ትንቢተ ሆሴዕ 7

AMHEVGአማርኛ16 ጥቅሶች2:31 አዳምጥ
አዳምጥ 2:31 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በውጭም ወንበዴዎች ቀምተዋልና እስራኤልን እፈውስ ዘንድ በወደድሁ ጊዜ የኤፍሬም ኃጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ።

2እኔም ክፋታቸውን ሁሉ እንዳሰብሁ በልባቸው አያስቡም አሁንም ሥራቸው ከብባቸዋለች፥ በፊቴም አለች።

3ንጉሡን በክፋታቸው፥ አለቆቹንም በሐሰታቸው ደስ አሰኝተዋል።

4ሁሉም አመንዝራዎች ናቸው፤ ጋጋሪ እንደሚያነድድበት እንደ ምድጃ ናቸው፤ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ እሳትን መቈስቈስና እርሾን መለወስ ይቆያል።

5በንጉሣችን ቀን አለቆች ከወይን ጠጅ ሙቀት የተነሣ ታመሙ፤ እርሱም ከዋዘኞች ጋር እጁን ዘረጋ።

6እያደቡ ልባቸውን እንደ ምድጃ አዘጋጅተዋል፤ አበዛቸውም ሌሊቱን ሁሉ አንቀላፋ፤ በጠባም ጊዜ እንደ እሳት ነበልባል ይነድዳል።

7ሁሉም እንደ ምድጃ ግለዋል፥ ፈራጆቻቸውንም በሉ፤ ነገሥታቶቻቸውም ሁሉ ወደቁ፤ ከእነርሱም ወደ እኔ የሚጮኽ የለም።

8ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፤ ኤፍሬም እንዳልተገላበጠ ቂጣ ነው።

9እንግዶች ጕልበቱን በሉት፥ እርሱም አላወቀም፤ ሽበትም ወጣበት፥ እርሱም አላወቀም።

10የእስራኤልም ትዕቢቱ በፊቱ መሰከረ፤ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ግን አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም።

11ኤፍሬምም አእምሮ እንደሌላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፤ ግብፅን ጠሩ፥ ወደ አሦርም ሄዱ።

12ሲሄዱ አሽክላዬን አዘረጋባቸዋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎች አወርዳቸዋለሁ፤ መከራቸውን ሲሰሙ እገሥጻቸዋለሁ።

13ከእኔ ፈቀቅ ብለዋልና ወዮላቸው! በእኔም ላይ ዐመፀዋልና ጥፋት ይምጣባቸው! እኔ ልታደጋቸው ወደድሁ፥ እነርሱ ግን በሐሰት ተናገሩብኝ።

14በመኝታቸው ላይ ሆነው ያለቅሱ ነበር እንጂ በልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም፤ ስለ እህልና ስለ ወይን ጠጅ ይሰበሰቡ ነበር፤ በእኔም ላይ ዐመፁ።

15እኔም ክንዳቸውን አስተማርሁና አጸናሁ፤ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን መከሩብኝ።

16ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ እንደ ተንኰለኛ ቀስት ሆኑ፤ አለቆቻቸው ከምላሳቸው ቍጣ የተነሣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይህ በግብፅ ምድር ውስጥ መሳለቂያ ይሆንባቸዋል።

ማብራሪያ

7:1-7 የእግዚአብሔርን አገዛዝ በተግባር አለማመን ለሁሉ የእስራኤል ክፋት መሠረት ነበር፤ እግዚአብሔር ማየት እንደማይችል ወይም ትኩረት እንደማይሰጥ ሁሉ ነበር። ኃጢአቶቻቸውም በየአቅጣጫው ይታዩ ነበር። ልቦቻቸውም በሚንቦገቦግ ምድጃ ውስጥ እንዳለ እሳት በክፉ ምኞቶች ነድደው ነበር። ብሔር እንደመሆናቸው በመካከላቸው በነበረው ችግር ውስጥ ሳሉ፣ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር እርዳታ መፈለግን አስበው አያውቁም። የሰዎች ሕይወት ትክክለኛ ክፋት በልቦቻቸው ውስጥ ካለው ጋር ሲነጻጸር በጣም ትንሽ ክፍልፋይ ነው። ነገር ግን ምኞት በልብ ውስጥ ሲታቀፍ፣ ወደ ውጫዊ ኃጢአት ይፈነዳል። ሌሎችን ወደ ስካር የሚፈትኑ ሰዎች በፍጹም እውነተኛ ወዳጆቻቸው ሊሆኑ አይችሉም፤ ብዙ ጊዜም ጥፋታቸውን ያቅዳሉ። እንዲህም ሰዎች እርስ በርሳቸው መለኮታዊውን የበቀል እርምጃ ያስፈጽማሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV whenever I would heal Israel, the sins of Ephraim are exposed and the crimes of Samaria revealed. They practice deceit,… English BCV ሓሰት ኣዘውቲሮም እዮም እሞ፥ ሰራቒ ይኣቱ፤ ኣብ ወፃኢ ድማ ሸፋቱ ይኸትሩ ኣለዉ እሞ፥ ንእስራኤል ክፍውሶ ምስ ደለኹ፥ ሓጢኣት ኤፍሬምን፥ ክፍኣት ሰማርያን ተቐልዐ። ትግርኛ GAZBIB “Yeroo ani Israa'elin fayyisuu barbaadutti, yakki Efreem, jal'inni Samaariyaas in mul'ata; isaan gowwoomsaadhaan in hoj… Afaan Oromoo BCV GIZ ወሶበ ሰፋሕክዎ ለእስራኤል ትትከሠት ዓመፃሁ ለኤፍሬም ወእከያ ለሰማርያ እስመ ሐሰተ ገብሩ፤ ወያበውእ ሰራቄ ኀቤሁ ይስእል ወይሰልብ በፍኖት ከመ ይኅበር ማዕሌቶሙ። giz GAZGAZ “Yeroo ani Israa'elin fayyisuu barbaadutti, yakki Efreem, jal'inni Samaariyaas in mul'ata; isaan gowwoomsaadhaan in hoj… Afaan Oromoo BCV aksum ሓሰት ኣዘውቲሮም እዮም እሞ፥ ሰራቒ ይኣቱ፤ ኣብ ወፃኢ ድማ ሸፋቱ ይኸትሩ ኣለዉ እሞ፥ ንእስራኤል ክፍውሶ ምስ ደለኹ፥ ሓጢኣት ኤፍሬምን፥ ክፍኣት ሰማርያን ተቐልዐ። ትግርኛ AMHNIV እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣ የኤፍሬም ኀጢአት፣ የሰማርያም ክፋት ይገለጣል። እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ። አማርኛ SWAHSUV Wakati nitakapo kumponya Israeli, ndipo yafunuliwapo maovu ya Efraimu, na ubaya wa Samaria; maana wanatenda uongo, na m… Kiswahili