የሐዋርያት ሥራ 23

AMHEVGአማርኛ35 ጥቅሶች4:51 አዳምጥ
አዳምጥ 4:51 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጳውሎስም ሸንጎውን ትኵር ብሎ ተመልክቶ፦ “ወንድሞች ሆይ፥ እኔ እስከዚች ቀን ድረስ በመልካም ሕሊና ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ኖሬአለሁ” አለ።

2ሊቀ ካህናቱም ሐናንያ አፉን ይመቱት ዘንድ በአጠገቡ ቆመው የነበሩትን አዘዘ።

3በዚያን ጊዜ ጳውሎስ፦ “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ፥ እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን?” አለው።

4በአጠገቡ የቆሙትም፦ “የእግዚአብሔርን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህን?” አሉት።

5ጳውሎስም፦ “ወንድሞች ሆይ፥ ሊቀ ካህናት መሆኑን ባላውቅ ነው፤ ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር’ ተብሎ ተጽፎአልና” አላቸው።

6ጳውሎስ ግን እኵሌቶቹ ሰዱቃውያን እኵሌቶቹም ፈሪሳውያን መሆናቸውን አይቶ፦ “ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ፈሪሳዊ የፈሪሳዊም ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስፋና ስለ ሙታን መነሣት ይፈርዱብኛል፡” ብሎ በሸንጎው ጮኸ።

7ይህንም ባለ ጊዜ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ጥል ሆነ ሸንጎውም ተለያየ።

8ሰዱቃውያን፦ “ትንሣኤም መልአክም መንፈስም የለም” የሚሉ ናቸውና፤ ፈሪሳውያን ግን ሁለቱን ያምናሉ።

9ታላቅ ጩኸትም ሆነ፥ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑት ጻፎች ተነሥተው፦ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይስ መልአክ ተናግሮት ይሆን?” ብለው ተከራከሩ።

10ብዙ ጥልም በሆነ ጊዜ የሻለቃው ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ጭፍሮቹ ወርደው ከመካከላቸው እንዲነጥቁት ወደ ሰፈሩም እንዲያገቡት አዘዘ።

11በሁለተኛውም ሌሊት ጌታ በአጠገቡ ቆሞ፦ “ጳውሎስ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርህ እንዲሁ በሮሜም ትመሰክርልኝ ዘንድ ይገባሃልና አይዞህ፡” አለው።

12በጠባም ጊዜ አይሁድ ጳውሎስን እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ በመሐላ ተስማሙ።

13ይህንም ሴራ ያደረጉት ሰዎች ከአርባ ይበዙ ነበር፤

14እነርሱም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ሽማግሌዎቹ መጥተው፦ “ጳውሎስን እስክንገድል ድረስ ምንም እንዳንቀምስ ተረጋግመን ተማምለናል።

15እንግዲህ አሁን እናንተ ከሸንጎው ጋር ሆናችሁ ስለ እርሱ አጥብቃችሁ እንደምትመረምሩ መስላችሁ ወደ እናንተ እንዲያወርደው ለሻለቃው አመልክቱት፤ እኛም ሳይቀርብ እንድንገድለው የተዘጋጀን ነን” አሉአቸው።

16የጳውሎስ የእኅቱ ልጅ ግን ደባቸውን በሰማ ጊዜ፥ መጥቶ ወደ ሰፈሩ ገባና ለጳውሎስ ነገረው።

17ጳውሎስም ከመቶ አለቆች አንዱን ጠርቶ፦ “ይህን ብላቴና ወደ ሻለቃው ውሰድ፥ የሚያወራለት ነገር አለውና፡” አለው።

18እርሱም ይዞት ወደ ሻለቃው ወሰደውና፦ “ይህ ብላቴና የሚነግርህ ነገር ስላለው እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶ ወደ አንተ እንድወስደው ለመነኝ” አለው።

