድሕኑ ኸም ዝውሰዱ፥ ዘስተብህል የለን። ትግርኛ GAZBIB “Namni qajeelaan in du'a, namni Waaqayyoof of kennu, wanti hamaan akka isa irra hin geenyeef in fudhatama; namni kana y… Afaan Oromoo BCV GIZ ርኢክሙሂ ከመ ተሀጕለት ጽድቅ ወኢኀለይክሙ በልብክሙ ወአእተቱ ዕደወ ጻድቃነ፤ ወአልቦ ዘአእመረ እስመ እምገጸ ዐመፃ ተአተተ። giz GAZGAZ “Namni qajeelaan in du'a, namni Waaqayyoof of kennu, wanti hamaan akka isa irra hin geenyeef in fudhatama; namni kana y… Afaan Oromoo BCV aksum ፃድቕ ይመውት፥ ግና ነቲ ነገር ብልቡ ዘስተውዕሎ የለን፤ ምሕረት ዝገብሩ ሰባት ይውሰዱ፤ ፃድቃን ካብ ክፉእ ምእንቲ ኽድሕኑ ኸም ዝውሰዱ፥ ዘስተብህል የለን። ትግርኛ SWAHSUV Mwenye haki hupotea, wala hakuna atiaye hayo moyoni; na watu watauwa huondolewa, wala hakuna afikiriye ya kuwa mwenye h… Kiswahili