ትንቢተ አሞጽ 9

AMHEVGአማርኛ15 ጥቅሶች3:01 አዳምጥ
አዳምጥ 3:01 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፦ “መድረኮቹ ይናወጡ ዘንድ ጕልላቶቹን ምታ፥ በራሳቸውም ሁሉ ላይ ሰባብራቸው፤ እኔም ከእነርሱ የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ፤ የሚሸሽ አያመልጥም፥ የሚያመልጥም አይድንም።

2ወደ ሲኦል ቢወርዱ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ ወደ ሰማይም ቢወጡ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤

3በቀርሜሎስም ራስ ውስጥ ቢሸሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፤

4በጠላቶቻቸውም ፊት ተማርከው ቢሄዱ ከዚያ ሰይፍን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይገድላቸዋል፤ ዓይኔንም በእነርሱ ላይ ለክፋት እንጂ ለመልካም አላደርግም።”

5የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድርን ይዳስሳል እርስዋም ትቀልጣለች፥ የሚኖሩባትም ሁሉ ያለቅሳሉ፤ ሙላዋም እንደ ግብፅ ወንዝ ትነሣለች፥ ደግሞ እንደ ግብፅ ወንዝ ትወርዳለች።

6አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ጠፈሩንም በምድር ላይ የመሠረተ፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።

7የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብፅ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?

8እነሆ፥ የጌታ የእግዚአብሔር ዓይኖች በኃጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፥ ከምድርም ፊት አጠፋታለሁ፤ ነገር ግን የያዕቆብን ቤት ፈጽሜ አላጠፋም፥ ይላል እግዚአብሔር።

9እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ እህልም በወንፊት እንዲነፋ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እነፋለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።

10ክፉው ነገር አይደርስብንም፥ አያገኘንምም የሚሉ የሕዝቤ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።

11በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፥ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤

12ይኸውም የኤዶምያስን ቅሬታ፥ ስሜም የተጠራባቸውን አሕዛብን ሁሉ ይወርሱ ዘንድ ነው፥ ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።

13እነሆ፥ አራሹ አጫጁን፥ ወይን ጠማቂውም ዘሪውን የሚያገኝበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ተራሮችም በተሀውን የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ይቀልጣሉ።

14የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፥ የፈረሱትንም ከተሞች ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁንም ይጠጣሉ፤ አታክልትንም ያባጃሉ፥ ፍሬውንም ይበላሉ።

15በምድራቸውም እተክላቸዋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም፥ ይላል አምላክህ እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

9:1-10 ነቢዩም በራእይ እግዚአብሔርን በቤቴል ባለው የጣዖት መሠዊያ ላይ ቆሞ አየ። ኃጢአተኞች ከእግዚአብሔር ፍርድ የትም ቢሸሹ፣ ፍርዱ ይደርስባቸዋል። እግዚአብሔር በጸጋው ወደ ሰማይ የሚያመጣቸውን በፍጹም አይወድቁም፤ ነገር ግን በራሳቸው በከንቱ በመታመን ወደዚያ ለመውጣት የሚሞክሩት ግን ይጣላሉ፣ በኀፍረትም ይሞላሉ። ማምለጥን የማይቻል፣ ጥፋትንም እርግጠኛ የሚያደርገው ነገር ቢኖር፣ እግዚአብሔር ዓይኖቹን በእነርሱ ላይ ለክፉ እንጂ ለበጎ አለማስቀመጡ ነው። ጌታ ለክፉ እንጂ ለበጎ የማይመለከትላቸው ወዮላቸው! ጌታ አይሁድን ይበትናቸዋል፣ እህል በወንፊት እንደሚናወጥ ሁሉ በመከራም ይጎበኛቸዋል። ነገር ግን ከእነርሱ አንዳንዶችን ያድናል። የአይሁድን እንደ የተለየ ሕዝብ ሆኖ አስደናቂ አጠባበቅ እዚህ ላይ አስቀድሞ የተነገረ ይመስላል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV I saw the Lord standing by the altar, and he said: “Strike the tops of the pillars so that the thresholds shake. Bring … English BCV ንጐይታ ኣብ ጥቓ መሰውኢ ደው ኢሉ እንተሎ ረአኽዎ። ንሱውን ከምዙይ በለ፦ “እቲ ልዳውቲ ኽሳዕ ዝነቓነቕ ነቲ ጕልላት ውቕዓዮ፤ ተሰባቢሩ ኸዓ ኣብ ርእሲ እቶም ህዝቢ ይውደቕ። ኣነ ኸዓ ነቶም… ትግርኛ GAZBIB Ammas Waaqayyo gooftaan iddoo aarsaa gara irraa utuu dhaabatuu mul'ataan nan arge; inni,“Manichi guutummaatti akka raaf… Afaan Oromoo BCV GIZ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር ይቀውም ዲበ ምሥዋዕ ወይቤለኒ፦ ዝብጥ ዲበ ምሥሃል ወያድለቀልቅ ዴዳያት እስመ እቀትሎሙ በኲናት ወይመትርዎሙ አርእስቲሆሙ፤ ወአልቦ ዘያመስጥ እምእለ ተርፉ ወአልቦ ዘይድ… giz GAZGAZ Ammas Waaqayyo gooftaan iddoo aarsaa gara irraa utuu dhaabatuu mul'ataan nan arge; inni,“Manichi guutummaatti akka raaf… Afaan Oromoo BCV aksum ንጐይታ ኣብ ጥቓ መሰውኢ ደው ኢሉ እንተሎ ረአኽዎ። ንሱውን ከምዙይ በለ፦ “እቲ ልዳውቲ ኽሳዕ ዝነቓነቕ ነቲ ጕልላት ውቕዓዮ፤ ተሰባቢሩ ኸዓ ኣብ ርእሲ እቶም ህዝቢ ይውደቕ። ኣነ ኸዓ ነቶም… ትግርኛ AMHNIV ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “መድረኮቹ እንዲናወጡ፣ ጒልላቶቹን ምታ፣ በሕዝቡም ሁሉ ራስ ላይ ሰባብራቸው፤ የቀሩትን በሰይፍ እገድላቸዋለሁ፤ ከእነርሱ አንድም… አማርኛ SWAHSUV Nalimwona Bwana akisimama karibu na madhabahu; akasema, vipigo vichwa vya nguzo, hata vizingiti vitikisike; vivunje vip… Kiswahili