ትንቢተ ሆሴዕ 5

AMHNIVአማርኛ15 ጥቅሶች2:55 አዳምጥ
አዳምጥ 2:55 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ! እናንት እስራኤላውያን፤ አስተውሉ! የንጉሥ ቤት ሆይ፤ ስሙ! ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤ በምጽጳ ወጥመድ፣ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።

2ዐመፀኞች በግድያ በርትተዋል፤ ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ።

3ስለ ኤፍሬም ሁሉን ዐውቃለሁ፤ እስራኤልም ከእኔ የተሰወረች አይደለችም፤ ኤፍሬም፣ አንተ አሁን አመንዝረሃል፤ እስራኤልም ረክሳለች።

4“የሠሩት ሥራ፣ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ የአመንዝራነት መንፈስ በልባቸው አለ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁትም።

5የእስራኤል ትዕቢት በራሷ ላይ ይመሰክራል፤ እስራኤላውያንና ኤፍሬምም በኀጢአታቸው ይሰናከላሉ፤ ይሁዳም ደግሞ አብሮአቸው ይሰናከላል።

6እግዚአብሔርን ለመሻት፣ የበግና የፍየል መንጋ እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻቸውን ነድተው ሲሄዱ፣ እርሱ ስለ ተለያቸው፣ ሊያገኙት አይችሉም።

7ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም፤ ዲቃሎች ወልደዋልና፤ ስለዚህ የወር መባቻ በዓላቸው፤ እነርሱንና ዕርሻቸውን ያጠፋል።

8“በጊብዓ መለከትን፣ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ በቤትአዌን የማስጠንቀቂያ ድምፅ አሰሙ፤ ‘ብንያም ሆይ፤ መጡብህ!’ በሉ።

9በቅጣት ቀን፣ ኤፍሬም ባድማ ይሆናል፣ በእስራኤል ነገዶች መካከል፣ በእርግጥ የሚሆነውን ዐውጃለሁ።

10የይሁዳ መሪዎች፣ የወሰን ድንጋዮችን እንደሚነቅሉ ሰዎች ናቸው፤ እንደ ጐርፍ ውሃ፣ ቊጣዬን በላያቸው ላይ አፈስሳለሁ።

11ጣዖትን መከተል በመውደዱ፣ ኤፍሬም ተጨቊኖአል፤ በፍርድም ተረግጦአል።

12እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፣ ለይሁዳም ሕዝብ እንደ ነቀዝ ሆኛለሁ።

13“ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቊስሉን ባየ ጊዜ፣ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ እርሱ ግን ሊያድናችሁ፣ ቊስላችሁንም ሊፈውስ አይችልም።

14እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና፤ ሰባብሬና አድቅቄአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።

15በደላቸውንም እስኪያውቁ ድረስ፣ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤ ፊቴን ይሻሉ፤ በመከራቸውም አጥብቀው ይፈልጉኛል።”

ማብራሪያ

5:1-7 የአምላክ ዘልቆ የሚያይ ዐይን፣ ድብቅ የኃጢአት ፍላጎትና ዝንባሌን፣ የእስራኤል ቤት ለኃጢአታቸው የነበራቸውን ፍቅር፣ እንዲሁም ኃጢአቶቻቸው በእነሱ ላይ የነበራቸውን ግዛት ተመለከተ። ትዕቢት ሰዎችን በሌሎች ኃጢአቶች ግትር ያደርጋል። ይሁዳም በተመሳሳይ እርምጃዎች ትሄድ ስለነበር፣ ከእስራኤል ጋር ትወድቃለች። ከጌታ ጋር በክህደት በመሥራት ሰዎች ራሳቸውን ብቻ ነው የሚያታልሉት። ጌታን በመንጋዎቻቸውና በከብቶቻቸው ብቻ ለመፈለግ የሚሄዱት፣ በልባቸውና በነፍሶቻቸው ሳይሆን፣ ሊያገኙት አይችሉም፤ በሚገኝበት ጊዜ ጌታን የማይፈልግ ማንም አይሳካለትም። አሁንም ገና ቀደም ብለን እግዚአብሔርን መፈለግ ምን ያህል ለእኛ ወሳኝ እንደሆነ ተመልከቱ፤ ምክንያቱም ይህ ተቀባይነት ያለው ጊዜና የመዳን ቀን ነው።

5:8-15 ንስሐ የማይገቡ ኃጢአተኞች ጥፋት እነርሱን ለማስፈራት የሚነገር ተራ ንግግር ብቻ አይደለም፤ እርሱ የማይሻር ፍርድ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ካህናት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ፥ ልብ አድርጉ፤ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው። አማርኛ ENGNIV “Hear this, you priests! Pay attention, you Israelites! Listen, O royal house! This judgment is against you: You have b… English BCV “ኣቱም ካህናት፥ ነዙይ ስምዑ፤ ኣቱም ቤት እስራኤል፥ ኣቕልቡ፤ ኣቱም ቤት ንጉስ፥ ፅን በሉ፤ ኣብ ምፅጳ መፈንጠር፥ ኣብ ታቦር ከዓ ዝተዘርግሐት መርበብ ኴንኹም ኢኹም እሞ፥ እዝ ፍርዲ እዙይ… ትግርኛ GAZBIB “Isin luboota nana kana dhaga'aa, yaa gurguddoota Israa'el, yaadatti qabadhaa; warri mana mootichaas gurra keessan as q… Afaan Oromoo BCV GIZ ስምዑ ዘንተ ካህናት ወአጽምዕዎ ቤተ እስራኤል ወይስምዕዎ ቤተ ነጋሢ፤ እስመ በእንቲአክሙ ውእቱ ዝንቱ ኵሉ ኵነኔ እስመ መሥገርተ ኮንክምዎ ለዘያስተሐይጽ፤ ወከመ መሥገርት እንተ ሰፍሑ ያሥግሩ… giz GAZGAZ “Isin luboota nana kana dhaga'aa, yaa gurguddoota Israa'el, yaadatti qabadhaa; warri mana mootichaas gurra keessan as q… Afaan Oromoo BCV aksum “ኣቱም ካህናት፥ ነዙይ ስምዑ፤ ኣቱም ቤት እስራኤል፥ ኣቕልቡ፤ ኣቱም ቤት ንጉስ፥ ፅን በሉ፤ ኣብ ምፅጳ መፈንጠር፥ ኣብ ታቦር ከዓ ዝተዘርግሐት መርበብ ኴንኹም ኢኹም እሞ፥ እዝ ፍርዲ እዙይ… ትግርኛ SWAHSUV Sikieni haya, enyi makuhani, sikilizeni, enyi nyumba ya Israeli, tegeni masikio yenu, enyi wa nyumba ya mfalme, kwa kuw… Kiswahili