ትንቢተ ሆሴዕ 8

AMHNIVአማርኛ14 ጥቅሶች2:33 አዳምጥ
አዳምጥ 2:33 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“መለከትን በአፍህ ላይ አድርግ፤ ሕዝቡ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና፣ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና፣ ንስር በእግዚአብሔር ቤት ላይ ነው፤

2እስራኤልም፣ ‘አምላካችን ሆይ፤ እኛ እናውቅሃለን’ እያሉ፣ ወደ እኔ ይጮኻሉ።

3ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ናቁ፤ ጠላትም ያሳድዳቸዋል።

4ያለ እኔ ፈቃድ ነገሥታትን አነገሡ፤ እኔንም ሳይጠይቁ አለቆችን መረጡ፤ በብራቸውና በወርቃቸው፣ ለገዛ ጥፋታቸው፣ ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።

5ሰማርያ ሆይ፤ የጥጃ ጣዖትሽን ጣይ፤ ቊጣዬ በእነርሱ ላይ ነድዶአል፤ የማይነጹት እስከ መቼ ነው?

6ይህም በእስራኤል ሆነ! ባለ እጅ የሠራው ይህ ጥጃ፣ አምላክ አይደለም፤ ያ የሰማርያ ጥጃ፣ ተሰባብሮ ይደቃል።

7“ነፋስን ይዘራሉ፤ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ አገዳው ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም፤ እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ ባዕዳን ይበሉታል።

8እስራኤል ተውጠዋል፤ በአሕዛብም መካከል፣ ዋጋ እንደሌለው ዕቃ ሆነዋል።

9ለብቻው እንደሚባዝን የዱር አህያ፣ ወደ አሦር ሄደዋልና፤ ኤፍሬም በእጅ መንሻ ወዳጅ አበጀ።

10በአሕዛብ መካከል ራሳቸውን ቢሸጡም፣ እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ በኀያል ንጉሥ ጭቈና ሥር፣ እየመነመኑ ይሄዳሉ።

11“ኤፍሬም ለኀጢአት ማስተስረያ ብዙ መሠዊያዎችን ቢሠራም፣ እነርሱ የኀጢአት መሥሪያ መሠዊያዎች ሆነውበታል።

12በሕጌ ውስጥ ያለውን ብዙውን ነገር ጻፍሁላቸው፤ እነርሱ ግን እንደ እንግዳ ነገር ቈጠሩት።

13ለእኔ የሚገባውን መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤ እግዚአብሔር ግን በእነርሱ አልተደሰተም፤ ስለዚህ ክፋታቸውን ያስታውሳል፤ ኀጢአታቸውን ይቀጣል፤ ወደ ግብፅም ይመለሳሉ።

14እስራኤል ፈጣሪውን ረሳ፤ ቤተ መንግሥቶችንም ሠራ፤ ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አበዛ፤ እኔ ግን በከተሞቻቸው ላይ እሳትን እለቃለሁ፤ ምሽጎቻቸውንም ይበላል።”

ማብራሪያ

8:1-4 እስራኤል በጭንቀት በተጫነች ጊዜ ከእግዚአብሔር ጥበቃን ይማፀኑ ነበር፤ ነገር ግን ይህ ቸል ይባል ነበር። ‹አምላኬ ሆይ፣ አውቅሃለሁ› ብሎ ማለት፣ ‹አምላኬ ሆይ፣ እወድሃለሁ፣ አገለግልሃለሁ፣ አንተንም ብቻ እጠጋለሁ› ብለን ለመናገር ካልቻልን፣ ምንስ ጥቅም ይኖረዋል?

8:5-10 ጣዖታትን በማምለክ ብዙ፣ ሰላምና ድልን ለራሳቸው ተስፋ አድርገው ነበርና፥ ነገር ግን ተስፋዎቻቸው ከንቱ ሆኑ። የዘሩት ግንድም ቅጠልም የለውም፥ ወይም ቢኖረውም እንኳን ቡቃያው ፍሬ አይሰጥም፤ በውስጣቸው ምንም አልነበረም። የጨለማ ሥራዎች ፍሬ የለሾች ናቸው፤ ይልቁንም የእነዚያ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነው። የኃጢአተኞች ተስፋ ያታልላቸዋል፥ ትርፋቸውም ወጥመድ ይሆናል። በአደጋ ጊዜ፥ በተለይም በፍርድ ቀን፥ ሥጋዊ ዘዴዎች ሁሉ ይከሽፋሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6