ትንቢተ ሆሴዕ 5

AMHEVGአማርኛ15 ጥቅሶች2:29 አዳምጥ
አዳምጥ 2:29 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ካህናት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ፥ ልብ አድርጉ፤ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።

2ዓመፀኞችም እርድ አብዝተዋል፤ እኔ ግን እነዚያን ሁሉ እዘልፋለሁ።

3ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፥ እስራኤልም ከእኔ አልተሰወረም፤ ኤፍሬም ሆይ፥ ዛሬ አመንዝረሃል፥ እስራኤልም ረክሶአል።

4ወደ አምላካቸው ይመለሱ ዘንድ ሥራቸውን አላቀኑም፤ የግልሙትና መንፈስ በውስጣቸው አለና፤ እግዚአብሔርንም አላውቁምና።

5የእስራኤልም ትዕቢት በፊቱ ይመሰክራል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በኃጢአታቸው ይሰናከላሉ፤ ይሁዳም ደግሞ ከእነሱ ጋር ይሰናከላል።

6እግዚአብሔርንም ለመሻት በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ነድተው ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱም ተመልሶአልና አያገኙትም።

7ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ወንጅለዋል፤ አሁንም አንድ ወር እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል።

8በጊብዓ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉና፦ “ብንያም ሆይ፥ ከአንተ በኋላ” እያላችሁ በቤትአዌን ላይ እሪ በሉ።

9ኤፍሬም በዘለፋ ቀን የፈረሰ ይሆናል። በእስራኤል ነገዶች ዘንድ በእርግጥ የሚሆነውን ነገር ገልጫለሁ።

10የይሁዳ አለቆች ድምበርን እንደሚነቅሉ ሆነዋል፤ እኔም መዓቴን እንደ ውኃ አፈስስባቸዋለሁ።

11ኤፍሬም ከትእዛዝ በኋላ መሄድን ወድዶአልና የተገፋና በፍርድ የተጐዳ ሆኖአል።

12እኔም ለኤፍሬም እንደ ብል፥ ለይሁዳም ቤት እንደ ነቀዝ ሆኜአለሁ።

13ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ ከቊስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም።

14እኔም ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄዳለሁ እወስድማለሁ፥ የሚያድንም አይገኝም።

15በደላቸውንም እስኪያውቁ ድረስ፥ ፊቴንም እስኪሹ ድረስ ሄጄ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤ በመከራቸው ጊዜ እጅግ አድርገው ፊቴን ይፈልጋሉ።

ማብራሪያ

5:1-7 የአምላክ ዘልቆ የሚያይ ዐይን፣ ድብቅ የኃጢአት ፍላጎትና ዝንባሌን፣ የእስራኤል ቤት ለኃጢአታቸው የነበራቸውን ፍቅር፣ እንዲሁም ኃጢአቶቻቸው በእነሱ ላይ የነበራቸውን ግዛት ተመለከተ። ትዕቢት ሰዎችን በሌሎች ኃጢአቶች ግትር ያደርጋል። ይሁዳም በተመሳሳይ እርምጃዎች ትሄድ ስለነበር፣ ከእስራኤል ጋር ትወድቃለች። ከጌታ ጋር በክህደት በመሥራት ሰዎች ራሳቸውን ብቻ ነው የሚያታልሉት። ጌታን በመንጋዎቻቸውና በከብቶቻቸው ብቻ ለመፈለግ የሚሄዱት፣ በልባቸውና በነፍሶቻቸው ሳይሆን፣ ሊያገኙት አይችሉም፤ በሚገኝበት ጊዜ ጌታን የማይፈልግ ማንም አይሳካለትም። አሁንም ገና ቀደም ብለን እግዚአብሔርን መፈለግ ምን ያህል ለእኛ ወሳኝ እንደሆነ ተመልከቱ፤ ምክንያቱም ይህ ተቀባይነት ያለው ጊዜና የመዳን ቀን ነው።

5:8-15 ንስሐ የማይገቡ ኃጢአተኞች ጥፋት እነርሱን ለማስፈራት የሚነገር ተራ ንግግር ብቻ አይደለም፤ እርሱ የማይሻር ፍርድ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “Hear this, you priests! Pay attention, you Israelites! Listen, O royal house! This judgment is against you: You have b… English BCV “ኣቱም ካህናት፥ ነዙይ ስምዑ፤ ኣቱም ቤት እስራኤል፥ ኣቕልቡ፤ ኣቱም ቤት ንጉስ፥ ፅን በሉ፤ ኣብ ምፅጳ መፈንጠር፥ ኣብ ታቦር ከዓ ዝተዘርግሐት መርበብ ኴንኹም ኢኹም እሞ፥ እዝ ፍርዲ እዙይ… ትግርኛ GAZBIB “Isin luboota nana kana dhaga'aa, yaa gurguddoota Israa'el, yaadatti qabadhaa; warri mana mootichaas gurra keessan as q… Afaan Oromoo BCV GIZ ስምዑ ዘንተ ካህናት ወአጽምዕዎ ቤተ እስራኤል ወይስምዕዎ ቤተ ነጋሢ፤ እስመ በእንቲአክሙ ውእቱ ዝንቱ ኵሉ ኵነኔ እስመ መሥገርተ ኮንክምዎ ለዘያስተሐይጽ፤ ወከመ መሥገርት እንተ ሰፍሑ ያሥግሩ… giz GAZGAZ “Isin luboota nana kana dhaga'aa, yaa gurguddoota Israa'el, yaadatti qabadhaa; warri mana mootichaas gurra keessan as q… Afaan Oromoo BCV aksum “ኣቱም ካህናት፥ ነዙይ ስምዑ፤ ኣቱም ቤት እስራኤል፥ ኣቕልቡ፤ ኣቱም ቤት ንጉስ፥ ፅን በሉ፤ ኣብ ምፅጳ መፈንጠር፥ ኣብ ታቦር ከዓ ዝተዘርግሐት መርበብ ኴንኹም ኢኹም እሞ፥ እዝ ፍርዲ እዙይ… ትግርኛ AMHNIV “እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ! እናንት እስራኤላውያን፤ አስተውሉ! የንጉሥ ቤት ሆይ፤ ስሙ! ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤ በምጽጳ ወጥመድ፣ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና። አማርኛ SWAHSUV Sikieni haya, enyi makuhani, sikilizeni, enyi nyumba ya Israeli, tegeni masikio yenu, enyi wa nyumba ya mfalme, kwa kuw… Kiswahili