መጽሐፈ መክብብ 5

AMHNIVአማርኛ20 ጥቅሶች3:32 አዳምጥ
አዳምጥ 3:32 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትሄድ እግርህን ጠብቅ። ለመስማት መቅረብ የሰነፎችን መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤ እነርሱ ክፉ እንደሚሠሩ አያውቁምና።

2በአፍህ አትፍጠን፤ በእግዚአብሔርም ፊት ማንኛውንም ነገር ለመናገር፣ በልብህ አትቸኵል፤ እግዚአብሔር በሰማይ፣ አንተ ደግሞ በምድር ነህ፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን።

3በሥራ ብዛት ሕልም እንደሚታይ፣ ብዙ ቃል ባለበትም የሞኝ ንግግር ይገለጣል።

4ለእግዚአብሔር ስእለትን በተሳልህ ጊዜ ለመፈጸም አትዘግይ፤ በሰነፎች ደስ አይለውምና፤ ስእለትህን ፈጽም።

5ስእለት ተስሎ ካለመፈጸም፣ አለመሳል ይሻላል።

6አንደበትህ ወደ ኀጢአት እንዲመራህ አትፍቀድ፤ ለቤተ መቅደስ መልእክተኛም፣ “የተሳልሁት በስሕተት ነበር” አትበል። እግዚአብሔር በተናገርኸው ተቈጥቶ የእጅህን ሥራ ለምን ያጥፋ?

7ብዙ ሕልምና ብዙ ቃል ከንቱ ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔርን ፍራ።

8በአገር ውስጥ ድኻ ተጨቍኖ፣ ፍትሕ ተጓድሎ፣ መብትም ተረግጦ ብታይ፣ እንደነዚህ ባሉ ነገሮች አትደነቅ፤ ምክንያቱም አንዱን አለቃ የበላዩ ይመለከተዋል፤ በእነዚህ በሁለቱም ላይ ሌሎች ከፍ ያሉ አሉ።

9ከምድሩ የሚገኘው ትርፍ ለሁሉም ነው፤ ንጉሡም ራሱ የሚጠቀመው ከዕርሻ ነው።

10ገንዘብን የሚወድ፣ ገንዘብ አይበቃውም፤ ብልጽግናም የሚወድ፣ በትርፉ አይረካም፤ ይህም ከንቱ ነው።

11ሀብት በበዛ ቊጥር፣ ተጠቃሚውም ይበዛል፤ በዐይኑ ብቻ ከማየት በቀር ታዲያ፣ ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል?

12ጥቂትም ይሁን ብዙ ቢበላ፣ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው፤ የሀብታም ሰው ብልጽግና ግን እንቅልፍ ይነሣዋል።

13ከፀሓይ በታች የሚያሳዝን ክፉ ነገር አየሁ፦ ይህም ለባለቤቱ ጒዳት የተከማቸ ሀብት፣

14ወይም በአንድ መጥፎ አጋጣሚ የጠፋ ብልጽግና ነው፤ ልጅ ሲወልድም፣ ለእርሱ የሚያስቀርለት ምንም ነገር አይኖርም።

15ሰው ከእናቱ ማሕፀን ዕራቊቱን ይወለዳል፤ እንደ መጣው እንዲሁ ይመለሳል። ከለፋበትም ነገር፣ አንድም እንኳ በእጁ ይዞ ሊሄድ አይችልም።

16ይህ ደግሞ እጅግ ክፉ ነገር ነው፤ ሰው እንደ መጣ እንዲሁ ይሄዳል፤ የሚደክመው ለነፋስ ስለ ሆነ፣ ትርፉ ምንድ ነው?

17በብዙ ጭንቀት፣ መከራና ብስጭት፣ ዘመኑን ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይበላል።

18የሰው ዕጣው ይህ ስለ ሆነ፣ እግዚአብሔር በሰጠው በጥቂት ዘመኑ ከፀሓይ በታች በሚደክምበት ነገር ርካታን ያገኝ ዘንድ፣ መብላቱና መጠጣቱም መልካምና ተገቢ መሆኑን ተገነዘብሁ።

19እግዚአብሔር ለሰው ባለጠግነትና ሀብት መስጠቱ፣ እንዲደሰትበትም ማስቻሉ፣ ዕጣውን እንዲቀበልና በሥራውም እንዲደሰት ማድረጉ፣ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።

