ትንቢተ ኢሳይያስ 43

AMHNIVአማርኛ28 ጥቅሶች4:57 አዳምጥ
አዳምጥ 4:57 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ! የፈጠረህ፤ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤

2በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።

3እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የእስራኤልም ቅዱስ መድኀኒትህ ነኝና፤ ግብፅን ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣ ኢትዮጵያንና ሳባን በአንተ ፈንታ እሰጣለሁ።

4ለዐይኔ ብርቅና ክቡርም ስለ ሆንህ፣ እኔም ስለምወድህ፣ ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ።

5ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ ልጆችህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።

6ሰሜንን፣ ‘አምጣ’፣ ደቡብንም፣ ‘ልቀቅ’ እላለሁ፤ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፣

7በስሜ የተጠራውን ሁሉ፣ ለክብሬ የፈጠርሁትን፣ ያበጀሁትንና የሠራሁትን አምጡ።”

8ዐይን እያላቸው የታወሩትን፣ ጆሮ እያላቸው የደነቈሩትን አውጣ።

9ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰብ፤ ሰውም ይከማች፤ ከእነርሱ አስቀድሞ ይህን የነገረን፣ የቀድሞውን ነገር ያወጀልን ማን ነው? ሌሎችን ሰምተው፣ “እውነት ነው” እንዲሉ፣ ትክክለኝነታቸውም እንዲረጋገጥ ምስክሮቻቸውን ያቅርቡ።

10“ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣ እርሱ እኔ እንደሆንሁ ትረዱ ዘንድ፣ እናንተ ምስክሮቼ፣ የመረጥሁትም ባሪያዬ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር። “ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ ከእኔም በኋላ አይኖርም።

11እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም ሌላ የሚያድን የለም።

12ገልጫለሁ፤ አድኛለሁ፤ ተናግሬአለሁ፤ በመካከላችሁ እኔ እንጂ ባዕድ አምላክ አልነበረም። እኔ አምላክ እንደሆንሁ፣ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር፤

13“ከጥንት ጀምሮ እኔው ነኝ፤ ከእጄም ማውጣት የሚችል የለም፤ እኔ የምሠራውን ማን ማገድ ይችላል?”

14የእስራኤል ቅዱስ፣ የሚቤዣችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ እናንተ በባቢሎን ላይ ሰራዊት እሰዳለሁ፤ በሚመኩባቸውም መርከቦች፣ ባቢሎናውያንን ሁሉ እንደ ኰብላይ አመጣለሁ።

15እኔ እግዚአብሔር፣ የእናንተ ቅዱስ፣ የእስራኤል ፈጣሪ፣ ንጉሣችሁ ነኝ።”

16በባሕር ውስጥ መንገድ፣ በማዕበል ውስጥ መተላለፊያ ያበጀ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

17እንደ ገና ላይነሡ እዚያው እንዲተኙ፣ እንደ ጧፍ ኵስታሪ ረግፈው እንዲጠፉ፣ ሠረገሎችንና ፈረሶችን፣ ሰራዊቱንና ደጀኑን በአንድነት ያወጣ እንዲህ ይላል፤

18“የቀደመውን ነገር አታስቡ፤ ያለፈውን እርሱ።

19እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤

20የምድረ በዳ አራዊት፣ ቀበሮና ጒጒት ያከብሩኛል፤ በምድረ በዳ ውሃ፣ በበረሓም ምንጭ እሰጣለሁና። ለመረጥሁት ሕዝቤ ውሃ እሰጣለሁ፤

21ለራሴ ያበጀሁት ሕዝብ ምስጋናዬን ያውጅ ዘንድ ይህን አደርጋለሁ።

22“ያዕቆብ ሆይ፤ አንተ ግን አልጠራኸኝም፤ እስራኤል ሆይ፤ የእኔ ነገር ታክቶሃል።

23ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎች አላመጣህልኝም፤ በመሥዋዕትህም አላከበርኸኝም። በእህል ቍርባን አላስቸገርሁህም፤ በዕጣን መሥዋዕትም አላሰለቸሁህም።

24መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን አልገዛህልኝም፤ በመሥዋዕትህ ሥብ አላጠገብኸኝም፤ ነገር ግን የኀጢአት ሸክምህን ጫንህብኝ፤ በበደልህም አደከምኸኝ።

