ትንቢተ ሆሴዕ 9

AMHEVGአማርኛ17 ጥቅሶች3:09 አዳምጥ
አዳምጥ 3:09 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እስራኤል ሆይ፥ ከአምላክህ ተለይተህ አመንዝረሃልና እንደ አሕዛብ ደስ አይበልህ፥ ሐሴትንም አታድርግ፤ በእህሉ አውድማ ሁሉ ላይ የግልሙትናን ዋጋ ወድደሃል።

2አውድማውና መጥመቂያው አይመግባቸውም፥ ጉሽ ጠጅም ይጐድልባታል።

3በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይቀመጡም፤ ኤፍሬምም ወደ ግብፅ ይመለሳል፥ በአሦርም ርኩስን ነገር ይበላሉ።

4ለእግዚአብሔርም የወይን ጠጅን ቁርባን አያፈስሱም፥ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤ የኀዘንም እንጀራ ይሆንላቸዋል፥ የሚበላውም ሁሉ ይረክሳል፤ እንጀራቸውም ለሰውነታቸው ይሆናል እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይገባም።

5በዓመት በዓል ቀንና በእግዚአብሔር በዓል ቀን ምን ታደርጋላችሁ?

6እነሆ፥ ከጥፋት ሸሽተው ሄዱ፥ ግብፅም ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች፤ ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሳል፥ እሾህም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል።

7የበቀል ወራት መጥቶአል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ያውቃል፤ ከኃጢአትህና ከጠላትነትህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሰንፎአል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።

8ኤፍሬም ከአምላኬ ጋር ተመልካች ነበረ፤ አሁን ግን ነቢዩ በመንገዱ ሁሉ ላይ የወፍ ወጥመድ ሆነ፥ በአምላኩም ቤት ጠላትነት አለ።

9በጊብዓ ዘመን እንደ ነበረ እጅግ ረከሱ፤ እርሱም በደላቸውን ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይበቀላል።

10እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ ወይን ሆኖ አገኘሁት፤ አባቶቻችሁንም ከመጀመሪያዋ ዓመት እንደ በለስ በኵራት ሆነው አየኋቸው፤ እነርሱ ግን ወደ ብዔልፌጎር መጡ፥ ለነውርም ተለዩ፥ እንደ ወደዱትም ርኩስ ሆኑ፥

11የኤፍሬምም ክብር እንደ ወፍ በርሮ ይጠፋል፤ መውለድና መፅነስ ማርገዝም አይሆንላቸውም።

12ልጆቻቸውንም ቢያሳድጉ ሰው እንዳይቀርላቸው ልጅ አልባ አደረጋቸዋለሁ፤ ከእነርሱም በራቅሁ ጊዜ ወዮላቸው!

13እኔ እንዳየሁ የኤፍሬም ልጆች ለምርኮ ተሰጥተዋል፤ ኤፍሬምም ልጆቹን ወደ ገዳዩች ያወጣል።

14አቤቱ፥ ስጣቸው፤ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፍን ማኅፀን የደረቀውንም ጡት ስጣቸው።

15ክፋታቸው ሁሉ በጌልገላ አለ፤ በዚያ ጠልቻቸዋለሁ፤ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመፀኞች ናቸው።

16ኤፍሬም ተመታ፥ ሥሩም ደረቀ፥ ፍሬም አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።

17አልሰሙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል፤ በአሕዛብም መካከል ተቅበዝባዦች ይሆናሉ።

ማብራሪያ

9:1-6 እስራኤል ለጣዖቶቻቸው በሚያቀርቡት መባ አማካኝነት ሽልማት ሰጧቸው። በሃይማኖት ጉዳይ ንፉግ የሆኑ ሰዎች በፍትወቶቻቸው ላይ ደግሞ አባካኝ መሆን የተለመደ ነው። ከእግዚአብሔር ሞገስና ከዘላለም ሕይወት ከሚገኘው ሽልማት ይልቅ፣ በሰብል በረከት ውስጥ ያለውን ሽልማት የሚወዱ ሰዎች እንደ ጣዖት አምላኪዎች ይቆጠራሉ። በመከር ደስታ የተሞሉ ናቸው፤ ለኃጢአትም የማዘን ዝንባሌ የላቸውም። ዓለምንና የዓለምን ነገሮች ጣዖታችንና ድርሻችን ስናደርግ፣ እግዚአብሔር ስንፍናችንን ሊያሳየንና ሊያርመን ፍትሐዊ ነው። የጌታን ሕጎች የማይገዛለት ወይም በፍቅሩ የማይነዳ ማንም በእግዚአብሔር ምድር ለመኖር ሊጠብቅ አይችልም። የጸጋን መንገዶች ስንጠቀምባቸው፣ ከእኛ ቢወሰዱ ምን እንደምናደርግ ልናስብ ይገባል። ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት የማድረግ ደስታዎች ለለውጥ የማይገዙ ሲሆኑ፣ በብር የተገዙ ወይም ሰዎች ብራቸውን የሚያስቀምጡባቸው ደስ የሚያሰኙ ቦታዎች ግን ሊወድሙ ይችላሉ። እንደ ነፍስ ረሃብ የከፋ ረሃብ የለም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Do not rejoice, O Israel; do not be jubilant like the other nations. For you have been unfaithful to your God; you love… English BCV ኦ እስራኤል፥ ካብ ኣምላኽካ ተፈሊኻ ኣመንዚርካ፥ ኣብ ኵሉ ዓውዲ ስርናይ ዋጋ ምንዝርና ፈቲኻ ኢኻሞ፥ ከም ኣህዛብ ደስ ኣይበልካ፤ ኣይትተሓጐስውን። ትግርኛ GAZBIB Yaa Israa'el, ati ejjuu keetiin Waaqayyo kee irraa waan gara galteef, midhaan oobdii hundumaa irratti argattus “Gatii g… Afaan Oromoo BCV GIZ ኢትትፈሣሕ ወኢትትሐሠይ እስራኤል ከመ አሕዛብ እስመ ዘመውከ እምአምላክከ፤ ወአፍቀርከ ሀብተ እምኵሉ ዓውደ እክል ወምክያደ ወይን። giz GAZGAZ Yaa Israa'el, ati ejjuu keetiin Waaqayyo kee irraa waan gara galteef, midhaan oobdii hundumaa irratti argattus “Gatii g… Afaan Oromoo BCV aksum ኦ እስራኤል፥ ካብ ኣምላኽካ ተፈሊኻ ኣመንዚርካ፥ ኣብ ኵሉ ዓውዲ ስርናይ ዋጋ ምንዝርና ፈቲኻ ኢኻሞ፥ ከም ኣህዛብ ደስ ኣይበልካ፤ ኣይትተሓጐስውን። ትግርኛ AMHNIV እስራኤል ሆይ፤ ደስ አይበልሽ፤ እንደ ሌሎችም ሕዝቦች ሐሤት አታድርጊ፤ ለአምላክሽ ታማኝ አልሆንሽምና፤ በየእህል ዐውድማውም ላይ፣ ለጋለሞታ የሚከፈለውን ዋጋ ወደሻል። አማርኛ SWAHSUV Usifurahi, Israeli, kwa sababu ya furaha, kama hao mataifa; kwa kuwa umezini juu ya Mungu wako, umependa ujira katika k… Kiswahili