20እግዚአብሔር የልብ ደስታ ስለሚሰጠውም በሕይወቱ ዘመን ያሉትን ቀናት እምብዛም አያስባቸውም።

ማብራሪያ

5:1-3 ራስህን ወደ እግዚአብሔር አምልኮ አቅና፤ ለዚህም ራስህን ለማዘጋጀት ጊዜ ውሰድ። ሐሳቦችህ ከመንከራተትና ከመባዘን ጠብቅ፤ ፍላጎቶችህም ወደ ተሳሳቱ ነገሮች እንዳይሳቡ ተጠንቀቅ። ከንቱ ድግግሞሾችን ልንርቅ ይገባል። ብዙ ጸሎቶች እዚህ አይወገዙም፣ ነገር ግን ትርጉም የሌላቸው ናቸው። ምን ያህል ጊዜ የሚንከራተቱ ሐሳቦቻችን በመለኮታዊ ሥርዓቶች ላይ የምናደርገውን ተሳትፎ ከሰነፎች መሥዋዕትነት እምብዛም አይሻልም። በጸሎት ውስጥ የሚነገሩ ብዙና የተጣደፉ ቃላት በልብ ውስጥ ያለውን ሞኝነት፣ ስለ እግዚአብሔር ያለንን ዝቅተኛ ሐሳብ፣ እንዲሁም ስለ ነፍሶቻችንም ያለንን ግድ የለሽነት ያሳያሉ።

5:4-8 አንድ ሰው በችኮላ ቃልኪዳን ሲያደርግ፣ አፉ ለሥጋው ኃጢአት ምክንያት ሆነ። ይህ ሁኔታ የሚያመለክተው አንድ ሰው ወደ ካህን ቀርቦ፣ ቃልኪዳኑን በችኮላ እንደፈጸመውና እሱን መፈጸም ስህተት እንደሆነ በማስመሰል ነበር። እንዲህ ያለው እግዚአብሔርን ማሾፍ፣ የእግዚአብሔርን ቁጣ ያስከትል ነበር፤ ይህም ባልተገባ መንገድ የያዘውን ሁሉ ሊያጠፋው ይችላል። የሰውን ፍርሃት መግታት አለብን። እግዚአብሔርን ከፊትህ አስቀድም። ያንጊዜም የድሆችን ጭቆና ባየህ ጊዜ፣ መለኮታዊውን አሳቢነት አትነቅፍም። ዓላማዎቹ በዚህ መንገድ ሲዛቡ ባየህ ጊዜም፣ የአስተዳደር ሥርዓትን አታጣጥልም፤ ሰዎችን ከበደል ለመጠበቅ እንደማይችል ስታይም ሃይማኖትን አትነቅፍም። ጨቋኞች ደኅንነት ያላቸው ቢመስሉም፣ እግዚአብሔር ግን ሁሉንም ይጠይቃል።

5:9-17 የእግዚአብሔር አቅርቦት መልካምነት በግዴለሽነት ለሚያይ ሰው ከሚታየው በላይ በተመጣጣኝ ሁኔታ የተከፋፈለ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይበልጣልና፤ እነርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና። አማርኛ ENGNIV Guard your steps when you go to the house of God. Go near to listen rather than to offer the sacrifice of fools, who do… English BCV ናብ ቤት እግዚኣብሄር እንትትኣቱ እግርኻ ሓሉ፤ ክፉእ ከም ዝገብሩ ኣይፈልጡን እዮምሞ ኻብ መስዋእቲ ሰነፋት፥ ክትሰምዕ ምቕራብ ይሐይሽ። ትግርኛ GAZBIB Mana Waaqayyootti yommuu ol lixxu miilla kee eeggadhu! Dhaga'uudhaaf ol lixi! Dhaga'uun aarsaa isa warri gowwoonni dhi'… Afaan Oromoo BCV GIZ ዕቀብ እገሪከ ሶበ ተሐውር ኀበ እግዚአብሔር ወቅረብ ለሰሚዕ እምነ ሀብቶሙ ለአብዳን መሥዋዕተከ እስመ ኢኮኑ ማእምራነ ለገቢረ ሠናይ። giz GAZGAZ Mana Waaqayyootti yommuu ol lixxu miilla kee eeggadhu! Dhaga'uudhaaf ol lixi! Dhaga'uun aarsaa isa warri gowwoonni dhi'… Afaan Oromoo BCV aksum ናብ ቤት እግዚኣብሄር እንትትኣቱ እግርኻ ሓሉ፤ ክፉእ ከም ዝገብሩ ኣይፈልጡን እዮምሞ ኻብ መስዋእቲ ሰነፋት፥ ክትሰምዕ ምቕራብ ይሐይሽ። ትግርኛ SWAHSUV Jitunze mguu wako uendapo nyumbani kwa Mungu; Maana ni heri kukaribia ili usikie, Kuliko kutoa kafara ya wapumbavu; Amb… Kiswahili