ይቅርታ
36 ቁጥሮች15አማርኛዘጸ 34:6-7
ዘኍ 14:19-20
ዳዊ 19:12
12ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።
ዳዊ 25:7
7የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ፤ አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ።
ዳዊ 25:18
18ድካሜንና መከራዬን እይ፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
ዳዊ 32:1-2
ዳዊ 85:2-3
ዳዊ 86:3-5
ዳዊ 103:1-14
1ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን።
2ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ፤
3ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥
4ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ፥
5ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጕልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።
6እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።
7ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን።
8እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ።
9ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘላለምም አይቈጣም።
10እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።
11ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ።
12ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥ እንዲሁ ኃጢአታችንን ከእኛ አራቀ።
13አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፡ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤
14ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ።
ማቴ 6:12
12እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በለን፤
ማቴ 6:14-15
ማቴ 12:31-32
ማር 2:7
7“ይህ ሰው ስለ ምን እንደዚህ ያለ ስድብ ይናገራል? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው አሰቡ።
2ኛ ጴጥ 3:9
9ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
1ኛ ዮሐ 2:12
12ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ።