አጽናኝ
13 ቁጥሮች11አማርኛ2ኛ ቆሮ 1:3-4
ዳዊ 94:19
19አቤቱ፥ ለልቤ እንደ መከራዋ ብዛት፡ ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።
ማቴ 5:4
4የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።
ዮሐ 14:18
18ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
ዳዊ 118:5
5በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ሰማኝ አሰፋልኝም።
ዮሐ 16:7
7እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።
ኢሳ 51:12
12የማጽናናችሁ እኔ ነኝ፥ እኔ ነኝ፤ የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ትፈራ ዘንድ አንተ ማን ነህ?
ዮሐ 14:26
26አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
ራእ 7:16-17
ዮሐ 15:26
26ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤
2ኛ ቆሮ 1:5
5የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ እንደ በዛ፥ እንዲሁ መጽናናታችን ደግሞ በክርስቶስ በኩል ይበዛልናልና።