19የሻለቃውም እጁን ይዞ ፈቀቅ አለና ለብቻው ሆኖ፦ “የምታወራልኝ ነገር ምንድር ነው?” ብሎ ጠየቀው።

20እርሱም፦ “አይሁድ ስለ ጳውሎስ ከፊት ይልቅ አጥብቀህ እንደምትመረምር መስለህ፥ ነገ ወደ ሸንጎ ታወርደው ዘንድ ሊለምኑህ ተስማምተዋል።

21እንግዲህ አንተ በጅ አትበላቸው፤ እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተማምለው ከእነርሱ ከአርባ የሚበዙ ሰዎች ያደቡበታልና፤ አሁንም የተዘጋጁ ናቸው የአንተንም ምላሽ ይጠብቃሉ፡” አለው።

22የሻለቃውም፦ “ይህን ነገር ለእኔ ማመልከትህን ለማንም እንዳትገልጥ” ብሎ ካዘዘ በኋላ ብላቴናውን አሰናበተው።

23ከመቶ አለቆቹም ሁለት ጠርቶ፦ “ወደ ቂሣርያ ይሄዱ ዘንድ ሁለት መቶ ወታደሮችንና ሰባ ፈረሰኞችን ሁለት መቶም ባለ ጦር መሣሪያዎችን ከሌሊቱ በሦስተኛው ሰዓት አዘጋጁ፡” አላቸው።

24ጳውሎስንም ወደ አገረ ገዡ ወደ ፊልክስ በደኅና እንዲያደርሱት የሚያስቀምጡበትን ከብት ያዘጋጁ ዘንድ አዘዛቸው።

25ደብዳቤም ጻፈ እንዲህ የሚል፦

26“ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ ወደ ክቡር አገረ ገዡ ወደ ፊልክስ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን።

27ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ባሰቡ ጊዜ ከጭፍሮቹ ጋር ደርሼ አዳንሁት፥ ሮማዊ እንደ ሆነ አውቄ ነበርና።

28የሚከሰስበትንም ምክንያት አውቅ ዘንድ አስቤ ወደ ሸንጎአቸው አወረድሁት፤

29በሕጋቸውም ስለ መከራከር እንደ ከሰሱት አገኘሁ እንጂ ለሞት ወይም ለእስራት የሚያደርስ ክስ አይደለም።

30በዚህም ሰው አይሁድ ሴራ እንዲያደርጉበት ባመለከቱኝ ጊዜ ያን ጊዜውን ወደ አንተ ሰደድሁት፥ ከሳሾቹንም ደግሞ በፊትህ ይከሱት ዘንድ አዘዝኋቸው። ደኅና ሁን።”

