መጽሐፈ መክብብ 6

AMHEVGአማርኛ12 ጥቅሶች2:03 አዳምጥ
አዳምጥ 2:03 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም በሰው ላይ እጅግ የከበደ ነው።

2እግዚአብሔር ለሰው ሀብትንና ጥሪትን ክብርንም ሰጠው፥ ከወደደውም ሁሉ ለነፍሱ አልጐደለውም፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበላዋል እንጂ ከእርሱ ይበላ ዘንድ እግዚአብሔር አላሠለጠነውም፤ ይህም ከንቱና ክፉ ደዌ ነው።

3ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነፍሱም መልካምን ባትጠግብ መቃብርንም ባያገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፦ “ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል፡” አልሁ።

4በከንቱ መጥቶአል በጨለማ ይሄዳል ስሙም በጨለማ ይሸፈናል፤

5ደግሞም ፀሐይን አላየውም አላወቀውምም፤ ለዚህም ከዚያ ይልቅ ዕረፍት አለው።

6ሺህ ዓመት ሁለት ጊዜ በሕይወት ቢኖር መልካምንም ባያይ፥ ሁሉ ወደ አንድ ስፍራ የሚሄድ አይደለምን?

7የሰው ድካም ሁሉ ለአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አትጠግብም።

8ከሰነፍ ይልቅ ለጥበበኛ ጥቅም ምንድር ነው? በሕያዋን ፊትስ መሄድ ለሚያውቅ ለድሀ ጥቅሙ ምንድር ነው?

9በዓይን ማየት በነፍስ ከመቅበዝበዝ ይሻላል፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

10የሆነው ስሙ አስቀድሞ ተጠራ፥ ሰውም እንደ ሆነ ታወቀ፤ ከእርሱ ከሚበረታው ጋር ይፋረድ ዘንድ አይችልም።

11ከንቱን የሚያበዛ ብዙ ነገር አለና ለሰው ጥቅሙ ምንድር ነው?

12ሰው በከንቱ ወራቱ ቍጥርና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ለሰው ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?

ማብራሪያ

6:1-6

ሰው ብዙውን ጊዜ ለውጫዊ ደስታው የሚያስፈልገውን ሁሉ አለው፤ ሆኖም ጌታ ለስስት ወይም ለክፉ ዝንባሌዎች አሳልፎ ይሰጠዋልና ያለውን ነገር በመልካም ወይም በሚያስደስት መንገድ መጠቀም አይችልም። በሆነ መንገድ ወይም በሌላ ንብረቶቹ ለባዕድ እጅ ይወድቃሉ፤ ይህ ከንቱነትና ክፉ ደዌ ነው። በዕብራውያን ዘንድ ብዙ ቤተሰብ ትልቅ ምኞትና የከበረ ክብር ነበር፤ ረጅም ዕድሜም በአጠቃላይ የሰው ልጆች ሁሉ ምኞት ነው። እነዚህ ነገሮች ቢጨመሩለትም አንድ ሰው ሀብቱን፣ ቤተሰቡንና ሕይወቱን ሊደሰትበት አይችልም። እንዲህ ያለው ሰው በሕይወቱ ጉዞ ያለ ዓላማ ወይም ጥቅም የተወለደ ይመስላል። ለቅፅበት ብቻ ወደ ሕይወት የገባና በሚቀጥለው ቅፅበት የሚተዋት ሰው ለረጅም ጊዜ ለመሰቃየት ብቻ ከኖረ ሰው የተሻለ ዕጣ ፈንታ አለው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6