25“ስለ ራሴ ስል መተላለፍህን የምደመስ ስልህ፣ እኔ፣ እኔው ነኝ፤ ኀጢአትህን አላስባትም።

26እስቲ ያለፈውን አስታውሰኝ፤ ተቀራርበን እንከራከርበት፤ ትክክለኛ ስለ መሆንህም አስረዳ።

27የመጀመሪያው አባትህ ኀጢአት ሠርቶአል፤ መምህሮችህም ዐምፀውብኛል።

28ስለዚህ የመቅደስህን አለቆች አዋርዳለሁ፤ ያዕቆብን ለጥፋት፣ እስራኤልን ለስድብ እዳርጋለሁ።

ማብራሪያ

43:1-7 የእግዚአብሔር ሞገስና በጎ ፈቃድ ለሕዝቡ ለሁሉም አማኞች እጅግ ብዙ መጽናናትን ይናገራል። አዲሱ ፍጥረት የትም ቢሆን፣ የእግዚአብሔር አሠራር ነው። በልጁ ደም የተቤዠጉት ሁሉ፣ እርሱ ለራሱ ለይቷቸዋል። እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የሆነላቸው፣ ማን ወይም ምን ሊቃወማቸው ቢችልም መፍራት የለባቸውም። ግብፅና ኢትዮጵያ፣ ሕይወታቸውና ሀብታቸው ሁሉ፣ ከክርስቶስ ደም ጋር ሲወዳደሩ ምንድናቸው? እውነተኛ አማኞች በእግዚአብሔር ፊት የከበሩ ናቸው፤ እርሱም ከየትኛውም ሕዝብ በላይ በእነርሱ ላይ ደስታው ነው። በእሳትና በውሃ ውስጥ እንዳለፉ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እስከሆነ ድረስ ምንም ክፉ ነገር አይፈሩም፤ ይደገፋሉ እንዲሁም ይወጣሉ። ታማኞቹ ይበረታታሉ። ከየአቅጣጫው ይሰበሰባሉ። ይህንን ደስ የሚያሰኝ እይታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ነቢዩ ደግሞም ከሚያስጨንቁ ፍራቻዎች ያርቃል።

43:8-13 ጣዖት አምላኪዎች ለጣዖቶቻቸው እንዲከላከሉ እንዲቀርቡ ተጠርተዋል። የሚሠሩአቸውና በእነሱ የሚታመኑ እነሱኑ ይመስላሉ። የሰው መልክና ችሎታዎች አሏቸው፤ ነገር ግን የማስተዋል ችሎታ የላቸውም። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ የጸጋውን ኃይል፣ የመጽናናቱን ጣዕም፣ የመለኮታዊ አርአያነቱን ደግ እንክብካቤ፣ እና የተስፋ ቃሉን እውነት ያውቃሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ። አማርኛ ENGNIV But now, this is what the Lord says– he who created you, O Jacob, he who formed you, O Israel: “Fear not, for I have re… English BCV ሕዚ ግና ኦ ያእቆብ፥ እቲ ዝፈጠረካ፥ ኦ እስራኤል፥ እቲ ዝሰርሐካ፥ እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል ኣሎ፦ “ተቤዚወካ እየ እሞ፥ ኣይትፍራሕ፤ ብስምካ ፀዋዕኩኻ፤ ንስኻ ናተይ ኢኻ። ትግርኛ GAZBIB Amma garuu yaa Yaaqoob, yaa Israa'el, Waaqayyo inni si uume, inni si tolches, “Ani si fureera hin sodaatin, “Ati kan ko… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይእዜኒ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር አምላክ ዘገብረኪ ያዕቆብ ወዘፈጠረከ እስራኤል፦ ኢትፍራህ እንከ እስመ አድኀንኩከ ወሰመይኩ ስመከ ወዚአየ አንተ። giz GAZGAZ Amma garuu yaa Yaaqoob, yaa Israa'el, Waaqayyo inni si uume, inni si tolches, “Ani si fureera hin sodaatin, “Ati kan ko… Afaan Oromoo BCV aksum ሕዚ ግና ኦ ያእቆብ፥ እቲ ዝፈጠረካ፥ ኦ እስራኤል፥ እቲ ዝሰርሐካ፥ እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል ኣሎ፦ “ተቤዚወካ እየ እሞ፥ ኣይትፍራሕ፤ ብስምካ ፀዋዕኩኻ፤ ንስኻ ናተይ ኢኻ። ትግርኛ SWAHSUV Lakini sasa, Bwana aliyekuhuluku, Ee Yakobo, yeye aliyekuumba, Ee Israeli, asema hivi, Usiogope, maana nimekukomboa; ni… Kiswahili