31ወታደሮቹም እንደ ታዘዙት ጳውሎስን ይዘው በሌሊት ወደ አንቲጳጥሪስ አደረሱት፤

32በነገውም ከእርሱ ጋር ይሄዱ ዘንድ ፈረሰኞችን ትተው ወደ ሰፈር ተመለሱ።

33እነዚያም ወደ ቂሣርያ ገብተው ደብዳቤውን ለአገረ ገዡ በሰጡ ጊዜ ጳውሎስን ደግሞ በፊቱ አቆሙት።

34ካነበበውም በኋላ የወዴት አውራጃ እንደ ሆነ ጠየቀው፤ የኪልቅያ ሰው መሆኑንም ባወቀ ጊዜ።

35“ከሳሾችህ ደግሞ ሲመጡ እሰማሃለሁ” አለው፤ በሄሮድስም ግቢ ውስጥ ይጠብቁት ዘንድ አዘዘ።

ማብራሪያ

23:1-5 እዚህ ዘንድ የታማኝ ሰው ባሕርይ እናገኛለን። እግዚአብሔርን በፊቱ ያደርጋል፥ በፊቱም ያለ ይመስል ይኖራል። የሚናገረውንና የሚያደርገውን በሕሊናው ይመረምራል፤ በሚያውቀውም መጠን ከክፉ ነገር ሁሉ ይርቃል፥ መልካሙንም ይጠጋል። በንግግሩና በምግባሩ ሁሉ በሕሊናው ይጠነቀቃል። እንዲህ በእግዚአብሔር ፊት የሚኖሩ ሁሉ፥ እንደ ጳውሎስ ሁሉ፥ በእግዚአብሔር ፊትም በሰው ፊትም መተማመን ይኖራቸዋል። የጳውሎስ መልስ ቅን የሆነ ተግሣጽና ትንቢትን ያካተተ ቢሆንም፥ እነዚያን በተናገረበት ወቅት ስለደረሰበት አያያዝ እጅግ ተቆጥቶ የነበረ ይመስላል። ታላላቅ ሰዎች ስለ ስህተታቸው ሊነገራቸው ይችላል፥ ሕዝባዊ ቅሬታዎችም በተገቢው መንገድ ሊቀርቡ ይችላሉ፤ የእግዚአብሔር ሕግ ግን ለሥልጣን ላይ ላሉት አክብሮትን ይጠይቃል።

፳፫፥፮-፲፩ ፈሪሳውያን የየሁዳውያን ቤተ ክርስቲያን እምነት ትክክለኛ ተከታዮች ነበሩ። ሰዱቃውያን ግን ለመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ለመለኮታዊ ራእይ ወዳጆች አልነበሩም፤ የወደፊቱን ሕይወት ይክዱ ነበር፤ የዘላለም ደስታ ተስፋም ሆነ የዘላለም ቅጣት ፍርሃት አልነበራቸውም። ክርስቲያን ስለመሆኑ ጥያቄ በቀረበበት ጊዜ፣ ጳውሎስ የሙታን ትንሣኤ ተስፋ እንደተጠየቀ በእውነት ተናግሮ ነበር። በዚህ አከራካሪ ነጥብ ላይ የራሱን አመለካከት በመናገር፣ ፈሪሳውያንን ከማሳደድ እንዲያስወግዳቸውና ከዚህ ሕገወጥ ብጥብጥ እንዲጠብቁት ማድረግ ለእርሱ ተገቢ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Paul looked straight at the Sanhedrin and said, “My brothers, I have fulfilled my duty to God in all good conscience to… English BCV ሽዑ ጳውሎስ፥ ነቶም ኣብ መጋባእያ ዝተኣከቡ ኣትኲሩ እናጠመተ “ኣቱም ኣሕዋተይ፥ ኣነ ኽሳዕ እዛ መዓልቲ እዚኣ፥ ኣብ ቕድሚ እግዚኣብሄር ብንፁህ ሕሊና እየ ዝተመላለስኩ” በሎም። ትግርኛ GAZBIB Phaawulos ija warra yaa'ii keessa ilaalee, ?Jarreen obboloota nana! Ani hamma guyyaa har'aatti garaan koo utuu ana hin … Afaan Oromoo BCV GIZ ወነጺሮ ጳውሎስ ዐውደ ይቤሎሙ፦ “አንሰኬ ኦ አኀውየ በኵሉ ትምህርት ሠናይ ተፀመድክዎ ለእግዚአብሔር እስከ ዛቲ ዕለት።” giz GAZGAZ Phaawulos ija warra yaa'ii keessa ilaalee, ?Jarreen obboloota nana! Ani hamma guyyaa har'aatti garaan koo utuu ana hin … Afaan Oromoo BCV aksum ሽዑ ጳውሎስ፥ ነቶም ኣብ መጋባእያ ዝተኣከቡ ኣትኲሩ እናጠመተ “ኣቱም ኣሕዋተይ፥ ኣነ ኽሳዕ እዛ መዓልቲ እዚኣ፥ ኣብ ቕድሚ እግዚኣብሄር ብንፁህ ሕሊና እየ ዝተመላለስኩ” በሎም። ትግርኛ AMHNIV ጳውሎስም ወደ ሸንጎው ትኵር ብሎ በመመልከት፣ “ወንድሞች ሆይ፤ እኔ እስከዚች ቀን ድረስ በእግዚአብሔር ፊት በንጹሕ ሕሊና ተመላልሻለሁ” አለ። አማርኛ SWAHSUV Paulo akawakazia macho watu wa baraza, akasema, Ndugu zangu, mimi kwa dhamiri safi kabisa nimeishi mbele za Mungu hata … Kiswahili