ትንቢተ ኢሳይያስ 42

AMHEVGአማርኛ24 ጥቅሶች4:26 አዳምጥ
አዳምጥ 4:26 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።

2አይጮኽም ቃሉንም አያነሣም፥ ድምፁንም በሜዳ አያሰማም።

3የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፥ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል።

4በምድርም ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ ይበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።

5ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፥ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፥ በእርስዋ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፥ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

6እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፥ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ፥ የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።

8እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።

9እነሆ፥ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፥ አዲስ ነገርንም እናገራለሁ፤ አስቀድሞም ሳይበቅል እርሱን አስታውቃችኋለሁ።

10ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርስዋም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፥ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።

11ምድረ በዳውና ከተሞቹ የቄዳርም ሰዎች የሚቀመጡባቸው መንደሮች ድምፃቸውን ያንሡ፤ በሴላ የሚኖሩ እልል ይበሉ፥ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።

12ለእግዚአብሔር ክብርን ይስጡ፥ ምስጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ።

13እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይወጣል እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል በጠላቶቹም ላይ ይበረታል።

14ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፥ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፤ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮኻለሁ፤ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ።

15ተራሮችንና ኮረብቶችን አፈርሳለሁ፥ ቡቃያዎቻቸውንም ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ደሴቶች አደርጋለሁ፥ ኵሬዎችንም አደርቃለሁ።

16ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፥ በማያውቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፥ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውምም።

17በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፦ አምላኮቻችን ናችሁ፡ የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፥ ፈጽመውም ያፍራሉ።

18እናንተ ደንቆሮች፥ ስሙ፤ እናንተም ዕውሮች፥ ታዩ ዘንድ ተመልከቱ።

19ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹሙ ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው?

20ብዙ ነገርን ታያላችሁ ነገር ግን አትጠባበቁትም፤ ጆሮአችሁም ተከፍተዋል፥ ነገር ግን አትሰሙም።

21እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ።

22ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፤ ሁላቸው በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፤ ብዝበዛ ሆነዋል የሚያድንም የለም፥ ምርኮም ሆነዋል፥ ማንም፦ መልሱ፡ አይልም።

23ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፥ ለሚመጣውም ጊዜ የሚያደምጥና የሚሰማ ማን ነው?

24ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ይሄዱ ዘንድ ያልወደዱት ለሕጉም ያልታዘዙለት እግዚአብሔር እርሱ አይደለምን?

25ስለዚህ የቍጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አፈሰሰበት፤ በዙሪያም አነደደው እርሱ ግን አላወቀም፥ አቃጠለውም እርሱ ግን ልብ አላደረገም።

ማብራሪያ

ኢሳይያስ 42:1-4 ይህ ትንቢት በክርስቶስ ተፈጽሟል (ማቴዎስ 12:17)። ነፍሳችን በእርሱ ላይ ትደገፍ፣ በእርሱም ደስ ይበላት፤ ያንጊዜም በእርሱ ተብሎ አብ በእኛ ደስ ይሰኛል። መንፈስ ቅዱስ መጣ ብቻ ሳይሆን በእርሱ ላይ አረፈ፣ ያለ መጠን። እርሱ የኃጢአተኞችን ተቃውሞ በትዕግሥት ተሸከመ። መንግሥቱ መንፈሳዊ ነው፤ በምድራዊ ክብር ሊገለጥ አልነበረም። እርሱ በጥርጣሬና በፍርሃት ለተጨነቁ፣ እንደተቀጠቀጠ ሸንበቆ ለሆኑት፣ እንደሚያጨስ የተልባ ፈትል ላሉት፣ ወይም አዲስ እንደበራ የመብራት ክር ሆኖ ሊጠፋ የተቃረበን ርኅሩኅ ነው። እርሱ አይንቃቸውም፣ የማይችሉትንም ከባድ ሥራ ወይም መከራ አይጭንባቸውም። እርሱ በብዙ ተአምራቱና በትንሣኤው የቅዱስ ሃይማኖቱን እውነት ሙሉ በሙሉ አሳየ። በወንጌሉ ኃይልና በጸጋው በሰዎች አእምሮ ውስጥ ጠቢባንና ጻድቃን የሚያደርጋቸውን መርሆች ይሰርጻል። እጅግ ሩቅ የሆኑ ብሔራት ሕጉንና ወንጌሉን ይጠብቃሉ፣ በደስታም ይቀበሉታል። ጥሪያችንንና ምርጫችንን እርግጠኛ ለማድረግ፣ አብም በእኛ ላይ ለበጎ ደስ እንዲሰኝ ከፈለግን፣ ክርስቶስን ማየት፣ መስማት፣ ማመንና መታዘዝ አለብን።

ኢሳ ፵፪፥፭-፲፪ የቤዛነት ሥራ ሰውን እንደ ፈጣሪው ለእግዚአብሔር ሊታዘዝ ወደሚገባው ታዛዥነት ይመልሰዋል። ክርስቶስ የዓለም ብርሃን ነው። በጸጋውም ሰይጣን ያሳወራቸውን አእምሮአቸውን ይከፍታል፤ ከኃጢአት ባርነትም ነፃ ያወጣል። እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያኑን አግዟል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “Here is my servant, whom I uphold, my chosen one in whom I delight; I will put my Spirit on him and he will bring just… English BCV “እንሆ፥ ደጊፈ ዝሓዝኩዎ ባርያይ፥ ኣነ ዝሓረኽዎ፥ ብእኡ ኸዓ ደስ ዝብለኒ፥ ሕሩየይ፥ መንፈሰይ ኣብ ልዕሊኡ ኣሕዲረ ኣለኹ፤ ንሱ ኸዓ ንኣህዛብ ፍትሒ ኸውፅአሎም እዩ። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo itti fufee,“Kunoo, garbichi koo inni ani ol ol qabu, inni ani fo'adhe, inni ani jaalladhu isa kana! Ani hafuur… Afaan Oromoo BCV GIZ ናሁ ቍልዔየ ዘአኀዝክዎ፤ ወእስራኤል ኅሩይየ ዘተወክፈቶ ነፍስየ፤ ወወሀብኩ መንፈስየ ዲቤሁ ያመጽእ ፍትሐ ለአሕዛብ። giz GAZGAZ Waaqayyo itti fufee,“Kunoo, garbichi koo inni ani ol ol qabu, inni ani fo'adhe, inni ani jaalladhu isa kana! Ani hafuur… Afaan Oromoo BCV aksum “እንሆ፥ ደጊፈ ዝሓዝኩዎ ባርያይ፥ ኣነ ዝሓረኽዎ፥ ብእኡ ኸዓ ደስ ዝብለኒ፥ ሕሩየይ፥ መንፈሰይ ኣብ ልዕሊኡ ኣሕዲረ ኣለኹ፤ ንሱ ኸዓ ንኣህዛብ ፍትሒ ኸውፅአሎም እዩ። ትግርኛ AMHNIV “ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፣ በእርሱም ደስ የሚለኝ ምርጤ ይህ ነው፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል። አማርኛ SWAHSUV Tazama mtumishi wangu nimtegemezaye; mteule wangu, ambaye nafsi yangu imependezwa naye; nimetia roho yangu juu yake; na… Kiswahili